Saturday, January 22, 2022

በህንድ ውቅያኖስ የሱማልያን የአሳ ሃብት የሚበዘብዙት ህገወጥ የውጭ ነጋዴዎች

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

ካፕቴን ፊሊፕስ በመባል የሚታወቀውና ከ7 ዓመታት በፊት ለእይታ የበቃው ታዋቂ የሆሊውድ ፊልም በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ፊልሙ የሚያጠነጥነው በአንድ አሜሪካዊ የመርከብ ካፕቴን ላይ ሲሆን በርካታ ኮንቴነሮችን የጫነች አንድ ግዙፍ መርከብን እየነዳ የነዳጅ ሃብታም ከሆነችው አረብ አገር ኦማን ከተነሳ በኋላ የህንድ ውቅያኖስን አቋርጦ ወደ የኬንያው ሞምባሳ ወደብ በሚያቀናበት ሰዓት ድንገት ከሱማሌ የባህር ላይ ሽፍቶች ጋር ይገጣጠማል፡፡ ካፒቴኑና የመርከቧ ሰራተኞች ከሽፍቶቹ ለማምለጥ የመርከቧን ፍጥነት ጨምረው ለማምለጥ ቢሞክሩም ከክላሽንኮፍ እስከ ባዙቃ ታጥቀው በፈጣንና ትናንሽ ጀልባዎች የህንድ ውቅያኖስ ላይ እንዳሻቸው ሲፈነጩ ከሚውሉት የሱማሌ ወጣቶች ግን ማምለጥ አልቻለም፡፡ ሽፍቶቹ መርከቧን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠሩ በኋላም ካፒቴኑንና እረዳቶቹን በማገት በሚልዮኖች የሚቆጠር ዶላር ከመርከቧ ባለቤቶች እንዲላክላቸው አለበለዝያም ሰራተኞቹን እንደሚገሉ ያስጠነቅቃሉ፡፡

የዚህ ፊልም መነሻ የሆነው እውነተኛ ታሪክ የተፈፀመው የዛሬ አስራ አንድ ዓመት ሲሆን በወቅቱ የሱማሌ የባህር ላይ ሽፍቶች የህንድ ውቅያኖስን ያሸበሩበትና ከመቶ በላይ የሚሆኑ መርከቦችን በማገት በሚልዮኖች የሚቆጠር ዶላር ያፈሱበት ጊዜ ነበር፡፡ ይባስ ብሎም እነዚህ ሽፍቶች በትናንሽ ጀልባዎቻቸው ላይ ከነጦር መሳርያቸው ማዕበልን ተጋፍጠው የውሃ ጥማትና ረሃብ ሳይበግራቸው ውቅያኖሱን በማቋረጥ በደቡብ እስከ 4ሺ ኪሎሜትር ርቀው ወደ ታንዛንያና ብሎም እስከ ማዳጋስካር በምስራቅ ደግሞ እስከ ኦማን በመጓዝ መርከቦች ላይ ጥቃት ማድረግ ጀምረው ነበር፡፡ በዚህ አደገኛ የውቅያኖስ ጉዞ ላይም ጀልባቸው ሰጥሞባቸው፣ ማዕበል ውጧቸው፣ ረሃብና ጥማት አሸንፏቸው የሞቱ የሱማሌ ወጣቶች በርካታ ናቸው፡፡ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በነዚህ ሽፍቶች ስለተፈፀመ እገታ በየለቱ ከመዘገብም አልፎ የሃያላን አገራት መንግስታትን ጭንቀት ውስጥ ከቶም ነበር፡፡ የዓለማችን ከ12 ፐርሰንት በላይ የሚሆነው የመርከብ ጭነት በዚህ አካባቢ የሚያልፍ ሲሆን በተለይም ከአረብ ሃገራት ተነስቶ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ለሚጓጓዘው ነዳጅ ዋነኛ መተላለፊያው ነው፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የመከረው የተባበሩት መንግስታት የፀጥታ ምክርቤት በህንድ ውቅያኖስ ላይ በተለይም በሱማልያ ግዛት አቅራብያ ሃያላን አገራት የጦር መርከብ እንዲያሰፍሩ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ ሩስያና ሌሎች በርካታ አገራት ከባባድ መሳርያዎችን የጫኑ የጦር መርከቦችን በአካባቢው አስፍረዋል፡፡ የሃያላኑ ጦራቸውን ማስፈር ከሽፍቶቹም አልፎ ወደ ሌላ ተፅዕኖ የማሳደር ፉክክርም የደረሰ ይመስላል፡፡ ከዚህ አልፎም እንደ ቻይና ያሉ አገራት የአሳ አጥማጅ መርከቦቻቸውን በባህር ጦራቸው አጅበው ወደ ሱማልያ ግዛት መላካቸው ወደ አካባቢው የመጡት የእውነት ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ሳይሆን ብሔራዊ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ እንደሆነ ያሳያል፡፡

ሱማልያ እንደዛሬ የእርስ በርስ ጦርነት ባያደቃትና ስርዐት አልበኝነት ባይነግስባት ኖሮ ድንበሮቿን የሚያስከብር፣ ብሔራዊ ጥቅሞቿን የሚያስጠብቅና ወጣቶች ከስራ አጥነት ወደ ወንጀል እንዳይሸጋገሩ የሚከላከል መንግስት ይኖራት ነበር፡፡ ዛሬ በአሜሪካና የፈረንሳይ ወታደሮች ከህንድ ውቅያኖስ ላይ ተይዘው በኒውዮርክና በአውሮፓ እስር ቤቶች የሚማቅቁት የሱማሌ ወጣቶች ወደ ሽፍታነት ሳይቀየሩ በፊት በአሳ ማጥመድ የሚተዳደሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ነበሩ፡፡ የህንድ ውቅያኖስ ላይ ሽብርን ለቀው የነበሩት እነዚህ ወጣቶች ከ15 እስከ 30 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙና አማራጭ በማጣት ወደ ወንጀል የገቡ መሆናቸውን ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡

መንግስት በሌላት ሱማልያ ከአውሮፓና ከእስያ አገራት ግዙፍ የአሳ አጥማጅ መርከቦችን ይዘው በመምጣት በተደራጀ መልኩ በውቅያኖሱ ላይ አሳ ሲያጠምዱ ተቆጣጣሪ እንደማይኖራቸው የሚያውቁት የባዕድ አገር ነጋዴዎች የአካባቢውን የአሳ ሃብት እያራቆቱት ሲሄዱ በአነስተኛ ጀልባዎች አሳ አጥምደው የእለት ኑሮዋቸውን በሚገፉት የሱማሌ ወጣቶች ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖን አሳድሯል፡፡ ሱማልያ እንደ አልሻባብ ባሉ ቡድኖች እየታመሰች ሰርቶ ማደር በማይታሰብበት አገር አሳ ማጥመድ ብቸኛ አማራጭ የሆነባቸው ወጣቶች የተፈጥሮ ፀጋችን የሚሉት የባህር ላይ ሃብት ሲመናመን ባዩበት ጊዜ ወደ ግዛታቸው የሚመጡትን ህገወጥ መርከቦች ወደ ማገት እንዲገቡ አስገድዷቸዋል፡፡

መርከቦች በባህር ላይ ሲንቀሳቀሱ የሚገቡት ኢንሹራንስ የሰው ህይወት ከጠፋ ወይም መርከቦች ከጥቅም ውጪ ከሆኑ ሊከፍሉ የሚችሉትን ካሳ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለአጋቾቹ በርካታ ሚልዮኖችን መክፈል ኢንሹራንሶቹ እንደተሻለ አማራጭ መውሰዳቸውን የተመለከቱት የሱማልያ ወጣቶች ሌሎች ተጨማሪ መርከቦችንም ለማገት እንዲነሳሱ አድርጓቸዋል፡፡ ታድያ ይህ ባጭር ጊዜ ከፍተኛ ገቢን የሚያስገኝ እድል መፈጠሩን የሰሙት የሱማልያ ሚሊሻዎችና እንደ አልሻባብ ያሉ የአሸባሪ ቡድኖች አሳ አጥማጆቹን በማስታጠቅና የተለያዩ ድጋፎችን በመስጠት ከሚገኘው ዶላር ላይ መካፈልን ጀመሩ፡፡ አልሻባብ ወይም ሌሎች የሱማልያ ታጣቂዎች እንደ አሳ አጥማጆቹ የህንድ ውቅያኖስን እየሰነጠቁ ማዕበልን ተጋፍጠውና አቅጣጫ ሳይጠፋቸው በውሃ ላይ መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡ በአንፃሩ ደግሞ አሳ አጥማጆቹ እንደ የሳተላይት ስልክ፣ የጦር መሳርያና ሌሎች ድጋፎች ስለሚያስፈልጋቸው ሁለቱ አካላት በቅንጅት የህንድ ውቅያኖስን ለማናወጥ ችለው ነበር፡፡

ዛሬ ሽፍቶቹ በሃያላን አገር የጦር መርከብ በአካባቢው ማስፈር ምክንያት መርከቦችን ደፍረው መጠጋት የተዉ ይመስላል፡፡ ነገር ግን እንደ ቻይናና ኢራን የመሳሰሩ አገራት ዘመናዊ የአሳ አጥማጅ መርከቦችን በመላክ በህገወጥ መልኩ በሱማልያ የውቅያኖስ ዳርቻ ላይ መረቦቻቸውን መዘርጋታቸውን ቀጥለዋል፡፡ የሱማልያ መንግስትም ድንበሩን የሚቆጣጠርበት አቅም አጥቶ ዘንድሮም ለህልውናው እየታገለ ይኖራል፡፡

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -