Wednesday, May 25, 2022

በአንድ በኩል ያጋደለው የኢትዮጲያ ንግድ

አዳዲሶቹ የፖሊሲ ለውጦች የወጪ እና የገቢ ንግድ ልዩነትን ለማጥበብ ተስፋ ይሆናሉ?

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

ቅድስት አለሙ የ29 አመት የአዲስ አባባ ነጋዴ ናት፡፡ በመንግስት ዩኒቨርስቲ በኢንፎርሜሽን ሳይንስ የትምህርት ክፍል ተመድባ የጀመረችውን ትምህርቷን ነጋዴ ለመሆን በሚል ምክኒያት አቋርጣ ወደ ቤተሰቦቿ አዲስ አበባ ተመለሰች፡፡ ውሳኔውን ስትወስን ግልጽ ያለ እቅድ ኖሯት አይደለም፡፡

“ነጋዴ መሆን እንደምፈልግ ብቻ ነበር የማውቀው፡፡ ምናልባት ባይሳካ እንኳን አንዱ ኮሌጅ ገብቼ ትምህርቴን እቀጥላለው ብዬ በግማሽ ልቤ እያሰብኩ ነበር የመጣሁት፡፡” 

ትላለች ቅድስት ኢትዮኖሚክስ በሱቋ ውስጥ ጎብኝቷት፤ አሁንም አሁንም በሚደወል ስልኳ በተቆራረጠው ቆይታው፡፡

አዲስ አበባ እንደተመለሰች ነገሮች እንዳሰበችው ቀላል አልነበሩም፡፡ ትምህርቷን እንድትማር የሚፈልጉት ቤተሰቦቿ ቀላል አልሆኑም፡፡ በስተመጨረሻ ግን ስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ ቅድስት አለኝ ያቸውን ሃሳብ ለቤተሰቧ አቅርባ፤ እያቅማሙም ቢሆን ተቀበሏት፡፡ የቅድስት ሃሳብ በአውሮፓ እና አሜሪካ የሚገኙ ዘመድ አዝማድና ጓደኞቿን አስተባብራ ኦሪጅናል ጫማዎችን እየገዙ እንዲልኩላት እና እሷ ሱቅ ከፍታ ለአዲስ አበባ ነዋሪ ማቅረብ ነው፡፡

ኢትዮኖሚክስ ቅድስትን ሲያናግራት እጅግ ግዙፍ ለሆኑት ኮርፖሬሽኖች እንኳን በሰልፍ የሚያገኙትን የዶላር ምንዛሬ እንዴት ለማግኘት አስባ እንደጀመረችው ጠይቋት ነበር፡፡

“እሱ ቀላል ነው፡፡ ዘመድ አዝማድ እና ጓደኞቼ በየወሩ ለቤተሰቦቻቸው ዶላር ይልካሉ፡፡ እሱን እዛው ለኔ እቃ ገዝተው ይልኩልኛል፡፡ እኔ እዚህ በቀኑ ባለው ምንዛሬ አስልቼ ቤታቸው ድረስ እየሄድኩ ገንዘባቸውን አደርሳለው፡፡ ዋናው እምነት ነው፡፡ ለነሱም ባንክ ድረስ ከመንከራተት አዳንኳቸው ማለት ነው፡፡”

ትላለች ቅድስት እየሳቀች፡፡

ኢትዮኖሚክስ አገሪቱ የውጪ ምንዛሬ ከምታገኝባቸው መንገዶች አንዱ እነዚህ ቤተሰቦች ለወገኖቻቸው በሚልኩት ገንዘብ በኩል እንደሆነ፤ የሷ ድርጊትም በረጅም ጊዜ የአገሪቱን የውጪ ምንዛሬ ክምችት ሊጎዳ እንደሚችል ታውቅ እንደሆነ ጠይቋት ነበር፡፡ ቅድስት እንዲህ ነበር የመለሰሰችው፡-

“እውነቱን ለመናገር ስለኢኮኖሚክሱ ምናምን ብዙ የማውቀው ነገር የለም፡፡ ግን እኔም አኮ እራሴን መደገፍ አለብኝ፡፡ የውጪ ምንዛሬ ለማግኘት ሰልፉ መከራ ነው፡፡ በዛ ላይ አንዳንድ ጊዜ ያንቺ የጫማ ነው፤ ከኋላ ተሰለፊ ትባላለህ፤ ከዛ የጸጉር ዊግ ለማምጣት የተሰለፈ ሰው ተሳክቶለት ጸጉር ሲያስመጣ ታያለህ፤ ከዛ በሳምንቱ በውጪ በምንዛሬ የሚመጡ መድሃኒቶች እጥረት ተከሰተ ሲባል ትሰማለህ፡፡ ነገሩ ግራ የሚያጋባ ነው፤ ስለዚህ የራስህን መንገድ ፈልገህ እራስህን መቻል አለብህ፡፡”

ኢትዮኖሚክስ የቅድስትን ሁሉንም ወቀሳዎች በግሉ ማረጋገጥ ባይችልም፤ የምንዛሬ ሰልፍን የተመለከቱ ማስረጃዎችን ግን ማገኘት ይቻላል፡፡

የገቢ ንግድ ላይ መሰማራት ትምህርቱን ትቶ ባጣ ቆየኝ ላደረገው እንኳን መግቢያው መንገድ በንጽጽር ቀለል ያለ እንደሆነ የቅድስት ምስክርነት ያሳያል፡፡ ምርቶችን ወደ ውጪ የመላክ ንግድ ላይ መሰማራት ለፈለገ ዜጋ ግን ታሪኩ የተገላቢጦሽ ሊሆን ይችላል፡፡

ዋሲሁን በላይ የሁለተኛ ዲግሪ የኢኮኖሚክስ ምሩቅ ነው፡፡ የኢትዮጲያው ኢኮኖሚስት የሚል የፌስቡክ ገጽ እና ድህረገጽ መስራችም ነው፡፡ ዋና ስራው የማምረቻውን ዘርፍ መቀላቀል ለሚፈልጉ ዜጎች የአዋጪነት፤ እና የአካባቢ ተጽዕኖ ጥናትን ማካሄድና ማማከር ነው፡፡ ኢትዮኖሚክስ ለዚህ ጽሁፍ አናግሮት ነበር፡፡

“የውጪ ንግድ ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ ዜጎች ጉዟቸውን ቀላል ለማድረግ ታስቦ ሲሰራ የነበረ ስራ አልነበረም፡፡ አሁን የተወሰኑ እንቅስቃሴዎች እያየን ነው፡፡ በጥንቃቄ ከተያዙ የተወሰነ ለውጥ ይራል የሚል እምነት አለኝ፡፡” 

ይላል ዋሲሁን፡፡

በኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ትንተና ውስጥ የወጪ እና የገቢ ንግድ አለመመጣጠን የሚለው አገላለጽ ምናልባት እንደሙዚቃ እንዳዝማች ብዙ ጊዜ የተደጋገመ ተብሎ ቢጠቀስ ማጋነን አይሆንም፡፡ ባሳለፍነው 2012 ዓ/ም የተለመደውን እሮሮ የሚመስል ሪፖርት አዳምጠናል፡፡ ግብርና እንደተለመደው ለአገሪቱ ጠቅላላ ምርቱ 46 በመቶውን ድርሻ ተወጥቷል፡፡ የማምረቻው ዘርፍአሁንም የብስጭት ምንጭ ሆኖ ውድድሩን ጨርሷል- 21በመቶ ድርሻ፡፡ የኢትዮጲያ የውጪ ንግድ አጠቃላይ መጠን ሶስት ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ሆኖ ሲያጠናቅቅ፤ የገቢ ንግዱ አጠቃላይ መጠን ወደ 17 ቢሊዮን ዶላር ሆኖ የበጀት አመቱ ተጠናቋል፡፡ ይህ በአንድ በኩል ያጋደለ የንግድ ስርዐት የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ መገለጫ ከሆነ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ተቆጥረዋል፡፡

“የትኛውም አገር አኩል በኩል ማምጣት አይቻልም፤ ቢሆንም ግን በተቻለ መጠን ልዩነቱን ማጥበብ ያስፈልጋል፡፡” 

ይላል ዋሲሁን ስለወጪ እና ገቢ ንግድ አለመመጣጠን በጽንሰ ሃሳብና በልምድ የተደገፈ ማብራሪያ እንዲያደርግለት ኢትዮኖሚክስ ባገኘው ወቅት፡፡

ቀረብ ብሎ ላስተዋለ የኢትዮጲያ መንግስት ይህንን የገቢና ወጪ ንግድ ለማመጣጠን ፍንጭ ጽንሰሃሳብ በሚሰጥ መልኩ ሲፍጨረጨር ከርሟል፡፡ በፋይናንስ ዘርፉ እየተደረጉ ያሉ የፖሊሲ ማሻሻያዎችም ይታያሉ፡፡ የጥቃቅን እና አነስተኛ የብድር ተቋማት ወደባንከነት ማደግ፤ የወጪ ምንዛሬን ገበያ መር ለማድረግ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች መጀመር፤ በውጪ ምንዛሬ ገንዘብ ማስቀመጥ የሚቻልበት ሁኔታ መመቻቸት እና ሌሎችም ከብዙ እንድምታቸው መካከል የወጪ እና የገቢ ንግዱ ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንዲኖራቸው ታስበው የተደረጉ ማሻሻያዎች ናቸው፡፡

የኢትዮጲያ የወጪና ገቢ ንግድ በወፍ በረር 

እ.ኤ.አ. በ2014 የተሰበሰበ መረጃ እንሚያሳየው ኢትዮጲያ በአመቱ 22 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ምርት ስታስገባ፤ ወደውጪ የላከችው ከአምስት ሚሊዮን ዶላር ጥቂት የሚሻገር ነው፡፡ በ2015 እ.ኤ.አ. ኢትዮጲያ 26ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ያስወጣ ምርት ስታስገባ ወደውጪ የላከችው ጥቂት ከ5 ቢሊዮን ተሻግሮ ነበር፡፡ ከ2006 እስከ 2019 እ.ኤ.አ. 374 ቢሊዮን ዶላር በላይ የጠየቀ ምርት ገቢ ሲደረግ ወጪ ምርቶች ያስገኙት ዶላር በጥቂቱ ከ72 ቢሊዮን የተሻገረ ነበር፡፡

በ2017 እ.ኤ.አ. የተሰበሰበ መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጲያ ከምታስገባቸው ምርቶች መካከል አውሮፕላኖች፤ ሄሊኮፕተሮች፤ የነዳጅ ተርባይኖች፤ የታሸጉ መድሃኒቶች፤ ስልኮች፤ እና የጭነት ማመላለሻ መኪናዎች ይገኙባቸዋል፡፡ አገሪቱ ከምትልካቸው ምርቶች መካከል ደግሞ ቡና፤ የቅባት እህሎች፤ እና አበባ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ የምርቶቹ ዝርዝር ልዩነት የንግድ ታሪኩን ቅልብጭ አድርጎ የሚያሳይ ይመስላል፡፡

ይህ ሙሉ የንግድ ፕሮፋይል ለማሳየት በቂ ካልሆነ የሚቀጥለው ዝርዝር ሊረዳ ይችላል፡፡ የምግብ ዘይት፤ ስንዴ፤ የአሳ ምርቶች፤ ሽንኩርት፤ የፍራፍሬ ጭማቂዎች ኢትዮጲያ በዶላር እየገዛች ወደ አገር ውስጥ ታስገባለች፡፡ በ2020 እ.ኤ.አ. ብቻ ኢትዮጲያ ስንዴን ከውጪ ለማስገባት ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ አውጥታለች፡፡
የገበሬው ልዩ ጠባቂ አድርጎ እራሱን ሲያስተዋውቅ በነበረውና ግብርና መር ኢኮኖሚ እከተላለው በሚለው ኢህአዴግ መንግስት ዘመን ይህ መታየቱ ለብዙ የዘርፉ ተማራማሪዎች የትችት ምክኒያት ሆኖ መክረሙ አያከራክርም፡፡

እንደዋሲሁን ማብራሪያ ትልቁ ነገር የወጪ እና የገቢ ንግዱ በንጽጽር የአገሪቱን ጥቅም በሚያስገኝ መርህ ላይ መመስረት መቻሉ ነው ይላል፡፡

 

 “ያስፈለገህን ነገር በሙሉ አታመርትም፤ ያላስፈለገህን ነገር በሙሉ ደግሞ አላመርትም አትልም፡፡ አሜሪካቹ ትሪደንት ማስቲካን አይጠቀሙም፡፡ ነገር ግን ያመርቱታል፡፡ ምክኒያቱም ከሚመረትበት፤ እና ከማጓጓዣ ወጪ አንጻር እንደ ኢትዮጲያ ባሉ አገራት ምርቱ ታዋቂ በመሆኑ አዋጭ ሆኖ አግኝተውታል፡፡ ስለዚህ ያመርቱታል፤ ግን ለአሜሪካኖች አይሸጡትም፡፡ ስላስፈለገህም ታመርታለህ ማለት አይደለም፡፡ በአገር ውስጥ የምታመርተው ዘይትና እና ከቻይና በርካሽ የምታዝገባው ዘይት ጥራቱ ተመሳሳይ ከሆነ ከወጪ ማስገባቱ ይሻለኛል ልትል ትችላለህ፡፡” 

ይላል ዋሁን የምናስገባቸው ምርቶች አይነት በራሳቸው የንግድ አለመመጣጠኑ ችግር ማሳያዎች ይሆናሉ ወይ በሚል ኢትዮኖሚክስ ላቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጥ፡፡

እንደዋሲሁን ትንተና ሁሉም የሚደረጉ የህግ ማሻሻያዎች እጅግ በጣም በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው፡፡ የአለም አቀፉ ባንክና የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በእንግሊዘኛው ወርልድ ባንክና ኢነትረናሽናል ሞኒተሪ ፈንድ የሚሉትን ሁሉ መቀበል ተገቢ አይደለም፡፡ እነዚህ ተቋማት ጫና ከሚያሳድሩበት ሃሳብ አንዱ ብር ከዶላር ጋር ያለውን የምንዛሬ መጠን ማርከስ ነው፡፡ ይህ በራሱ ጥቅም የለውም፡፡ ምንም እንኳን ይህ እርምጃ ሽያጭን ስለሚያበረታታ ብዙ የውጪ ምንዛሬ ለማገኘት ያስችላል የሚል የክርክር ነጥብ ቢኖርም፤ ከውጪ የምናስገባቸውን እቃዎች ብዙ ብር ተጠቅመን ስለምናስገባቸው፤ በአገር ውስጥ ገበያ ዋጋቸው ይጨምራል- ይህም የዋጋ ግሽበትን ያስከትላል፡፡

 

“የገቢና ወጪ ንግድ ለማመጣጠን በሚል አላማ የምትሰራው ስራ አይደለም፡፡ የብዙ እና በጥንቃቄ መያዝ ያለባቸው እርምጃዎች ጥርቅም ነው ነገሩ፡፡”

ዋሲሁን ለኢጥኖሚክስ ያብራራል፡፡

የገቢ ንግድን መተካት እና አገር ውስጥ መመረት በሚችሉ ምርቶች እየተኩ የገቢ ንግድን ዝቅ ለማድረግ መሞከር የማያሻማ እርምጃ ነው፡፡ በወባ፤ በኤች አይቪ እና በሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ዜጎቿ ሲያልቁባት የኖረቸው ኢትዮጲያ እንዴት ደም ደቡብ አፍሪካ ድረስ እየላከች ታስመረምራለች የሚል ትችት ሲደርስባት ቆይቷል፡፡ በኮሮና ዘመን አገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የደም መመርመሪያ ኪቶች ማምረቻ ፋብሪካ ከፍታለች፡፡ ማምረቻውን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ጠ/ሚ አብይ አህመድ ምርቱን ወደ ውጪም ለመላክ እቅድ መኖሩን ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጲያ ውስጥ ከባንክ ስርዐቱ ውጪ ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ እንዳለ ይገመታል፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ባንኮች ወደ 50 ቢሊዮን የሚጠጋውን መሰብሰብ ችለዋል፡፡ ይህ ሁሉም ተሰብስቦ መግባት ቢችል፤ ተጨማሪ ለብድር የሚሆን አቅርቦትን በመጨመር እና ለአገር ውስጥ አምራቾች በማበደር በአንድ በኩል የሚገቡትን ምርቶች መተካት በሌላ በኩል ደግሞ ወደውጪ የሚላኩ ምርቶችን ማበረታት ስለሚችል ጥሩ እርምጃ ሊሆን ይችላል፡፡ የጥቃቅን እና አነስተኛ የብድር ተቋማት ወደባንከነት ማደግም የብድር አቅርቦትን ስለሚጨምር ተመሳሳይ አዎንታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል፡፡

ወደውጪ የሚላኩ ምርቶች አይነትን መጨመር፤ በምርት ሂደት ውስጥ ያለፉ የፋብሪካ ምርቶችን ወደመላክ መሸጋገር የሚሉት ውሃ የሚያነሱ ምክረ ሃሳቦች ሆነው ይቀጥላሉ፡፡

“በባለፉት ጥቂት አመታት የማዕድን ዘርፉን ወደመደበኛ ንግድ ለማምጣት በተደረገው ጥረት ባሳለፍነው አመት 1ቢሊዮን ዶላር እካባቢ ገቢ አስገኝቷል፡፡ ይህ ከዚህ በፊት ያልነበረ ነው፡፡ በደምብ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡” 

ይላል ዋሲሁን ለኢትዮኖሚክስ፡፡

ሊብራላይዜሽን እና ፕራቬታይዜሽን ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ከተከናወኑ ጠቃሚ ምክረ ሃሳቦች ናቸው፡፡ የኢትዮቴሌኮምን የተወሰነ ድርሻ ወደግል ማዘዋወር- ፕራቬታይዜሽን እና ገበያውን ሌሎች እንዲሳተፉበት ማድረግ ሊብራላይዜሽን በጥንቃቄ ከተተገበሩ የራሳቸው ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡

የካፒታል ምርቶችን ማስገባት ልዩ ትኩረትም እንደሚሻ ይነገራል፡፡ እነዚህ ምርቶች አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ በየፋብሪካዎች ወይም እርሻዎች ላይ ተተክለው የሚያመርቷቸው ምርቶችን ወደውጪ መላክ የሚያስችሉ ቁሳቁሶች ናቸው፡፡

“አንዳንድ ጊዜ ሰሊጥ አምርቼ ወደውጪ እየላኩ ነው ግን ዘመናዊ መሳሪያ ስለሌለኝ ምርቱን ባስፈለገው ፍጥነት እና ማድረስ አይቻልም ሲል ትሰማዋለህ ገበሬን፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ ኤክስፖርት የሚያደርግልህን ባለሃብት ቅድሚያ ሰጥተህ ማስተናገድ አለብህ፡፡” 

ይላል ዋሲሁን አምራቾች የካፒታል ምሮቶችን ለማስገባት ያለባቸውን እንቅፋቶች ለኢትዮኮኖሚክስ ሲያብራራ፡፡

የውጪ ምንዛሬን በገበያ ዋጋ እንዲወሰን ማድረግ የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ ዝግጅት እያደረኩበት ነው ካላቸው የፖሊሲ ማሻሻያዎች አንድኛው ነው፡፡ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ሂደቱ ተጠናቆ ምናልባት እስከ ሶስት አመት ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ይህ በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ በብዙ መልኩ ኢኮኖሚው ላይ አዎንታዊ እንድምታ እንደሚኖረው ተገምቷል፡፡ ኢኮኖሚስቶች ግን ጥንቃቄ የሻዋል ይላሉ፡፡

“በአለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ተገፋፍተህ የምታደርገው ከሆነ ከባድ አደጋ አለው፡፡ አንዳንድ የአፍሪካ አገራት የባሰ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ የገቡ አሉ፡፡ በተጨባጭ ጥናት ላይ ተመስርተህ ከወሰንከው እና በጥንቃቄ ከተገበርከው ግን አዎንታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡” ይላል ዋሲሁን፡፡

ቅድስት ግን የውጪ ንግዱ በርትቶ እስኪደርስባት አትጠብቅም፡፡ ገበያ አሪፍ ነው ትላለች፡፡

“እኔ ለፌስቡክም እከፍላለው፡፡ አሜሪካ ያሉ ዘመዶቼ ለፌስቡክ በየወሩ በዶላር ይከፍሉልኛል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ያለ የፌስቡክ ተጠቃሚ ነዋሪ ቢፈልግም ባይፈልግም የኔን ማስታወቂያ ማየቱ አይቀርም፡፡ የሱቄም ቦታ ሰው የሚተላለፍበት ስለሆነ ጎራ የሚል ሰው አላጣም፡፡ በቀን እስከ 100 ስልክ አስተናግዳለው፡፡ ማስታወቂያዬን ከፌስቡክ አይተው ማለት ነው፡፡ ግን ሽያጭ ያው አንድም ሁለትም በቀን አላጣም፡፡ ነጋዴ ለመሆን በመመወሰኔ የሚጸጸተኝ አይደለም፡፡” 

ቅድስት ለኢትዮኖሚክስ እንዳለችው፡፡

የወጪ ንግድን ከገቢ ንግድ ጋር አኩል ማምጣት አይቻልም፤ ላያስፈልግም ይችላል፡፡ አሁን ያለውን ልዩነት ማጥበብ ግን ግዴታ መሆኑ ያስማማል፡፡ የወጪ ንግድ ዘርፍ ውስጥ መሳተፍ የሚፈልጉ ባለሃብቶች ልፋታቸው የቅድስትን ያክል ባይቀል፤ የአሁኑን ያክል መክበድም እንደሌለበት መስማማት ይቻላል፡፡ ሁሉን አቀፍ ፖሊሲ እጅግ በጣም በጥንቃቄ የሚመራ ትግበራ ጠቃሚነቱ አሌ አይባልም፡፡ ይህም ይመስላል፤ የአብይ አህመድ እና ሹመኞቻቸው በአንድ በኩል፤ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና ሹመኞቻቸው በሌላ በኩል የአጭር እና የረጅም ጊዜ ፈተና፡፡

- Advertisement -

4 COMMENTS

  1. ተኪ አማረኛ ቃላት እያሉ በፈረንጅ አፍ ባይፃፍ
    ኢትዮጲያ አይደለም ኢትዮጵያ እንጅ
    በተረፈ በርቱ

  2. I’ve been exploring for a bit for any high-quality articles or blog posts in this kind of area . Exploring in Yahoo I finally stumbled upon this web site. Studying this info So i am happy to exhibit that I have a very excellent uncanny feeling I discovered exactly what I needed. I so much definitely will make sure to don’t omit this website and provides it a glance on a relentless basis.

Leave a Reply to pineal Cancel reply

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -