Wednesday, May 25, 2022

ሃይማኖታዊ በዐላት፡- እርግማኖች ወይስ በረከቶች?

ህዝባዊ በዐላትን የምታባክነው ኢትዮጲያ

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

 

በአዲስ አበባ መስተዳድር ታቅዶ ሲከናወን የነበረው የመስቀል አደባባይ ግንባታ ከልማት አንድምታው ይልቅ ሃይማኖታዊ እንድምታው ጎልቶ የመከራከሪያ ነጥብ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ አዲስ አባባ ከምትታወቅባቸው ባህሪያት አንዱ የመኪና ማቆሚያ የሌላቸው ፎቆቿ ናቸው፡፡ የመኪና ማቆሚያ በዲዛይኖቻቸው ላይ አስገብተው ያስገነቡ የፎቅ ባለቤቶች አንኳን ቀስ በቀስ ሸንሽነው ማከራየትን አንደ ባህል ከተያያዙት ቆይተዋል፡፡ ባለመኪና ከመሆን እግረኛ መሆን ይሻላል እስኪባል ድረስ መኪና ማቆሚያ አጥቶ መንከራተት የከተማዋ ገጽታ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

ይህ ያሳሰበው የሚመስለው አስተዳደሩ የመኪና ማቆሚያ ችግር ይፈታል ያለውን ፕሮጀክት ነድፎ በመስቀል አደባባይ ስር ሲያስገነባ ቆይቷል፡፡ ይህ ከ5000 በላይ ሰራተኞች ተሳትፈውበታል የተባለውና ስራ ሲጀምር 1400 መኪኖችን በአንድ ላይ ያቆማል የተባለው ፕሮጀክት ከመጠናቀቁ ቀደም ብሎ የፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ጭቅጭቅ ምክኒያት ሆኖም ነው የቆየው፡፡

የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዩኔስኮ ያስመዘገበችውን የመስቀል በዐሏን ምዕመኖቿን ሰብስባ የምታከብርበት አካባቢ እንደመሆኑ፤ ፕሮጀክቱ ከመስቀል በፊት ካልተጠናቀቀ ከፍተኛ ቅሬታ ይፈጠራል የሚሉ መላምቶችም ነበሩ፡፡ የኮሮና ቫይረስ የብዙ ሰዎችን መሰብሰብ በመከልከሉ የመንግስትና የቤተክርስቲያኒቱ ግብግብ ሳይፈጠር ቀርቷል፡፡

የኢትዮጲያን ሄራልድ በመስከረም 2019 እ.ኤ.አ. የሚስቴሩን የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይክተርን ጠቅሶ እንደዘገበው የመስቀል በዐል በዩኔስኮ ከተዘገበ ወዲህ በዐሉን የሚታደሙ ቱሪስቶች በእጥፍ እንደጨመረ ዘግቧል፡፡ ዳይሬክተሩ ከ2017 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ ይህ ቁጥር እጅጉን ማሽቆልቆሉንም ነግረውኛል ይላል ዘገባው፡፡

ለሃይማኖቱ ተከታይ እና ለበዐሉ ታዳሚ ግን ነገሩ ከዚህም ሊከፋ ይችላል፡፡ እዮብ ተመስገን አዲስ አበባ ተወልዶ ያደገ የፒያሳ ልጅ ነው፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ የመስቀል በዐልን መታደም አንድም ቀን አምልጦት እነደማያውቅ ይናገራል፡፡

እኛ እኮ ለፖለቲካ ግብግብ ብለን የምናደርገው አይደለም፤ ከልጅነታችን ጀምሮ በወላጆቻችን ትከሻ ላይ ሆነን ከመሄድ ጀምሮ አሁን ደግሞ ልጆቻችንን በትከሻችን ላይ አድርገን የምንታደመው በዐል ነው፡፡

ይላል እዮብ ከአንድ አመት በፊት ስላጋጠመው ነገር እንዲያጫውተው ኢትዮኖሚክስ በስልክ አግኝቶት፡፡ ጉዳዩ እንዲህ ነው፡፡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በአንድ በኩል የእምነታቸው መገለጫ በሌላ በኩል የአገር ፍቅር መገለጫ ነው ብለው የሚያምኑበትን እና ኮኮብ የሌለውን አረንጓዴ ቢጫ እና ቀይ ቀለም ያለውን ባንዲራ መያዝ እነደማይቻል በወቅቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኩል ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፡፡ ይህ ባንዲራ ለሁለት አስርተ አመታት ኢትዮጲያ ውስጥ ህገ ወጥ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ይህ ግብግብ ቤተክርስቲያኒቱን መለያ ባንዲራዋን እስትቀይር ድረስ ያሳሰበ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስተሩ የምስጋና ሰልፍ የተጠራ ጊዜ እኔና ጓደኞቼ ሰልፉ ላይ ነበርን፡፡ ይህንኑ ባንዲራ ይዘን ነው የሄድነው፡፡ ችግር ይመጣብናል ብለን አልገመትንም ነበር፡፡

ይላል እዮብ የዛሬ አመት የመስቀል በዐልን ለማክበር ወደ መስቀለል አደባባይ ሲሄዱ በያዙት ባንዲራ ምክኒያት ለሰዐታት በእስር ላይ መቆየታቸውን ለኢትዮኖሚክስ ሲተርክ፡፡

ግብግቡ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዐላት ላይ ብቻ የሚታይ አይደለም፡፡ በየአመቱ የኢትዮጲያውያን አዲስ አመት በገባ የመጀመሪያው ወር ማለቂያ አካባቢ የብዙ ኢትዮጲያውያን የማህበራዊ ድህረ ገጾችን በቀለማት ባጌጡ ፎቶግራፎች የሚሞላው የኢሬቻ በዐልም ከዚህ ግብግብ የዘለለ አይመስልም፡፡ ኢሬቻ የመስቀል በዐልን ተከትሎ በኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጲያውያን የሚከበር ሌላኛው ሃይማኖታዊ በዐል ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በመዲናዋ አዲስ አበባ መከበር መጀመሩ ይህ የአንድ ወገንን የበላይነት ለማምጣት ፍላጎት እንዳለው ማሳያ ነው እየተባለ የሃሳብ ግብግብ ምንጭ ሆኖ ነበር፡፡ ለነገሩ ኢሬቻ ከአብይ የስልጣን ዘመን በፊትም በዋናነት በሚከበርበት በቢሾፍቱ ከተማ ከሃይማኖት መገለጫነቱ ዘሎ መንግስትን የመቃወሚያ መድረክ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

የ2013ቱ የኢሬቻ በዐልም ከዚህም ዘሎ የተደራቢ ግብግብ ምክኒያት ሆኖ ነው ያለፈው፡፡ በዐሉ በዋንኛነት በሚከበርበት ማህበረሰብ እንዲሁም በተቀረው ኢትዮጲያዊ ዘንድ ታዋቂ የነበረው ዝነኛ ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ በመሞቱና እርሱንም ተከትሎ ከታሰሩት ፖለቲከኞች አወዛጋቢነት ጋር ተያይዞ በዐሉ ላይ ሃይማታዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ ጥላ አጥልቶበት አልፏል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ለበዐሉ መከበሪያ የሚሆን ቦታ ለአባ ገዳዎች ያስረከበበት ይህም አዲስ አበባ የኔ ናት ለሚለው የኦሮሚያ ቡድን መንግስት ያዳላል በሚል ታምቶ ያለፈበትም ነበር፡፡

ለአክባሪው ዜጋ እንግልቱ ከዚህም የዘለለ ነበር፡፡ ኢብሳ ቱሉ (ኢትዮኖሚክስ በግለሰቡ ጥያቄ ስሙን ቀይሮታል) ከኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ዋና ከተማ አሰላ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ጀምሮ ነበር፡፡ በዐሉን እንደ 2012ቱ በአዲስ አበባ ለማክበር ከአንዱ ከተማ ወደ አንዱ ከተማ ለማለፍ ከፍተኛ ችግር ገጥሞት ነበር፡፡ እንደምንም አዲስ አበባ ቢደርስ የአዲስ አበባ መግቢያ በሮች በከባድ የጸጥታ ቁጥጥር ስር ነበሩ፡፡

ከመኪናው አዲስ አበባ መግቢያ ጋር ወርጄ ከዛ በእግሬ ጀሞ ከሚባለው አካባቢ ጀምሮ እስከ ቃሊቲ ድረስ ተጉዤ ጓደኞቼ ጋር አደርኩ፡፡

ይላል ኢብሳ ኢትዮኖሚክስ በስልክ ባነጋገረው ወቅት፡፡ ከዚያም ልፋት በኋላ አልተሳካለትም፡፡ አዲሱ የማክበሪያ ቦታ በጸጥታ ሃይሎች ታጥሮ የመግቢያ ካርድ በፍጹም ማግኘት አይቻልም ነበር፡፡

በርግጥ እንደዚያ አንደሚሆን ጠርጥሬ ነበር፡፡ ግን ጓደኞቼ ካርዱን እናገኛለን ብለው ቃል ገብተውልኝ ነበር፡፡

ይላል ኢብሳ ለኢትዮኖሚክስ፡፡ የኢሬቻን እለት በከፍተኛ የጸጥታ አካላት ተወጥራ ውላ ባደረችው አዲስ አበባ ከጓደኞቹ ጋር አሳልፎ በንጋታው ጠዋት ወደመጣባት አሰላ መመለስ ግድ ሆኖበት ነበር- ለኢብሳ፡፡

የባህላዊ እና ሃይማኖታዊ በዐላት አከባበር ከፖለቲካዊ ግብግብ ቢያመልጡ እንኳን በቂ ዝግጅት ያልተደረገባቸው፤ ወይም ዝግጅታቸው ሞያዊ ብሰለት ያጠራቸው መስለው ሊያልፉም ይችላሉ፡፡ ለዚህ ማሳያ እ.ኢ.አ. በ2012 ዓ/ም ጥር ላይ በጎንደር የተከበረው የጥምቀት በዐል አንዱ ማሳያ ነው፡፡ የሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንድ ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሯን ዶ/ር ሂሩት ካሳሁን እና የአዲስ አበባ የወቅቱ ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች ቱሪስቶችን በእንግድነት ላካተተው በዐል በመድረክነት የተዘጋጀው የእንጨት እርብራብ ተደርምሶ በአሳዛኝ ሁነት ተጠናቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በቦታው ላይ የነበረው የጎንደሩ ልጅ ዳንኤል አበበ ምክኒያቱን ለኢትዮኖሚክስ እንዲህ ያስታውሳል፡-

ወቅቱ የፖለቲካ ውጥረት የነገሰበት ስለነበር በሌላ ሊተረጉሙት የነበሩ ነበሩ እንጂ ችግሩ የጥንቃቄ እና የዝግጅት ማነስ ነው፡፡ እኛ መጀመሪያ ሲደረመስ የተጎዱ ሰዎችን ለማዳን ወደቦታው ስንቀርብ ሁለተኛ ወደታች ተደረመሰ፡፡ ያኔ እኔንም አንዱ እግሬ ላይ ጉዳት ደርሶብኝ ነበር፡፡ ግን ለክፉ አልሰጠኝም፡፡

ምክኒያቱ ምንም ይሁን ምን እንደወቅቱ የሚዲያዎች ዘገባ በትንሹ ለሶስት ሰዎች ሞት እና ከደርዘን በላይ ለሚሆኑ የአካል ጉዳት ምክኒያት ሆኖ አልፏል፡፡

ኢትዮጲያ በቱሪዝም ፍሰት በአፍሪካ አገራት መካከል ያለውን ፉክክር ለማሸነፍ የሚያስችል በቂ አቅም እንዳላት በዘርፉ የተደረጉ ጥቂት ጥናቶች በአንድ ድምጽ ይስማሙበታል፡፡ ነገር ግን… በባለፉት አስርት አመታት በተደጋጋሚ የሰማነው ቃል- አልተጠቀመችበትም፡፡

የቱሪዝም ዘርፍ በኢትዮጲያ

የኢትዪጲያ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በድህረ ገጹ ያቀረበው የስታቲስቲክስ ጥራዝ እ.ኤ.አ. 2012 ዓ/ም ድረስ ብቻ ያለው መረጃ የተጠናቀረበት ነው፡፡ እንደዚህ የመረጃ ጥንቅር ከሆነ በ2009 እ.ኤ.አ. ከ427 ሺህ በላይ ቱሪስቶች አገሪቱን ሲጎበኙ ይህ ቁጥር በ2012 እ.ኤ.አ. ከ596 ሺህ በላይ አድጓል፡፡ በኔዘርላንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ድጋፍ ካርሜን አልትስ በተባለች ግለሰብ በ2018 እ.ኤ.አ. የተደረገው የቱሪዝም ዘርፍ የእሴት ሰንሰለት ጥናት ይህ የቱሪስቶች ፍሰት ጭማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጭማሪ በመኖሩ እንጂ በኢትዮጲያ ብቻ በተደረገ ጥረት አለመሆኑን ያነሳል፡፡

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አጠናቀርኩት ባለው ዶክመንት መሰረት ቱሪስቶች በቆይታቸው ወቅት በ2009 እ.ኤ.አ. ከ244 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ሲያደርጉ በ2012 እ.ኤ.አ. ይህ ገቢ ወደ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንዳደገ ያስረዳል፡፡  አሜሪካ፤ እንግሊዝ፤ ጀርመን፤ ኬንያ እና ቻይና ከፍተኛዎቹ የቱሪስት መጋቢ አገራት መሆናቸውን ያነሳል፡፡ ቱሪስቶች ኢትዮጲያን ለመጎብኘት ምክኒያት ያሏቸውን ሲዘረዝርም መዝናናት፤ ዘመድ ጥየቃ፤ ኮንፍረንስ፤ ንግድ፤ ትራንዚት እና ሌሎችም ምክኒያቶች ናቸው ይላል፡፡ ለመዝናናት የሚመጡት ቱሪስቶች የትኛውን የአገሪቷን ገጽታ ፈልገው እንደሚመጡ የሚያሳይ መረጃ አልተገኝም፡፡

ቱሪስቶች ኢትዮጲያን የሚጎበኙበት ምክኒያት በንጽጽር ትንሸ ግልጽ በሆነ ሁኔታ የተቀመጠው በኢትዮጲያ የልማት ጥናት ኢንስቲቲዩት በ2010 እ.ኤ.አ. በተዘጋጀው ጥናት ላይ ሊባል ይችላል፡፡ ጥናቱ በዘፈቀደ መርጬ አናገርኳቸው ካላቸው ከ100 በላይ ቱሪስቶች ኢትዮጲያን ለሙከራ ያክል መጥተውባት፤ ያልጠበቁትን ነገር እንዳገኙና እጅግ እንደተደሰቱ ነገረውኛል ይላል፡፡ አገሪቱ የያዘቻቸው ታሪካዊ፤ ተፈጥሯዊ፤ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊቶች እጅግ የተለዩ እንደሆኑ እና የአፍሪካን ውድድር ለምን በቀላሉ እያሸነፈች እንዳልሆነ እንዳልገባቸው ገልጸውልኛል ይላል፡፡ የፖለቲካ ውጥረት እና የጸጥታ ጉዳይ ግን ከሃሳባቸው ሳይወጣ እንደቆዩ ጥናቱ አልደበቀም፡፡

በዚህ ምልከታ የካርሜን አልትስ ጥናትም የሚስማማ ይመስላል፡፡ ጥናቱ የኢትዮጲያ ቱሪዝም ምርቶች ለዘመናት የነበሩ እና ያልተቀየሩ ናቸው ሲል ያትታል፡፡ በዋንኛነት የሚተዋወቁት የቱሪዝም ምርቶች የሰሜኑ የታሪክ ቅርስ እና በደቡብ ደግሞ ከሃዋሳና ላንጋኖ እንዲሁም ከኦሞ፤ ስምጥ ሸለቆ እና የብሄራዊ ፓርኮች ጋር የተገናኙ ናቸው ይላል፡፡ ከጊዜ በኋላ እጅግ ባነሰ ሁኔታም ቢሆን አፋርን፤ የባሌ ተራሮችን፤ ሃረርን፤ ደቡብ ምዕራብ አካባቢ ያሉ አካባቢዎችን እንደአዲስ የቱሪዝም ምርት እየተተዋወቁ ቢሆንም ጥናትን መሰረት አድርጎ ባህላዊ፤ ተፈጥሯዊ፤ ታሪካዊ፤ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ገጽታዎችን ወደጥቅም መቀየር እጅግ ክፍተት እንዳለበት ጥናቱ ይተቻል፡፡

ህዝባዊ በዐላት እና ፌስቲቫል ቱሪዝም፡ የሌሎች አገራት ልምድ

ፌስቲቫል ቱሪዝም ባህላዊ፤ ሃይማኖታዊ፤ ኪነጥበባዊ እና ሌሎችንም ህዝባዊ በዐላትን ለመታደም የሚመጡ ቱሪስቶችን ለመሳብ፤ ለማስተዳናገድ እና ከዚህም ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማግኘት ታቅዶ የሚከናወን እራሱን የቻለ የቱሪዝም ዘርፉ ምርት ነው፡፡ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፤ ሳይንስና ባህል ድርጅት በ2009 እ.ኤ.አ. የፌስቲቫል ቱሪዝምን በተመለከተ መረጃ ለመሰብሰብና ለማጥናት ይጠቅማል ብሎ ያዘጋጀው መመሪያ ደቡብ አፍሪካ እና አውስትራሊያ ጥሩ ልመድ ሊገኝባቸው የሚችሉ አገራት እንደሆኑ ያስቀምጣል፡፡ አንደዶክመንቱ ከሆነ አውስትራሊያ በየአመቱ 200 የሚሆኑ ፉስቲቫሎችን ስታዘጋጅ፤ ደቡብ አፍሪካ በበኩሏ 100 የሚሆኑ ፌስቲቫሎችን ታዘጋጃለች ይላል፡፡

ሜልቪል ሳይማን በ2011 እ.ኤ.አ. ባደረገውና ቱሪዝም ኢኮኖሚክስ ላይ ታትሞ በወጣው ጥናቱ በደቡብ አፍሪካ በምስራቃዊ ኬፕ ግዛት ስለሚዘጋጀው ግራምስተን ብሄራዊ የኪነጥበብ ፌስቲቫል ስለተባለው ኩነት ያትታል፡፡ በ2009 እ.ኤ.አ. በተዘጋጀው በዚህ ፌስቲቫል ላይ ከ39 ሚሊዮን የደቡብ አፍሪካ ራንድ ወይም ከሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቶበታል ይላል፡፡ ይህም የፌስቲቫል ተሳታፊዎች ለሆቴሎች፤ ለቲኬት፤ ለምግብና ለመጠጥ እና ለሌሎችም ያወጧቸውን ወጪዎች በመቀመር የደረስኩበት ነው ይላል ሜልቪል፡፡

ቪክቶር ላፎንቴ ሳንዜስ እና አጋሮቹ የቅዱሱ ሳምንት በሚል በብዙዎች ዘንድ በሚታወቀው ሃይማኖታዊ በዐል ላይ ያጠኑትና በ2017 በቱሪዝም ኢኮኖሚክስ ላይ ታትሞ በወጣው ጥናታቸው በዐሉ በስፔን ኢኮኖሚ ላይ ያለውን ተጽዕኖ አስቀምጠዋል፡፡ እንደአጥኚዎቹ ይህ ሃይማኖታዊ በዐል ከ82 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ገቢ የሚገኝበት ሲሆን፤ ከዚህም 82 በመቶው የሚሆነው ስፔይን ኢኮኖሚ ውስጥ የሚቀር ነው ይላሉ፡፡

የተለያዩ ድህረገጾች የሃጅ እና ዑምራህ ጉዞ ለሳውዲ አረቢያ በየአመቱ ይዞ የሚመጣው በረከት ሰማያዊም ምድራዊም ነው ይላሉ፡፡ እነደ ብዙ ማጣቀሻዎች ከሆነ ሃጅ እና ኡምራህ በ2022 እ.ኤ.አ. ጉዞው ለሳውዲ በዐሉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ባሉት ጥቂት ቀናት ብቻ ከ150 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስገባ እና ከ100 ሺህ በላይ ስራ ለዜጎች ይፈጥራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሳውዲ ቻምበርስ ምክርቤትን በመጥቀስ ያሳያሉ፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መስራቤት እንደአዲስ በከለሰው ድህረ ገጹ ገና፣ ኢሬቻ፣ ጥምቀት፤ ፋሲካ፤ ኢድ አልፈጥር፤ ሼክ ሁሴን፤ ሙሃራም፤ የቡና ሴሪሞኒ እንደማይዳሰሱ ቅርሶች ተብለው ይዘረዝራል፡፡ ዝርዝሩ የጨምበላላ የዘመን መለወጫን፤ መስቀልን እና ሌሎች በኢትዮጲያውያን ብቻ የሚከበሩ በዐላትን እንደቱሪዝም ምርት ለማስተዋወቅ ስለተደረገ ጥረት መረጃ ለማግኘት ኢትዮኖሚክስ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በ2012 እ.ኢ.አ. በተከበረው የኢሬቻ በዐል ዋዜማ የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የተረዳ የሚመስል ንግግር አድርገው ነበር፡፡ በዚህ ንግግራቸው አዲስ አበቤው በዐሉ ሊያመጣ የሚችለውን የንግድ ትስስር ጥቅም በማሰብ በየኔነት ስሜት እንዲቀበሉት አሳስበው ነበር፡፡ ግንዛቤው ባልከፋ፤ የንግድ ጥቅሙ ከተሰላ ግን ጥቅሙ ተጨማሪ የንግድ ገቢ ከሚያስፈልጋት ከቢሾፍቱ ነጥቆ በኢንቨስትመንት ለተጥለቀለቀችው አዲስ አበባ መጨመር የውሳኔው መሰረት ኢኮኖሚያዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ ነበር ቢባል ከስህተት ብዙ የሚርቅ አይመስልም፡፡

የኢሬቻ አከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ

ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ የህዝብ በዐላትን ለይቶ እንደቱሪዝም ምርት መጠቀም፤ ሁሉም የሁላችንም ነው የሚለው አስተሳሰብ ግፋ ቢል በስራ አስፈጻሚ አካላት ዘንድ እንዲኖር ማድረግ፤ ጥቅሙንም ለሁሉም የአገር ልጆች ለማካፈል መሞከር ጊዜ የማይሰጠው ስራ ይመስላል፡፡ ሁሉንም አዲስ አበባ ከማከማቸት ይልቅ የጥምቀቱን ወደ ጎንደር፤ የመስቀሉን ወደላሊበላ፤ ኢሬቻውን ወደ ቢሸፍቱ፤ የእስልምና በዐላቱን ወደ አልነጃሺ ወይ ወደ ሃረር ገፍቶ ጥቅሙን ማዳረስ የግንዛቤውን ምልዑነት ባሳየ እና አገር ውስጥ ቱሪዝምንም ባበረታታ ነበር፡፡

በሃይማኖት በዐላት ወቅት ግብግብ ካሁን በኋላም ላለመቀጠሉ ማስተማመኛ ያለ አይመስልም፡፡ በቅርቡ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለምታከብረው የጥምቀት በዐል ለረጅም ጊዜ የማክበሪያ ቦታ ሆኖ የቆየው የጃንሜዳ ቦታ የግብግብ ምክኒያት ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ የኮሮና መግባትን ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ የተጨናነቁ ቦታዎችን ማቃለል በሚል የተለያዩ እርምጃዎችን ወስዶ እንደነበር ይታወቃል፡፡

የማስተካከያ እርምጃዎቹ ከነካቸው የመገበያያ ቦታዎች አንዱ ፒያሳ የሚገኘው የአትክልት ተራ አንዱ ነው፡፡ በቀድሞው የከተማዋ ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ የተተገበረው የፒያሳን አትክልት ተራ ወደ ጃንሜዳ የመውሰድ ሃሳብ፤ ጃንሜዳን በአትክልት ምርቶች ከማበላሸት በዘለለ፤ በጠንካራ እቅድ ባለመተግበሩ ምክኒያት ለታለመለት አላማ ሳይውል እንዲያውም እንደመስቀል አደባባዩ ፕሮጀክት መንግስት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን የባዕላት ማክበሪያ ቦታ የመንጠቅ ጥረት ነው በሚል ሃሜት ሳይለየው ሰንበቷል፡፡ የጥምቀት በዐል እየቀረበ ሲመጣም፤ ድምጻችን ለጃንሜዳ የሚል የማህበራዊ ድህረገጾች ንቅናቄ መጀመሩ የግብግቡ መጀመሪያ ፊሽካ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡
እዮብ፤ ኢብሳና ዳንኤል ግን ለሰማዩ ያላቸው ክብር የምድርም ምቾት እስኪያዘንብላቸው፤ ደህንነታቸው ተጠብቆ በዐላቱን ማክበር እንዲችሉ ማድረግ በአሁን ዘመን ሊያሳስብ አይገባም፡፡ በዐላቱ ስራ ባይፈጥሩላቸው እንኳን በያዙት ባንዲራ አለመታሰርን አሊያም በፖለቲከኞች ግብግብ ባዕላቱን ከማክበር አለመሰናከልን መጠየቅ መንግስት ሊመልሰው የሚገባ የዘመኑ ትንሹ ጥያቄ ነው የሚል አስተሳሰብ በስራ አስፈጻሚው ዘንድ መገንባትን ያሻል፡፡ ማክበር በቻሉት ላይ ደግሞ መድረክ ተደርምሶ እሞት ይሆን እንዴ ከሚል ስጋት ዜጋን መታደግ ብዙ የተወሳሰበ አስተዳደር የማይጠይቅ ነው፡፡

በመስቀል ስንት ሰው ታሰረ፤ በኢሬቻ ስንት ሰው ታደገ፤ በጥምቀት ስንት ሰው እግሩ ተሰበረ ከሚል ወጥቶ በእያንዳንዱ በዐል ምን ያክል የውጪ ምንዛሬ ተገኘ፤ ምንስ ያክል ስራ ተፈጠረ፤ እና የመጡትስ ቱሪስቶች ምን አሉ ወደሚል አስተሳሰብ መሻገር የግድ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ይህኛው የናንተ አይደለም፤ ያኛው የኛ አይደለም የሚለው አስተሳሰብ ግፋ ቢል ከመንግስት ስራ አስፈጻመሚዎች ርቆ፤ ሁሉም የሁላችንም ነው ወደሚል መሻገርን ይጠይቃል፡፡ ከዚህ ዘለል ሲልም ህዝባዊ ሃይማኖታዊ በዐላትን እንደ አንድ የቱሪዝም ምርት ማዕቀፍ ማስተዋወቅ፤ ለዚያም የሚጠይቀውን ኢንቨስትመንት እና የክህሎት ግንባታ ማድረግ ዘመኑ የሚጠይቀው አስተሳሰብ ይሆናል፡፡

 

- Advertisement -

1 COMMENT

  1. What i do not understood is actually how you are not actually much more well-liked than you might be now. You’re very intelligent. You realize therefore significantly relating to this subject, made me personally consider it from numerous varied angles. Its like women and men aren’t fascinated unless it’s one thing to do with Lady gaga! Your own stuffs excellent. Always maintain it up!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -