Saturday, January 22, 2022

በትግራይ ምርጫ የሚፎካከሩት ፓርቲዎችና የአመለካከት ልዩነታቸው

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

በነገው እለት በትግራይ የሚደረገው ክልላዊ ምርጫ ከክልሉም ባሻገር ከአዲስ አበባ እስከ አስመራና ዋሽንግተን ዲሲ ድረስ የበርካቶችን ትኩረት ስቧል። የፌደራል መንግስት ይህ ዓመት ከመገባደዱ በፊት ሊደረግ የነበረውን ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ ለማራዘም ወስኖ ሳለ የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ምርጫ እንዲካሄድ መወሰኑ አወዛጋቢ ሆኖ ቆይቷል። ይህንን ተከትሎም ባሳለፍነው ቅዳሜ በተጠራው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የአማራ ክልል ተወካዮች ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል መንግስት ላይ እርምጃ ይወሰድ የሚል ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ያደረጉት ያልተሳካ ግፊት ጉዳዮ ምን ያህል አወዛጋቢና ፖለቲከኞችን የከፋፈለ መሆኑን ያሳያል።

ይባስ ብሎም የክልሉን ምርጫ ለመዘገብ ከአዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፍያ ወደ መቀሌ ሊጓዙ የነበሩ የውጭና የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ የመረጃና ደህንነት አባላት ጉዟቸው እንዲስተጓጎል መደረጉ በፌደራል መንግስትና በትግራይ ክልላዊ መንግስት መካከል ያለው አለመግባባት ምን ያህል እንደተካረረ የሚያመላክት ነው።

ታድያ የትግራይ ክልላዊ ምርጫ ሕጋዊ ወይስ ሕገወጥ የሚለው ውዝግብ የአብዛኛዎቹን የመገናኛ ብዙሃንና ከክልሉ ውጭ ያሉ ፖለቲከኞችን ሙሉ ትኩረት በመያዙ ከዚህ ምርጫ ጋር ተያይዞ የመጣን አንድ ትልቅ ቁም ነገር ትኩረት እንዲያጣ ዳርጎታል። በምርጫው ላይ የሚሳተፉት ዋና ዋና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሃ.ት)፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት)፣ ውድብ ናፅነት ትግራይ (ሳ.ወ.ት)፣ ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዓዴፓ) እንዲሁም ባይቶና ሲሆኑ ከነዚህ አምስት ፓርቲዎች ውስጥ ሁለቱ አሁን በኢትዮጵያ ያለው በፌደራል ስርዐት ላይ የተመሠረተ አወቃቀር ተቀይሮ የኮንፌደሬሽን ማለትም ትግራይን ከክልልነት ከፍ አድርጎ ከኢትዮጵያ ጋር በኮንፌዴሬሽን ወደ ተቆራኘች አባል አገር ለማሸጋገር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል። ውድብ ናፅነት ትግራይ የተባለው ፓርቲ በበኩሉ ምርጫ አሸንፎ ስልጣን ከያዘ አንቀፅ 39ኝን በማወጅ ትግራይን ሙሉ በሙሉ እራሷን የቻለች ነፃ አገር አንድትሆን አደርጋለው በሚል ቅስቀሳ እያደረገ ይገኛል።

ከታሪካዊው ኢህአፓ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ከሚነገርለት ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዓዴፓ) በስተቀር ኢትዮጵያ አሁን በተዋቀረችበት የፌደራል ስርዐት መቀጠል አለባት የሚለውን የገዢውን የህወሃት ፓርቲ አቋም አጥብቀው በመቃወም ለትግራይ ከአሁኑ የላቀ ሉአላዊነትን የሚሹ ሦስት ተፎካካሪ ፓርቲዎች መፈጠር ኢትዮጵያ እያመራችበት ያለውን የፖለቲካ አቅጣጫ የሚያመላክት ነው። በአንድ በኩል የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ ብሔርን መሠረት አድርጎ የተዋቀረው የፌደራል ስርዐት መከለስ አለበት የሚሉ በአብዛኛው ከአዲስ አበባና ከአማራ ክልል አካባቢ የሚነሱ ጥያቄዎች በሌላ በኩል ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ኢትዮጵያን ከፓርላመንታዊ ወደ ፕሬዝዳንታዊ ስርአት ለማሸጋገር ያላቸውን ፍላጎት በመመልከት የትግራይ ህልውና አደጋ ላይ ነው የሚሉ አካላት በትግራይ ከእለት ወደ እለት ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል።

በአክሱም ስልጣኔ ዘመን ታላቅነትን ተጎናፅፋ የነበረችው ትግራይ ወደ ኋላ ቀርነት እንድትመለስ ያደረጋት ከሸዋ ጋር ሲደረግ የኖረው ሽኩቻና ከአፄ ዮሃንስ እስከ ህወሃት ያሉ ሃይሎች መነሻቸው የሆነችው ትግራይን አልፈው ሄደው በመሃል አገር ፖለቲካ በመጠመዳቸው ነው የሚለው ውድብ ናፅነት ትግራይ (ውናት) ከዚህ በኋላ አንቀፅ 39ኝን በማወጅ ሃገረ ትግራይን መመስረት ብቸኛው አማራጭ መሆኑን በተደጋጋሚ ይገልፃል። በመቀሌ ዩንቨርስቲ ምሁራን የሚመራውን ውናት ወክለው ከሳምንት በፊት በቴሌቭዥን ክርክር ላይ የቀረቡት አቶ ግርማይ በርሀ ፓርቲያቸው ምንም አይነት የሕገመንግስት መሻሻል ጥያቄ እንደሌለውና አሸንፈው ስልጣን ከያዙ በቀጥታ አንቀፅ 39ኝን ለማወጅ ሕዝቡን እንደሚያስመርጡ ገልፀዋል።

በተደጋጋሚ አዲስ አበባ ካሉ የአማርኛ ቋንቋ መገናኛ ብዙሃን ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ የነበሩት የባይቶና ፓርቲ አመራሮች በበኩላቸው ህወሃትን ፀረ ዲሞክራሲያዊና የሕዝቡን አደራ የበላ፣ ትግራይን ረስቶ አዲስ አበባና ሌሎች ክልሎችን ሲያለማ ብሎም የራሱን ስልጣን ሲያመቻች የቆየ በማለት ጠንከር ያለ ትችትን በገዥው ፓርቲ ላይ አውርደዋል። የባይቶና ሊቀመምበር የሆኑት አቶ ኪዳነ አመነ በአንድ ወቅት ኢትዮ ፎረም መቀሌ ውስጥ ባዘጋጀው ውይይት ላይ ህወሃት 10 ጊዜ ህገመንግስቱ ይከበር እያለ በፌደራል መንግስት ላይ የሚያደርገው ግፊት ለፕሮፓጋንዳ ብቻ ሳይሆን በትግራይ ክልል ውስጥም መስራት አለበት ሲሉ ተደምጠዋል። በአመሰራረቱ ወቅት የፌደራል ስርአትን ይቀበል የነበረው ባይቶና ከአንድ ዓመት በኋላ ትግራይ ከኢትዮጵያ ጋር በኮንፌደሬሽን መቀጠል አለባት የሚል የተከለሰ አቋሙን ግልፅ ካደረገ ሰነባብቷል። ባይቶና ስሙን የተዋሰው ባይቶ ከተባለው የትግራይ ባህላዊ የሸንጎ አሰራር ሲሆን ህወሃት ይከተላቸዋል ያላቸውን ከአውሮፓና ከእስያ የመጡ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መርሆዎች በመተው ባህላዊና ገበሬው በቀላሉ ይረዳዋል ባለው ከታች ወደላይ የሚዘረጋ የስልጣን አወቃቀር መተካት አላማዬ ብሎ ተነስቷል።

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሰው ደግሞ ሌላው ተፎካካሪ ፓርቲ ሲሆን ከፓርቲው አመራር አባላት አንዱ የሆኑት አቶ ወልደግዮርጊስ ገብረህይወት ጥቅምት ላይ ከአውሎ ሚድይ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “የፌደራል መንግስት በጣም ከአቅሙ በላይ ስልጣንና ሃብት ይዟል፤ ይህ ደግሞ ለምሳሌ አድልኦ ለማድረግ ወይም ፖለቲካ ለመስራት ሲፈልግ ያጠቃሃል፤ ይህ የትግራይ ሕዝብ የታገለለት አላማ አልነበረም” ሲሉ ፓርቲያቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በስራ ላይ በዋለው የፌደራል ስርዐት ላይ ያለውን አመለካከት አካፍለው ነበር። የሶሻል ዲሞክራሲን የሚያቀነቅነው ሳወት እንደ ካፒታሊዝም ባለ ሃብቶች ብቻ በፖለቲካውና ኢኮኖሚው ላይ የማይሳተፉበት ወይም እንደ ኮምኒዝም መንግስት ብቻውን ፖለቲካና ኢኮኖሚን የማይቆጣጠርበት ሁሉም ሕብረተሰብ መሃል ላይ ተገናኝቶ ማህበራዊ ተሳትፎ የሚያደርግበት የፖለቲካና የኢኮኖሚ መድረክ ለመፍጠር ቆርጦ ተነስቷል። በአቶ ሃይሉ ጉደፋይ የሚመራው ሳወት ኢትዮጵያን የሚያያት የትግራይን ጥቅም ከማስከበር አንፃር ሲሆን በፌደሬሽን መቆየት የመጀመርያው አማራጭ እንደሆነና ነገር ግን እንደ አንቀፅ 52 ያሉ የኢኮኖሚ ፖሊሲን የመቅረፅ ስልጣን በአመዛኙ ለፌደራል መንግስት የሚሰጡ አንቀፆች የክልሎችን ስልጣን የሚያዳክሙ በመሆናቸው እነዚህን ህጎች ለማሻሻልም እንዳያስችል አሁን ያለውን የሻከረ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖለቲካ ከግምት ውስጥ በማስገባት የኮንፌደሬሽን ስርዐት የተሻለ ነው ወደሚል ድምዳሜ የገባ ይመስላል።

ከሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለየት ያለ አቋም ያለው ደግሞ አዲሱ ኢህአፓ የሚል ቅፅል ስያሜ የተሰጠው ዓሲምባ ዴሞራስያዊ ፓርቲ (ዓዴፓ) ነው። ዓዴፓን ከታሪካዊው ኢሕአፓ ጋር የሚያመሳስለው ማሕበራዊ መሠረቱ ኢሮብ በመባል የሚታወቀው በምስራቃዊ ትግራይ የኤርትራ ድንበር አዋሳኝ ላይ የሚገኘው ብሔረሰብ መሆኑና እራሱን የሰየመበት የዓሲምባ ተራራም ከ46 ዓመት በፊት ከደርግ ሸሽተው ወደ አካባቢው የተሰደዱ የኢሕአፓ አባላት በወቅቱ ተሸሽገውበት የነበረው አካባቢ በመሆኑ ነው። ሆኖም ዓዴፓ ከሌሎች ተፎካካሪዎች የሚለይበት ዋነኛ ምክንያት ለኢሮብ ብሔረሰብ አባላት ጥብቅና የቆመ መሆኑ ነው። ዓዴፓ የባድመንም ሆነ ሌሎች ግዛቶችን ወደ ኤርትራ ተላልፎ መሰጠት አጥብቆ ሲቃወም “መንግስት የአልጀርስን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ተቀብያለው ማለቱ ብዙ መሬቶች በተለይም ከኢሮብ፤ ከግማሽ በላይ ወደ ኤርትራ ይሄዳል” ሲሉ የፓርቲው መስራች አባልና አስተባባሪ አቶ ዶሪ አስገዶም ለጀርመን ድምፅ ከዓመት በፊት ገልፀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች እስካሁን በቂ ትኩረት ያልሰጡት የገጠራማ ትግራይ ሕብረተሰብ ተፎካካሪ ፓርቲዎቹን በህወሃት እንዲሸነፉ መዳረጉ አይቀሬ ነው። ነፃና ሉአላዊት የሆነች ሃገረ ትግራይን ለመመስረት የሚታገለው ውናት አዲስ የምትወለደው አገር እንዴት አድርጋ በኢኮኖሚ እራሷን እንደምትችልም ሆነ ሊያጋጥሟት ስለሚችሉ መሰናክሎች በቂና አጥጋቢ የሆነ ዝርዝር ለሕዝቡ አላቀረበም። በሌላ በኩል ደግሞ አገር በቀልና ባህላዊ ለሆኑ የአስተዳደር ዘይቤዎች ትኩረት በመስጠት በክልሉ አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ ስርዐትን ማስፈን የሚፈልገው ባይቶና ይህ ባህላዊ የአስተዳደር ዘዴ ወደ ኢኮኖሚው ሲኬድ ምን አይነት ለውጥ እንደሚያመጣና በትክክል የፓርቲው ባይቷዊ ዘይቤን መሠረት ያደረገ የኢኮኖሚ መርህ ምን ሊመስል እንደሚችል እስካሁን ግልፅ ያደረገ አይመስልም። ተያይዞም ከዓመት በፊት ከጀርመን ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፓርቲያቸው ሶሻል ዴሞክራት እንደሆነ የገለፁት የዓዴፓ መሪ አቶ ዶሪ አስገዶም በበኩላቸው በቅርቡ በትግራይ ቲቪ ላይ በተካሄደ ክርክር ላይ ደግሞ ፓርቲያቸው ሙሉ በሙሉ በነፃ ገበያ ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚን ይደግፋል የሚል ከበፊቱ የሚቃረን አቋም መግለፃቸው ዓዴፓ ለኢኮኖሚው የሰጠውን ትኩረት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው።

ከሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተሻለ መልኩ የኢኮኖሚ መርሁን ግልፅ ያደረገው ሳልሳይ ወያነ ትግራይም (ሳወት) ቢሆን ይዞት የመጣው የሶሻል ዲሞክራሲ ርዕዮት ዓለም ማህበራዊ ፍትህን የሚያሰፍን፤ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የሕብረተሰቡ አባላት ወደኋላ እንዳይቀሩና እነሱን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፖሊሲዎችን የሚቀርፅ፤ በሃብት ክፍፍል የሚያምን ግን ደግሞ ዲሞክራሲያዊ የሆነ ስርዐትን የሚያሰፍን ነው። ሶሻል ዲሞክራሲ በአብዛኛው ሲተገበር የሚታየው እንደ ጀርመንና ስዊድን ባሉ የበለፀጉ አገራት ሲሆን ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ገና የሃብት ማካበት ሂደት ላይ ባሉ አገራት የሃብት ክፍፍልንና ማህበራዊ ፍትህን መሰረቱ ያደረገ ርዕዮተ ዓለም ይዞ መምጣት ለትግራይ ተመጣጣኝ ነው ወይ የሚል ጥያቄን ሲያስነሳ ታይታል።

ዛሬ ጠዋት ኢትዮኖሚክስ ያነጋገራቸው የሳወት አመራር አባል የሆኑት አቶ ሃይሉ ከበደ ኢኮኖሚውን በተመለከተ ፓርቲያቸው ከህወሃት በምን ይለያል የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው የትግራይ ችግር የሚመነጨው ህወሃት ከሚከተለው አብዮታዊ ዲሞክራሲ ነው ካሉ በኋላ ህወሃት እንደሚያደርገው የተወሰነ የሕብረተሰብ ክፍልን ለመጥቀም በሚል አንዱን የኢኮኖሚ ዘርፍ ከሌላው ለይቶ ማበረታታት ሳይሆን ሳወት በክልሉ ውጤታማ የመሆን አቅም አላቸው ለተባሉ ዘርፎች ሁሉ ሳያዳላ ማበረታቻ እንደሚያደርግ ገልፀዋል። በእርግጥ ትግራይ ካላት ለግብርና አመቺ ያልሆነ መልከአ ምድር አንፃር ህወሃት ለግብርና ዘርፉ የሚሰጠውን ልዩ ትኩረት ወደ ሌሎች ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉ ዘርፎች ማዞሩ ምክንያታዊ ነው። በተጨማሪም አቶ ሃይሉ እንዳሉት ሳወት የክልሉን መንግስት ከተቆጣጠረ ከህወሃት ጋር በሚመሳሰል መልኩ በኢኮኖሚው ላይ “ከባድ ሚናን” የሚጫወት ሆኖም በግል ዘርፉ ላይ መንገድ የመዝጋት ሳይሆን ፉክክርን እንደሚያበረታታ ገልፀዋል።

ነገር ግን የህወሃት ዋና ማህበራዊ መሠረት የሆነው አርሶ አደር የትግራይን ሕዝብ ከ80 ፐርሰንት በላይ ድርሻ የሚወስድ ሲሆን የሳወት ዘመናዊ አመለካከት በአጭር ጊዜ ውስጥ በአርሶ አደሩ ዘንድ ተቀባይነትን የማግኘት እድሉ አጠራጣሪ ነው። ህወሃት በትግራይ ክልል ስልጣን ላይ በቆየባቸው 27 ዓመታት በገጠሩ ክፍል የገነባቸው የጤናና የትምህርት ተቋማት፣ እንዲሁም ለገበሬዎች ማዳበርያን በረከሰ ዋጋ ሲያቀርብበት የነበረው መዋቅር ከነ ጉድለቱ ለአርሶ አደሩ ሕብረተሰብ አንፃራዊ የኑሮ መሻሻልን ያመጣ በመሆኑ ገዢው ፓርቲ በዘንድሮው ምርጫም ከትግራይ አርሶ አደሩ ሕብረተሰብ ከፍተኛ ድምፅን ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህም አልፎ የዘንድሮ ምርጫ በኮቪድ 19ኝ ምክንያት ተፎካካሪ ፓርቲዎች አብዛኛው ቅስቀሳቸውን በመገናኛ ብዙሃን እንዲወስኑ ማስገደዱ በቂ ግንኙነት ከአርሶ አደሩ ማሕበረሰብ ጋር እንዳያደርጉ እንቅፋት ሆኖባቸዋል።

ነገ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ወደ 3 ሚልዮን የሚጠጉ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን የክልሉን ምክር ቤት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮት የቆየው ህወሃት ስልጣኑን በተወሰነ መልኩ ማካፈሉ አይቀሬ ነው። ለትግራይ የበለጠ ነፃነትን የሚሹ ፓርቲዎች በክልሉ ምክር ቤት መቀመጫን ማግኘታቸው ደግሞ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ተፅዕኖን የሚያሳድርና ምናልባት ጠቅላይ ሚንስትሩ ቶሎ የአገር መድረክ እንዲመቻች ካላደረጉ የአገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር እየተሰነጣጠቀ ወደ ተለያየ አቅጣጫ የሚለያይ ይሆናል።

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -