Saturday, January 22, 2022

ሊባኖስ ላይ የተጋረጠው አደጋና የኢትዮጵያውያን ዕጣ ፈንታ

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

ከሁለት ቀናት በፊት በምስራቃዊ ሜድትራንያን ባህር ዳርቻ በምትገኘው የሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት የተከሰተው ፍንዳታ ከተማዋን ከማናወጥም አልፎ ድምፁ እስከ 240 ኪሎሜትር በመጓዝ በቆጵሮስ ደሴት ነዋሪዎች ላይ ድንጋጤን ፈጥሮ ነበር። ከ6 ዓመታት በፊት በፀጥታ አካላት ተወረሰ የተባለ ከ2,750 ቶን በላይ የሚመዝን አሞንየም ናይትሬት በከተማዋ የባህር ወደብ ተከማችቶ የቆየ ሲሆን ይህ ለቦምብ መስርያ የሚያገለግል ውህድ ኬሚካል በአቅራብያው ከተነሳ እሳት ጋር በመነካካቱ ግዙፍ ፍንዳታን ሳያስከትል እንዳልቀረ የሊባኖስ ባለስልጣናት ግምታቸውን እየሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡

በፍንዳታው በትንሹ 157 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከ5ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው እስካሁን ያሉ መረጃዎች የሚያሳዩ ቢሆንም አካባቢው ገና በአግባቡ ያልታሰሰ በመሆኑ የሟቾችም ሆነ የቁስለኞች ቁጥር መጨመሩ የማይቀር ነው፡፡

የተሻለ የስራ እድል ለማግኘት ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለሚሰደዱ በርካታ ኢትዮጵያውያን መዳረሻ ከሆኑት አገራት አንዷ ሊባኖስ ነች። ሆኖም ባለፉት 6 ወራት ባጋጠማት የኢኮኖሚ ውድቀትና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በግለሰብ ቤቶችና በንግድ ቦታዎች ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ ቁጥራቸው አነስተኛ የማይባል ኢትዮጵያውያን ከስራ በመፈናቀላቸው በቤሩት የቆንስላ ግቢ ተጠልለው የድረሱልን ጥሪ ሲያሰሙ በማህበራዊ ድህረ ገፆች ሲታዩ ቆይተዋል፡፡

የሰሞኑን ፍንዳታም የጋራ መኖርያ ሕንፃዎች ባሉበት አቅራብያ በመከሰቱ ምናልባት በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ላይ ጉዳት አድርሶ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ፡፡ ይህንን ተከትሎም ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በአካባቢው ላሉ ኢትዮጵያውያን በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ከኢትዮጵያ ቆንስላ ጋር ለመገናኘት እንዲሞክሩ አስታውቀዋል፡፡ ቆንስላውም በበኩሉ በፌስቡክ ገፁ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያውያን አደጋው ከተከሰተበት አካባቢ እንዲርቁና ከተቻለም ከቤት እንዳይወጡ አሳስቧል፡፡

በቤሩት የተከሰተው ፍንዳታ ለኢትዮጵያ መንግስት የማንቅያ ደወል ሊሆን የሚገባው ነው፡፡ ቀድሞውኑም በሃይማኖት በተከፋፈለ ሕዝብና አይን ለአይን በማይተያዩ ፖለቲከኞች ምክንያት ወደ እርስ በርስ ጦርነት ለመግባት ጫፍ ላይ ተንጠልጥላ ለዓመታት የኖረችው ሊባኖስ ፤ ዛሬ የገባችበት የኢኮኖሚ አዘቅትና መስፋፋቱን የቀጠለው የኮሮና ወረርሽኝ ሲጨመርባት ወደ አስከፊ የእርስ በርስ ጦርነት የመግባት እድሏ እየሰፋ መጥቷል፡፡ ገና ካሁኑም እንኳን በተደጋጋሚ መብታቸው ሲጣስ ለኖሩት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ይቅርና ለአገሪቱ ዜጎችም ሊባኖስ አደገኛ እየሆነች መጥታለች፡፡

ፍንዳታው የተከሰተበት ለሊባኖስ ዋነኛ የሜድትራንያን ባህር በር ሆኖ የሚያገለግለው ወደብ አገሪቱ ከውጭ ለምታስገባቸው በርካታ ምርቶች መሸጋገርያ ነው፡፡ የሊባኖስ ኢኮኖሚ የአመታዊ አጠቃላይ ምርት ሲተመን 53 ቢልዮን ዶላር ሲሆን ኢትዮጵያ ካላት የ91 ቢልዮን ዶላር ኢኮኖሚ ያነሰ ነው፡፡ ይሁን እንጂ 7 ሚልዮን የማይሞላ የህዝብ ብዛት ያላት ሊባኖስ አጠቃላይ ኢኮኖሚዋ በሕዝብ ብዛቷ ተካፍሎ የዜጎቿ የነፍስ ወከፍ ምርት አቅም ሲታይ አገሪቷን በዓለም ላይ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ እንድትመደብ ያደርጋታል፡፡

ሆኖም አብዛኛው የአገር ውስጥ የእህል ፍጆታ፣ ሸቀጣሸቀጥ፣ መድሃኒት፣ ነዳጅና እንደ መኪና ያሉ ተሽከርካሪዎች በአብዛኛው ከውጭ በዶላር ተገዝተው የሚገቡ በመሆናቸው በየዓመቱ እስከ 11 ቢልዮን ዶላር የሚገመት ዋጋ ያለው የውጭ ምርት ወደ አገር ውስጥ ታስገባለች። በአንፃሩ ወደ ውጭ ከሚላከው ምርት የሚገኘው ገቢ ከ3 ቢልዮን ዶላር በታች ነው፡፡ ይህ የገቢና ወጪ አለመመጣጠን የሚያስከትለውን የዶላር እጥረት ለማካካስ ሊባኖስ ላለፉት 30 አመታት ያልተለመደ ዘዴን ስትከተል ኖራለች፡፡

መንግስት ከአገሪቱ ብሔራዊ ባንክ ጋር በመተባበር አገር ለማስተዳደርና ለውጭ ግዢዎች የሚያስፈልገውን ዶላር ለማሟላት ከአገር ውስጥ የግል ባንኮች ዶላር ሲበደር ቆይቷል፡፡ እነዚህ የግል ባንኮች ታድያ ለብሔራዊ ባንኩ ዶላር እንዲያበድሩ የሚያበረታታ ዘዴ ሊኖር አስፈላጊ ስለነበር በየትም ዓለም የማይገኝ ከፍተኛ የወለድ መጠን ብሔራዊ ባንኩ በማቅረቡ አብዛኛዎቹ የግል ባንኮች ለነጋዴዎችና ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ማበደርን ትተው የሰበሰቡትን ዶላር ባጠቃላይ ለብሔራዊ ባንክ ሲያስረክቡ ሌላ ጊዜ ደግሞ በቀጥታ ለመንግስት ሲያበድሩ ቆይተዋል።

ይህ ከወለድ የሚገኝ ከፍተኛ ትርፍ የጣማቸው የግል ባንኮች በበኩላቸው የዳያስፖራ አባላትና የሌሎች የአረብ አገራት ባለሃብቶች ያላቸውን ዶላር ወደ ቤሩት አምጥተው እንዲይስቀምጡ ለመሳብ ዳጎስ ያለ የተቀማጭ ገንዘብ ወለድ ሲከፍሉ ነበር፡፡ ባንኮቹ ለባለሃብቱ የሚከፍሉት የተቀማጭ ወለድ ዶላሩን መልሰው ለብሔራዊ ባንክና ለሊባኖስ መንግስት ሲያበድሩ ከሚያገኙት ወለድ ያነሰ በመሆኑ ብዙም ሳይለፉ እጅግ ትርፋማ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡

ይህ አሰራር በተወሰነ መልኩ ብልህነት ቢመስልም ብሔራዊ ባንክና የአገሪቱ መንግስት ከግል ባንኮች ሲበደሩ የሚከፍሉት ከፍተኛ መጠን ያለው ወለድ አሰራሩን ምን ያህል ያዘልቀዋል የሚሉ ጥያቄዎች መነሳት የጀመሩት ከ9 ዓመት በፊት ነበር፡፡ ከጅምሩ የሊባኖስ አካሄድ ኢኮኖሚዋ በአግባቡ እንዳያድግ አንቆ የሚይዝ ነበር፡፡ ባንኮች የሚሰበስቡትን ዶላር ሁሉንም ማለት ይቻላል ለመንግስትና ብሔራዊ ባንክ አሳልፈው ማበደራቸው በአገር ውስጥ ያሉ ፋብሪካዎችና ሌሎች በልማታዊ ዘርፎች የተሰማሩ አካላት በቂ ብድር እንዳያገኙ ተፅእኖ ሲያሳድር የአገር ውስጥ ምርት እንዲመናመንና ሊባኖስ ከውጭ በሚመጣ ምርት ላይ ጥገኛ እንድትሆን አድርጎ በተጨምሪም ስራ አጥነት እንዲስፋፋ አድርጓል፡፡ ሕዝቡ መንግስት በብድር በሚያስገባው የውጭ ምርት የሃብታምነት ስሜት ተሰምቶት ጠንክሮ ሳይሰራ የቤት ሰራተኞችን ሳይቀር ከኢትዮጵያና ሌሎች ድሃ አገራት እያስመጣ በአሸዋ ላይ የተሰራ ቤት አይነት ኑሮ እንዲኖርም ዳርጎት ነበር፡፡

መንጋቱ አይቀርምና ሊባኖስ ስትኖር ከነበረችው ህልም መንቃት የጀመረችው ከ4 ዓመት በፊት ሳውዲ አረብያ ውስጥ የተከሰተ አንድ ሁኔታን ተከትሎ ነበር፡፡ በወቅቱ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ሳአድ ሃሪሪ ወደ ሳውዲ በተጓዙበት ወቅት ከልኡል መሃመድ ቢን ሳልማን ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት በሳውዲ ቴሌቭዥን ቀርበው ከስልጣን እንደሚወርዱ አስታውቀው ከሊባኖሳውያንም አልፎ ዓለምን ግራ አጋቡ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በቴሌቭዥን ቀርበው ድንገተኛ ውሳኔያቸውን ካሳወቁ በኋላ ለ10 ቀናት ያክል ያሉበት ሳይታወቅ ድምፃቸው መጥፋቱ በሳውዲ መንግስት እንደታገቱና ከስልጣን እንዲለቁም ተገደው የቴሌቭዥን መግለጫ እንዲሰጡ እንደተደረጉ የተለያዩ ግምቶች ተሰነዘሩ፡፡ የጠቅላይ ሚንስትር ሃሪሪ በሳውዲ መጥፋት ያሳሰባቸው የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ታድያ በይፋ ጠቅላይ ሚንስትሩን ለጉብኝት የጋበዟቸው ሲሆን ጉዳዩ ከአቅሟ በላይ የሆነባት ሳውዲም የቁም እስረኛ አድርጋቸው የነበሩትን የክብር እንግዳዋን እንድትለቃቸው ተገደደች።

ይህ ክስተት በርካታ ባለሃብቶችን ከተኙበት ያነቃ ነበር፡፡ ሶስት የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች ለበላይነት የሚፎካከሩባት ሊባኖስ የውስጥ ፖለቲካ ትኩሳቷ በአካባቢዋ ካሉ ግጭቶች ጋር ተደምሮ መረጋጋት እንዳይኖር አርጓት ቆይቷል፡፡ 35 ፐርሰንት አካባቢ የሚሆነው ሕዝብ የክርስትና እምነት ተከታይ ሲሆን እስከ 60 ፐርሰንት የሚጠጋው ደግሞ እስልምናን ይከተላል፡፡ በሺኣና በሱኒ ለሁለት የተከፈለው ሙስሊሙ ሕብረተሰብ ደግሞ በአንድ በኩል በኢራን የሚደገፍና በሌላ በኩል ደግሞ ከሳውዲ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው መሆኑ በሁለቱ መካከል አለመተማመንን ሲፈጥር አብዛኛው የሊባኖስ ፖለቲካ በሶስቱ የተለያዩ እምነት ተከታዮች መካከል በሚደረግ የስልጣን ፉክክር የተጠመደ ነው፡፡

ሄዝቦላ በመባል የሚታወቀው በኢራን የሚደገፍ የሺኣ ቡድን ሊባኖስ ውስጥ እየተጠናከረ መምጣት ያሰጋት ሳውዲ አረብያ ወዳጇ የነበሩትን የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ሃሪሪን ለ10 ቀናት አግታ ከስልጣን እንዲወርዱ ማስገደዷ ዶላራቸውን በቤሩት ባንኮች ላስቀመጡ በርካታ የውጭና የአገር ውስጥ ባለሃብቶች ዘንግተውት የነበረውን በሊባኖስ ላይ የተዳቀነ አደጋ ቆም ብለው እንዲያስቡ አርጓቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ሃሪሪ ከሳውዲ ከተለቀቁ በኋላ ወደስልጣን ቢመለሱም ቀጥሎ የመጣውን ችግር ሊያቆሙት አልቻሉም ነበር፡፡

ወድያውኑም ጥቂት የማይባሉ ባለሃብቶች ቀስ በቀስ ዶላራቸውን ከአገር ማሸሽ ሲጀምሩ ባንኮች እንደቀድሞው ለብሔራዊ ባንክና ለመንግስት የሚያበድሩትን ገንዘብ እንዲቅነሱ አስገደደ፡፡ ይህ ሁኔታ ለ2 ዓመታት ከቀጠለ በኋላ ከዕለት ወደለት ከግል ባንኮች የሚያገኘው ዶላር እየደረቀበት የመጣው መንግስትም ቀድሞ በተበደረው ላይ መክፈል የሚገባውን ከፍ ያለ ወለድ መክፈል ይችላል ወይ የሚሉ ጥያቄዎች ከ1ዓመት በፊት መነሳት ጀመሩ፡፡ የሊባኖስ መንግስት ያጋጠመውን የዶላር እጥረትና ተያይዞ የመጣውን አጠቃላይ የገቢ መቀነስ ለመቋቋም በሲጋራና እንደ ዋትስአፕ በሚባለው ስልክ ላይ የሚጫን ቴክኖኮጂ ላይ ግብር ሲጥል በሕዝቡ ዘንድ ቁጣን ቀሰቀሰ፡፡

ይባስ ብሎም የኢኮኖሚው መዋዠቅ እየተባባሰ በመጣበት ሰዓት የኮሮና ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ የተቀሩት የአገር ውስጥ ባለሃብቶችና ዳያስፖራው ገንዘባቸውን ከባንኮች ለማውጣት እሽቅድድም ጀመሩ። እንደዚህ በቀላሉ ነው ለ30 ዓመታት የቆየው የኢኮኖሚ መዋቅር ከስሩ መናድ የጀመረው፡፡ መንግስት እንደልቡ ዶልር ማግኘት አለመቻሉ የቀድሞ ብድሩን መልሶ ለመክፈል ከመቸገርም አልፎ ሊባኖስ የሚያስፈልጋትን የውጭ ምርት እንደ ከዚህ ቀደሙ ለአገር ውስጥ ፍጆታ ማቅረብ ተሳነው፡፡ የምግብና የአብዛኛዎቹ ሸቀጣ ሸቀጦች ዋጋ በፍጥነት ጨመረ፡፡ ቀጥሎም የግል ባንኮች ተጠቃሚዎች ያስቀመጡትን ዶላር እንደፈለጉ እንዳያወጡ እገዳ ማድረጋቸው ሕዝቡ በባንኮች ላይ እምነት እንዲያጣና በየመንገዱና በሱቆች ውስጥ የጥቁር ገበያ እንዲስፋፋ እድልን ፈጠረ፡፡

ዛሬ በሊባኖስ የሚታየው የሕዝብ ቁጣና በየመንገዱ እየተካሄዱ ያሉት ተቃውሞዎች ከ9 ዓመታት በፊት በተለያዩ አረብ አገራት ተቀጣጥሎ የነበረውና በግብፅና ቱኒዝያ የመንግስት ለውጥን ያስከተለው፤ በሊብያ፣ ሶርያና የመን ደግሞ እስካሁን ላልቆሙ የእርስ በርስ ጦርነቶች መነሻ የሆነው አርብ ስፕሪንግ ተብሎ የሚጠራው አብዮት አጀማመር ሰሞን የነበረውን ድባብ ያስታውሳል፡፡

በተለይም ከአገሪቱ መከላከያ ሃይል በላይ የተጠናከረ ሃይል ያለው የሄዝቦላ ቡድን በሺኣ የእስልምና ተከታዩ ሕብረተሰብ ዘንድ እንደ የነፃነት ታጋይ ሲታይ የኖረና ከክርስትያን ሊባኖሳውያን ጋርም ወዳጅነት ያለው ሲሆን የሺኣ እምነት ዋና ማዕከል ከሆነችው ኢራን ጋርም ጥብቅ የሆነ ግንኙነት አለው፡፡ በኢራን ትጥቅና የገንዘብ እርዳታ ጡንቻውን አፈርጥሞ እስከ ሶርያ ድረስ ሃይል በመላክ ለፕሬዝዳንት አሳድ ሲያግዝ የቆየው ሄዝቦላ በሊባኖስ ፖለቲካ ከአገሪቱ ፓርላማ እስከ የባህር ወደብ አስተዳድር ውስጥና ብሎም በንግዱ ዘርፍ ውስጥ ሰርጎ የገባ ነው፡፡ ይህ በኢራን ድጋፍ የመጣ የሄዝቦላ መጠናከር  አሜሪካንን፣ እስራኤልንና ሳውዲ አረብያን እጅጉን እያሳሳበ ይገኛል፡፡ በተለይም በሊባኖስና እስራኤል ድንበር አቅራብያ ላይ ሄዝቦላ በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን በእስራኤል ከተሞች ላይ አነጣጥሮ እንደሚጠባበቅ ይነገራል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሶስተኛ የሚሆነው የሱኒ እስልምና ተከታይ ሕብረተሰብ ከሳውዲ ጋር ባለው ወዳጅነት ምክንያት የገንዘብና የፖለቲካ ድጋፍ ከሪያድ እስከ ዋሺንግተን ዲሲ ድረስ የሚደረግለት ነው፡፡ በሊባኖስ ኢኮኖሚ መድቀቅ ምክንያት ለስራ አጥነት የተዳረገው ሕብረተሰብም ለጊዜው ቁጣውን በሰልፍና ድንጋይ ከመወርወር ባልዘለለ ንዴቱን እያሳየ ቢሆንም በቅርቡ ለችግሩ መፍትሄ ካልተገኘለት ሁሉም በየ እምነቱ በመደራጀት ትጥቅን አንስቶ ወደባሰ የእርስ በርስ ግጭት ማምራቱ የማይቀር ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር እስከ 1983 ድረስ ሊባኖስ ለ15 ዓመታት የዘለቀ የእርስ በርስ ጦርነት እንዳስተናገደች የሚታወስ ነው፡፡ ከዛ በኋላም እስራኤልና ሄዝቦላ ጦርነት ያካሄዱ ሲሆን ሁለቱንም ለኪሳራ ዳርጓቸው ነበር፡፡  

የሊባኖስ ቁልፍ መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ታድያ በአገሪቱ የሚከሰትን ማንኛውም አይነት ግጭት ልክ እንደ ሶርያ አካባቢያዊ መልክ እንዲይዝና የሚያደርግ ሲሆን እስራኤል፣ ኢራንና ሳውዲ የሚፋለሙበት የጦር ሜዳ ሊሆን የሚችልበት እድሉ የሰፋ ይሆናል፡፡ ሊባኖስ በሺዎች ለሚቆጠሩ በሕጋዊም ሆነ በሕገወጥ ለሄዱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መኖርያ መሆኗ ደግሞ ጉዳዩን ለኢትዮጵያ በቀጥታ የሚመለከት ያደርገዋል፡፡

የመካከለኛዋ ምስራቅ ፓሪስ ተብላ በምትታወቀውና ውብ የሆኑ ዘመናዊ ህንፃዎችን ባፈራችው ቤሩት ዛሬ የአንድ ዶላር ዋጋ በጥቁር ገበያ ከ1 ዓመት በፊት ከነበረበት በ80 ፐርሰንት መጨመሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለአመታት ያጠራቀሙትን ገንዘብ ወደ ዶላር ቀይረው አገራቸው ለመመለስ ቢሞክሩ እንኳን የገንዘባቸውን ዋጋ የሚያሳጣ ነው፡፡ ባንኮች በአብዛኛው ዶላር መሸጥ ማቆማቸው ደግሞ በእጅ ያለን ገንዘብ በተሻለ የባንክ ዝርዝር ዋጋ ለመቀየር የማይቻል ያደርገዋል፡፡

በሌላ በኩል አብዛኛዎቹ መካከለኛ ገቢ የነበራቸው አሰሪዎች ለኢትዮጵያውያን ሰራተኞቻቸው የሚከፍሉት ገንዘብ በማጣታቸው በቤሩት ባለው ቆንስላ ኢትዮጵያውያኑን በመኪና አምጥተው እየተዋቸው መሄድ ከጀመሩ ወራት አልፏቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከስራ በመውጣታቸው ማደርያ አጥተው በከተማዋ የሚንከራተቱ ኢትዮጵያውያን በርካታ ናቸው። የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ መፍትሄ ካልፈለገ በሊባኖስ ያለው አስጊ ሁኔታ ወደተባባሰ ደረጃ ቢደርስ ኢትዮጵያውያኑን ከዚህ አደጋ ለማውጣት የሚኖርው እድል እየጠበበ የሚሄድ ይሆናል፡፡

ኢትዮኖሚስ

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -