ስለ ኢትዮኖሚክስ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ2013 ዓ.ም በኒውዮርክ ከተማ የተቋቋመው ኢትዮኖሚክስ በተለያዩ ዘርፎች በቂ ትምህርትና ልምድን ባዳበሩ ባለሙያዎች የተፃፉ ጥልቅ ትንታኔዎች ለአንባቢዎች የሚቀርቡበት መድረክ ነው። ከአገር ውጪ ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ስለአገራቸው ወቅታዊ ሁኔታ መረጃዎችን እንዲያገኙ እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚኖሩ አንባቢዎች ስለ ዓለማችን ወቅታዊ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚተጋው ኢትዮኖሚክስ ለንግድ፣ ኢኮኖሚና፣ መልከዐ ምድራዊ ፖለቲካ ነክ ጉዳዮች ልዩ ትኩረትን ይሰጣል። የኢትዮኖሚክስ ፀሃፊዎች በአሜሪካ ኒውዮርክና ሚንያፖሊስ ብሎም በአውሮፓና በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች መቀመጫቸውን ያደረጉ በመሆናቸው ነገሮችን ከተለያዩ መአዘኖች የመመልከት እድል አላቸው።