Saturday, January 22, 2022

በሳውዲ እስር ቤቶች የሚማቅቁ ኢትዮጵያውያን በድንገት የዓለምን ትኩረት አግኝተዋል

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

“ሰው መሆኔን እንድጠላ ያደረገኝ ስራ ነው” በማለት በፌስቡክ ገፁ ላይ ገጠመኙን ያካፈለው ጋዜጠኛ ዘካርያስ ዘላለም ከሚኖርበት ካናዳ አዘጋጅቶት በእንግሊዙ ዘቴሌግራፍ ጋዜጣ ላይ ያሳተመው ፅሁፉ የዓለም መገናኛ ብዝሃን አውታሮችን ትኩረት ከመሳብም አልፎ የሳውዲ አረብያና የኢትዮጵያ መንግስታት እርስ በርሳቸው ጣት እንዲቀሳሰሩ ዳርጓቸዋል። ባሳለፍነው ሚያዝያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በሳውዲ አረብያ መስፋፋት ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከነዳጅ መፍለቅያዋ ምድር ተባረው ነበር። የሳውዲ መንግስት ከ 3ሺ በላይ የሚሆኑትን ካባረረ በኋላ ቀጣይ 200ሺ ያህሉን ለማባረር በዝግጅት ላይ ሳለ ከሰብአዊ መብት ተቋማት በደረሰበት ትችት ምክንያትና የኢትዮጵያ መንግስት ተመላሾቹን ስደተኞች የመቀበል አቅም እንደሌለው በማሳወቁ ሃሳቡን እንዲቀይር ተገዶ ነበር።

ይሁን እንጂ የሳውዲ መንግስት እነዚህን ወደ አገራቸው ሊላኩ የነበሩ ቀሪ 200ሺ ኢትዮጵያውያን ተሰማርተው ወደነበሩበት የስራ ቦታቸው ከመመለስ ይልቅ ወደ እስር ቤት ማጎርን ነበር የመረጠው። በአንድ ክፍል እስከ መቶ በሚደርስ ቁጥር የታጎሩት እስረኞች ከአሁን አሁን ተለቀቅን በማለት ሲጠባበቁ ከአራት ወራት በላይ የማቀቁ ሲሆን በእስር ቤቶቹ ያለው የንፅህና ጉድለት ከሳውዲ አስከፊ ሙቀት ጋር ተደምሮ በርካቶችን ለበሽታ ዳርጓቸዋል። አንዳንድ እስረኞች የተንቀሳቃሽ ስልኮችን ደብቀው ለማስገባት በመቻላቸው በኢትዮጵያና በሌሎች አገራት ላሉ ወገኖች እንዲሁም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የድረሱልን ጥሪን ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

እስረኞቹ በፌስቡክና በቴሌግራም በለቀቋቸችው ፎቶዎችም ለቆዳ በሽታ ተዳርገው ፊታቸው የቆሳሰሉና ከሙቀቱ ሃያልነት የተነሳ እራቆታቸውን እርስ በርስ ተደራርበው በታሰሩባቸው ክፍሎች መሬት ላይ ተኝተው ይታያሉ። ከዚህም በተጨማሪ በፎቶዎቹ መሬት ላይ የወደቀ ሬሳና እራሱን በመስኮት አንቆ የገደለ ወጣት በሚዘገንን መልኩ ይታያሉ። ታድያ ስለዚህ ጉዳይ በፓርላማ ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ለጥያቄው የሰጡት ምላሽ ብዙዎችን ያስቆጣ ነበር። “በራሳቸው ጊዜ ሳያማክሩን በህገ ወጥ መልኩ አገር ጥለው ከወጡ በኋላ ችግር ሲያጋጥማቸው ብቻ ነው የመንግስትን እርዳታ የሚፈልጉት” ካሉ በኋላ ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለውም “እነዚህ ስደተኞች አንዳንዶቹ አገር የማተራመስ አላማ ያላቸው በመሆኑ በገዛ እጃችን ወደ አገር ውስጥ አስመልሰን ከተሞቻችንን አናስበጠብጥም” ነበር ያሉት።

በእስር ላይ ከሚገኙት አብዛኛዎቹ የትግራይ ተወላጅ መሆናቸው እንደተሰማም የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ክልላቸው ስደተኞቹን ለመቀበል ዝግጁ መሆኗንና የሳውዲ መንግስት በአውሮፕላን አሳፍሮ በቀጥታ ወደ መቀሌው አሉላ አባነጋ አየር ማረፍያ ሊልካቸው እንደሚችል የሚገልፅ ደብዳቤ ከወር በፊት ወደ ሪያድ ልከው ነበር። ሆኖም ከሳውዲ በኩል የተሰጠ ምላሽ ባለመኖሩ ባሳለፍነው ማክሰኞ ዶ/ር ደብረፅዮን ለሳውዲው ንጉድ ሳልማን ዳግም ለሁለተኛ ጊዜ ደብዳቤ መላካቸው ተዘግቧል። በዚህ ደብዳቤም የፌደራል መንግስት ዜጎቹን ለመቀበል ለምን እንዳልፈለገ ግልፅ እንዳልሆነና የትግራይ ክልል በእስር ላይ የሚገኙትን ስደተኞች ለመቀበል ዝግጁ በመሆኗ ንጉስ ሳልማን የተለመደውን ትብብራቸውን እንዲያደርጉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጠይቀዋል።

የእንግሊዙ ዘቴሌግራፍ ያወጣው ዘገባ በአሜሪካና አውሮፓ ባሉ ጋዜጦች በመስተጋባቱ በዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ዘንድ ሳውዲ ላይ በርካታ ትችትን ያስነሳ ሲሆን የሳውዲ መንግስት በበኩሉ ስደተኞቹ ያሉበት ሁኔታ ይህን ያህል የከፋ ስለመሆኑ በቂ መረጃ እንዳልነበረውና የችግሩ ዋነኛ ምንጭ ግን የኢትዮጵያ መንግስት ስደተኞቹን ተቀብዬ የማቆይበት የለይቶ ማቆያ የለኝም በሚል ሊቀበላቸው ፍላጎት ባለማሳየቱ ነው ሲል ስሞታ አቅርቧል። የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር በበኩሉም ስለ እስር ቤቶቹ አስከፊ ሆኔታ ለመጀመርያ ጊዜ የሰማው ሰሞኑን በእንግሊዙ ጋዜጣ ላይ ከወጣው ዘገባ እንደሆነ አስታውቋል።

ሆኖም ዘቴሌግራፍ በትላንትናው እለት ባወጣው ሁለተኛ ዘገባ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ሰኔ 17 ቀን በሳውዲ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በፃፈው ደብዳቤ ታሳሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ የሚያሳዩ ፎቶዎችን መልቀቃቸው ቤተሰቦችንና የኢትዮጵያን ሕብረተሰብ እየረበሸ በመሆኑ ከዚህ በኋላ በኢንተርኔት ከመለጠፍ እንዲቆጠቡ ፎቶዎቹን መልቀቅ ከቀጠሉ ግን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ሲያስጠነቅቅ ያሳያል። ይህም የኢትዮጵያ መንግስት የዘ ቴሌግራፍ ዘገባ ከመውጣቱ በፊት ስለ እስረኞቹ አስከፊ ሁኔታ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም በሚል የሰጠው ምላሽ ከእውነት የራቀ መሆኑንና ቆንስላው ፎቶዎቹ እንዳይለቀቁ ሲያስፈራራ እንደነበር ያሳያል።

ከእነዚህ ፎቶዎች በአንዱ ላይም ሙቀት መቋቋም አቅቶት የሞተ ወጣት የሚታይ ሲሆን መሬት ላይ በጨርቅ ተሸፍኖ ከእስረኞቹ መሃል ይገኛል። “ከመሃላችን አንዱ ሲሞት የእስር ቤት ጠባቂዎቹ እንደ ቆሻሻ ከጀርባ ወስደው ይጥሉታል” ያሉት ታሳሪዎቹ “የገዛ መንግስታቹ ካልፈለጋቹ እኛ ምን እናድርጋቹ” እንደሚሏቸው ተናግረዋል። ለአራት ወራት ያክል ታስሮ የቆየ አበበ የተባለ አንድ ስደተኛ ጠባቂዎቹ እንደሚደበድቧቸውና እንደ ቆሻሻ እንደሚታዩ እንዲሁም የዘረኝነት ስድብ እንደሚሰድቧቸው ለዘቴሌግራፍ ገልጿል። በበረሃ ላይ በአንድ ሞቃታማ ክፍል ተደራርበው ቀንና ለሊት ማሳለፋቸው ሳያንስ ያለ በቂ ውሃ በቀን አንድ ዳቦና ትንሽ ሩዝ ብቻ እንደሚያገኙ የገለፁት ስደተኞቹ ከለቀቋቸው ቪድዮዎች በአንዱ ላይ የታሰሩበትን ክፍል ከሽንት ቤት ሞልቶ የሚፈስ ሰገራ አጥለቅልቆት ይታያል።

ከሳውዲ ከተሞች ተለቅመው ከታሰሩት በተጨማሪ በየመን ወደ ሳውዲ ጉዞ ላይ የነበሩና ሁቲ በተባሉት ታጣቂዎች እየተባረሩ ወደ ሳውዲ ድንበር የተገፉ ዜጎች ይገኙበታል። ባለፈው ወር ሂዩማን ራይትስ ዋች በመባል የሚታወቀው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት የሁቲ ታጣቂዎች ኢትዮጵያውያኑ የኮሮና በሽተኖች ናቸው በሚል ወደ ሳውዲ ሲያባርሯቸው እንደነበረና አንድ ቦታ ላይ ስደተኞቹ ወደ ተሰበሰቡበት አካባቢ መድፍ በመተኮስ 40 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን በአንድ ጊዜ እንደገደሉ ያስረዳል። በተለይም በሚያዝያ ወር ላይ የሁቲ ታጣቂዎች ኢትዮጵያውያኑን በመሳርያ እያስፈራሩና ለማምለጥ የሞከሩትን እየገደሉ ወደ ሳውዲ ድንበር ካስጠጓቸው በኋላ የሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች በበኩላቸው ተኩስ በመክፈታቸው ስደተኞቹ በሁለት ታጣቂዎች መሃል አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው እንደነበር ሪፖርቱ ያሳያል።

ዘቴሌግራፍ የስደተኞችን አሰቃቂ ሁኔታ ለዓለም ይፋ ካደረገ በኋላም የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ስቴፈን ዳውቲ በሳውዲ አረብያ ባሉ አፍሪካውያን ላይ እየተፈፀመ ያለው ተግባር በአስቸኳይ መቆም እንዳለበትና ገለልተኛ የጤና ባለሙያዎችና የሰብአዊ መብት ተቋማት የእስረኞቹን ሁኔታ እንከታተሉ የሳውዲ መንግስት እንዲፈቅድ አሳስበዋል። ሚንስትር ስቴፈን ዳዊቲ አክለውም የእንግሊዝ መንግስት ሚንስትሮች ሳውዲ ይህንን ተግባር እንድታቆም ጫና እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዘቴሌግራፍን ዘገባ ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ባወጣው መግለጫ መንግስት ባለፉት ሶስት ዓመታት ከ400 ሺ በላይ ተመላሽ ዜጎችን ከሳውዲ አረብያ እንደተቀበለና ኢትዮጵያ ከየትኛውም አገር ዜጎቿን አልቀበልም ብላ አታውቅም ሲል አስተባብሏል። ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አክሎም ከጷግሜ 3 ጀምሮ ስደተኞቹን ወደ አገራቸው የመመለስ ሂደት እንደሚጀመር አስታውቋል።

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -