Sunday, April 11, 2021

በአሜሪካ ትልቁ የልጆች አልባሳት መሸጫ ኢትዮጵያ ላሉ አቅራቢዎቹ ሰጥቶ የነበረውን ትእዛዝ ሰረዘ

Must Read

በአክሱም ከተማ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

  ተቀማጭነቱን በለንደን ከተማ ያደረገውና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ክትትል የሚያደርገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰአታት በፊት ባወጣው ባለ 25...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊል ድርሻ ለቱርክ መንግስት ሊሸጥ ነው

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እስከ...

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሸጠችው ቦንድ ዋጋው እያሽቆለቆለ ነው

ከውጭ ባለሃብቶች 1 ቢልዮን ዶላር ለመበደር በ2007 እ.ኢ.አ ኢትዮጵያ የሸጠችው ቦንድ በአየርላንድ የቦንድ ገበያ ላይ ባለሃብቶቹ እርስ በርስ የሚገበያዩበት...

ዘ ቺልድረንስ ፕሌስ የተባለው የህፃናት አልባሳትን የሚሸጥ የአሜሪካ ኩባንያ በሃዋሳና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ባሉ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች አልባሳትን ሲያሰራ የቆየ ቢሆንም ከቅርብ ወራት ወዲህ በኮቪድ19 ምክንያት የተከሰተውን የገበያ መቀዛቀዝ ተከትሎ በሚልዮኖች ዶላር የሚገመት ዋጋ ያለው ትእዛዝ መሰረዙ ታውቋል። ኩባንያው በተጨማሪም ከ7 እና 8 ወራት በፊት ለተላኩለት ልብሶች የነበረበትን እዳ በወቅቱ ሳይከፍል በ6 ወር እንዳራዘመው በኢትዮጵያ ያሉት አቅራቢዎቹ ለእንግሊዙ ዘጋርድያን የተባለ ጋዜጣ ገልፀዋል።

ተቀማጭነቱን ኒውጀርዚ በተባለችው በአትላንቲክ ውቅያኖስ ዳርቻ ላይ የምትገኝ የአሜሪካ ክልል ያደረገው ዘ ቺልድረንስ ፕሌስ በዓመት እስከ 2 ቢልዮን ዶላር የሚገመቱ የልጆች አልባሳትን የሚሸጥ ሲሆን በአሜሪካ ብቻ ከ1ሺ በላይ ሱቆች አሉት። ሆኖም ኮቪድ19 ባለፉት ወራት ያስከተለው የገበያ መቀዛቀዝ በኩባንያው ገቢ ላይ ተፅዕኖ ያሳደረበት በመሆኑ በአቅራቢዎች ላይ ያለበትን እዳ በዋጋ ቅናሽ መልክ እንዲቃለልለት ጥያቄ አቅርቧል። ይህም በኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አቅራቢዎቹን ችግር ውስጥ እንደከተታቸው ስሞታ ስሞታት ሲያሰሙ ታይተዋል። ከነዚህ አቅራቢዎች አንዱ ለ ዘጋርድያን እንደተናገረው ይህ ኩባንያ ግዙፍና ኪሱ ወፍራም ከመሆኑ አንፃር በዓለም ፍርድቤቶች ከሰን ልናሸንፈውና ገንዘባችንን ልናገኝ የምንችልበት ሁኔታ አይደለም ያለው ብለዋል።

በኩባንያው የአቅርቦት ክፍል ሃላፊ የሆኑት ግሬጎሪ ፑል በበኩላቸው የተሰረዘው ትእዛዝ አቅራቢዎች ከኢትዮጵያ ከሚልኩላቸው አጠቃላይ አልባሳት 3 ፐርሰንት ብቻ መሆኑን ገልፀው በወቅቱ ስራቸው ተጠናቆ ለነበሩ አልባሳት ግን ሙሉ ክፍያን መፈፀማቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም ኩባንያው አሁን በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ለአቅራቢዎቹ የሚሰጠውን ትእዛዝ ከ10 ፐርሰንት በላይ ማሳደጉን አክለዋል። ይሁን እንጂ ሌሎች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች አልባሳትን የሚረከቡ ኩባንያዎች በኪሳራ እያሉ እንኳን በትእዛዛቸው መሰረት ተረክበው ክፍያቸውን መፈፀማቸው ዘቺልድረንስ ፕሌስን ለትችት ዳርጎታል።

በተለይም እንደ ዘቺልድረንስ ፕሌስ ያሉ የውጭ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ ይረከቧቸው የነበሩትን የተለያዩ ምርቶች መጠን በመቀነሳቸው በብዛት ሴቶችን ቀጥረው የሚያሰሩት ከሕንድና ሆንግኮንግ የመጡ አቅራቢዎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ላሉ ሰራተኞቻቸው ይሰጧቸው የነበሩ እንደ ነፃ መጓጓዣ የመሳሰሉ ድጋፎችን ከማቋረጥ ጀምሮ ደሞዝ በግማሽ እስከ መቁረጥ ደርሰዋል።

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

በአክሱም ከተማ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

  ተቀማጭነቱን በለንደን ከተማ ያደረገውና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ክትትል የሚያደርገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰአታት በፊት ባወጣው ባለ 25...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊል ድርሻ ለቱርክ መንግስት ሊሸጥ ነው

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እስከ ግማሽ የሚጠጋ የባለቤትነት ድርሻ ለቱርክ...

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሸጠችው ቦንድ ዋጋው እያሽቆለቆለ ነው

ከውጭ ባለሃብቶች 1 ቢልዮን ዶላር ለመበደር በ2007 እ.ኢ.አ ኢትዮጵያ የሸጠችው ቦንድ በአየርላንድ የቦንድ ገበያ ላይ ባለሃብቶቹ እርስ በርስ የሚገበያዩበት ዋጋ ማሽቆልቆሉን ቀጥሏል። ከሶስት ሳምንታት...

ኤርትራ፤ ከተራራው ጀርባ ጠልቃ የቀረችው ሰሜናዊት ኮኮብ

  ኤርትራ ከባህር በሯ በዘለለ፤ ምድሯ ጥቅም የለውም የሚለው አስተሳሰብ ከኢትዮጲያ ጋር ፍቺ ሳትፈጽም በፊት ገዢ ሃሳብ ሆኖ ነው የኖረው፡፡ በደርግ ጊዜ የኢትዮጲያ ፕሬዝዳንት የነበሩት...

ኢኮኖሚያዊ ህልሙ በፖለቲካ ይጨናገፍ ይሆን?

  በ2013 እ.ኤ.አ. የአዲስ አበባ መስፋፋት የኦሮሚያ ገበሪዎችን አፈናቅሏል በሚል የተጀመረው የጸጥታ አለመረጋጋት ሰባት አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ይህ አመጽ አሁን ያሉትን ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ስልጣን አምጥቶ...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -