Saturday, January 22, 2022

በህዳሴ ጉዳይ ለሁለት የተከፈለው የአሜሪካ መንግስትና ኢትዮጵያ ወደ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የላከችው ሽምግልና

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

በቅርቡ ከወደ ዋሽንግተን ዲሲ የተሰማው ዜና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ቀኝ እጅ የሆኑት የግምዣ ቤት ፀሃፊው ስቲቭን ምዩንሽን አሜሪካ ለኢትዮጵያ እያደረገች ያለችው እርዳታ ዝርዝር ከሚመለከተው የመንግስት አካል እንዲቀርብላቸው መጠየቃቸውን ይገልፃል፡፡ በህዳሴ ግድብ ዙርያ ኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳንን እንድያደራድሩ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ሃላፊነት ከተሰጣቸው ሁለት አደራዳሪዎች አንዱ የነበሩት ስቲቭን ምዩንሽን ኢትዮጵያ ድርድሩን አቋርጣ በመውጣቷ ከመቆጣትም አልፈው ስምምነት ሳይደረስ ግድቡን እንዳትሞላ የሚል ማሳሰብያ ሰጥተው የነበረ ሲሆን ለኢትዮጵያ በየአመቱ የሚሰጠው እርዳታ ዝርዝር ይቅረብልኝ ማለታቸውም እርዳታን እስከ ማቋረጥ የሚደርስ እርምጃ ለመውሰድ እያሰቡ መሆናቸውን ያመላክታል ፡፡እርምጃው ከሰብአዊነት ጋር የተያያዙ ረሃብን ለመከላከልና የሕፃናትን ጤንነት ለመጠበቅ የሚደረጉ እርዳታዎችን የማይነካ ሲሆን ባብዛኛው ከደህንነትና ከኢኮኖሚ ጋር የተያያዙ እርዳታዎችን እስከማገድ የሚደርስ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

ሆኖም ባብዛኛው የውጭ ጉዳይ የሚመለከተው የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት (እንደ ውጭ ጉዳይ ማለት ነው) የፕሬዝዳንት ትራምፕና የስቲቭን ምዩንሽን ለግብፅ ከፍተኛ አድልኦ ያሳየ ድርጊት አሜሪካ ለወደፊት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ወዳጅነት እንዳያሻክረው በመስጋቱ የስቴት ዲፓርትመንት ሃላፊዎች እስካሁን ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታን ዝርዝር የሚያሳይ ዶክመንት ለግምዣ ቤቱ ስቲቭን ምዩንሽን አልላኩም፡፡ በተለምዶ የስቴት ዲፓርትመንት የውጭ ጉዳይና የዲፕሎማሲ ስራዎችን በሃላፊነት የሚሰራ ሆኖ ሳለ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጉዳዩ ምንም ለማይመለከታቸውና ባብዛኛው ሃላፊነታቸው ከኢኮኖሚና ገንዘብ ከማተም ጋር ለሆነው የግምዣ ቤቱ ዋና ፀሃፊ ስቲቭን ምዩንሽን እንዲያደራድሩ ሃላፊነት መስጠታቸው በስቴት ዲፓርትመንት ሃላፊዎች ዘንድ ግራ መጋባትን እንዲሁም ቅሬታን ፈጥሮ ነበር፡፡

ሆኖም እንደ ኢትዮኖሚክስ ግምት ስቲቭን ምዩንሽን ለአደራዳሪነት የተመረጡበት ምክንያት አሜሪካ በዓለም ባንክ ያላትን ድርሻ ወክሎ ድምፅ የሚሰጠውና ከባንኩ ጋር ያላትን ጉዳይ የሚያስፈፅመው የአገሪቱ ግምዣ ቤት በመሆኑ ዋና ፀሃፊው ስቲቭን ምዩንሽንም በዓለም ባንክ ያላቸውን ተሰሚነት በመጠቀም ባንኩ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ግድቡ እንዳይሞላ ግፊት እንዲያደርግ በሚል ሃሳብ ነው ብሎ ያምናል፡፡ በተለይም ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ጀምሮ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጫና የመፍጠር እድል ከተከፈተላቸው የውጭ ተቋማት አንዱ በሆነው በዓለም ባንክ ላይ ከፍተኛ ድርሻ ያላት አሜሪካ ተቋሙን በእጅ አዙር እንደፈለገች ታሽከረክረዋለች የሚሉ ትችቶች ይሰማሉ፡፡ ለዚህም ማስረጃ የሚሆን ከ1 ወር በፊት የኢትዮጵያን ግድቡን እሞላለው የሚል ይፋ አቋም ተከትሎ የዓለም ባንክ ከዚህ በፊት ለማበደር ቃል ገብቶት የነበረውን ገንዘብ ለጊዜው አግዷል የሚል ዜና መሰማቱ ይታወሳል፡፡ ይህንን ጠንቅቀው የሚያውቁት ፕሬዝድንት ትራምፕ የግድቡን ውዝግብ ለመፍታት እንዲያደራድሩ የመረጧቸው ሁለት አካላት የዓለም ባንኩ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማላፓስና የግምዣ ቤቱ ዋና ፀሃፊ ስቲቭን ምዩንሽን መሆናቸው በምን መልኩ ኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛውን ግፊት ማድረግ ይቻላል በሚለው ላይ ጠንቅቀው እንዳሰቡበት ያመላክታል፡፡

ታድያ የዶናልድ ትራምፕና የስቲቭን ምዩንሽን በአጭር ጊዜ ጥቅም ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴን በመቃወም በርካታ የአሜሪካ ምክር ቤት አባላትና የስቴት ዲፓርትመንት ሃላፊዎች ፕሬዝዳንቱ ላይ ትችቶችን ሲሰነዝሩ ቆይተዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሚቀጥለው ምርጫ የማሸነፍ እድሌን ያሰፋልኛል በሚል እስራኤልንና ፍልስጤምን ያስማማል ብለው ያቀረቡት የመፍትሄ ሃሳብ ለእስራኤል ያደላ በመሆኑና ከፍልስጤማውያንም አልፎ ግብፅንና የተለያዩ የአረብ አገራትን ማስቆጣቱ ምናልባት ግብፅን በህዳሴ ግድብ በመደለል ማግባባት ይቻላል በሚል እምነት ድንገት ሳይታሰብ በግድቡ ጉዳይ ላይ አደራዳሪ ካልሆንኩ የሚል ጥያቄ እንዲያቀርቡ ዳርጓቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ኢትዮጵያ ለረጅም አመታት ይዛው የነበረውን የውጭ አደራዳሪ በተለይም የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት ያለመቀበል አቋም ወደ ጎን በመተው የዶናልድ ትራምፕን ጥያቄ ተቀብለው የግድቡን ድርድር ወደ ዋሺንግተን ዲሲ መላካቸው ለከፍተኛ የአገር ውስጥ ተቃውሞ ዳርጓቸው ነበር፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት ከፕሬዝዳንት ትራምፕ እንዲያሸማግሏቸው በሚል ከአንድ የህግ ባለሙያ ጋር ለሶስት ወር የሚቆይ የ130 ሺ ዶላር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ደጋፊና የቅርብ ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የህግ ባለሙያው ክሬግ በርካርድ ከፕሬዝዳንቱ ጋር ያላቸውን ቅርበት በመጠቀም የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስጠብቁ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ ለምሳሌም የኢትዮጵያን አምባሳደር ፍጹም አረጋን ጨምሮ የተለያዩ የኤምባሲ ሃላፊዎች ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ውይይት የሚያደርጉበትን መንገድ ማመቻቸት፣ ኢትዮጵያ አሜሪካንን ከጎኗ ለማሰለፍ በምትጠቀምባቸው ስልቶች ላይ ማማከር፣ እንዲሁም ስለ ኢትዮጵያ ጠቃሚነትና የአሜሪካ ታሪካዊ ወዳጅነት ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ማብራራትና ማግባባት የሚሉት ይጠቃለላሉ፡፡ ክሬግ በርካርድ ከዚህ በፊት በቀድሞው ፕሬዝደንት ጆርጅ ቡሽ ዘመን የአሜሪካ ንግድ ቢሮ የህግ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡ይህ አይነት አሰራር በእንግሊዝኛ አጠራሩ ሎቢዪንግ የሚባል ሲሆን የቀድሞው የኢህአዴግ መንግስት በአመት እስከ 4 ሚልዮን ዶላር በማውጣት በዋሺንግተን ዲሲ ሎቢስቶችን ቀጥሮ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ግብፅና ሱዳንን ጨምሮም በርካታ አገራት በበኩላቸው ከፍተኛ ገንዘብ በማፍሰስ ሎቢስቶችን ቀጥረው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጥቅማቸውን ለማስከበር የአቅማቸውን ግፊት በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ለማድረግ እንደሚሰሩ ይታወቃል፡፡

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -