Monday, April 12, 2021

በእጆ ያለውን ጥሬ 1 ሚልዮን ብር ምን ላይ ቢያውሉት ከፍተኛ ትርፍ ያስገኝሎታል?

Must Read

በአክሱም ከተማ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

  ተቀማጭነቱን በለንደን ከተማ ያደረገውና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ክትትል የሚያደርገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰአታት በፊት ባወጣው ባለ 25...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊል ድርሻ ለቱርክ መንግስት ሊሸጥ ነው

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እስከ...

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሸጠችው ቦንድ ዋጋው እያሽቆለቆለ ነው

ከውጭ ባለሃብቶች 1 ቢልዮን ዶላር ለመበደር በ2007 እ.ኢ.አ ኢትዮጵያ የሸጠችው ቦንድ በአየርላንድ የቦንድ ገበያ ላይ ባለሃብቶቹ እርስ በርስ የሚገበያዩበት...

ከሁሉ በማስቀደም ማድረግ የሌለቦትን ነገር እናካፍሎት። ኢትዮጵያ ውስጥ ለከፍተኛ ኪሳራ ከሚዳርጉ ውሳኔዎች አንዱ ጥሬ ገንዘብን በባንክ ማስቀመጥ ነው። የንግድ ባንክም ሆነ ሌሎች የግል ባንኮች ለደንበኞች የሚከፍሉት ከ7 ፐርሰንት የማይበልጥ ወለድ በአገሪቷ አብዛኛውን ጊዜ በየ አመቱ ከሚመዘገበው እስከ 15 ፐርሰንት የሚደርስ አማካይ የዋጋ ግሽበት መጠን እጅጉን ያነሰ በመሆኑ እርሶ በባንክ ባስቀመጡት ገንዘብ ላይ 7 ፐርሰንት ወለድ ያገኙ ቢመስሎትም እውነታው ግን ከ7 ፐርሰንት በላይ ኪሳራ መዳረጎት ነው። የዋጋ ግሽበት የብርን የመግዛት አቅም የሚሸረሽር ሲሆን 1 መቶ ብር ቁምሳጥኖት ውስጥ ለአንድ አመት ያክል ቢያስቀምጡ የአመቱ መጨረሻ ላይ በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ግሽበት 15 ፐርሰንት ቢሆን ገንዘቦት የዛን ያክል የመግዛት አቅሞ በመሸርሸሩ ከአመት በፊት የነበረው መቶ ብር አሁን ዋጋው 85 ብር ብቻ ይሆናል ማለት ነው። ይህንኑ ገንዘብ ከቁምሳጥኖት አውጥተው ባንክ ውስጥ በ7 ፐርሰንት ወለድ አስቀምጠውት ቢሆን ኖሮ ያቺ ሰባት ፐርሰንት ወለድ በመጠኑም ቢሆን ኪሳራዎን አሻሽላ ከ85 ብር ወደ 92 ብር ከፍ ብታደርገውም ዞሮ ዞሮ ግን ከኪሳራ አይድኑም።

በውጪው አለም ባንኮች የሚሰጡት ወለድ በትንሹ ከአመቱ የዋጋ ግሽበት ጋር እኩል መሆን ያለበት ሲሆን በኢትዮጵያ ግን የባንክ ወለድ የዋጋ ግሽበትን እንኳን አይሸፍንም። ይህን ካልን በሁዋላ 1 ሚልየን ብር ቢኖሮት ምን ቢያደርጉበት ትክክለኛ ትርፍ እንደሚያገኙ ከስር የዘረዘርናቸውን ዘዴዎች ይመልከቱ
1ኛ. ከመሬት ወይም ቤት ጋር የተያያዙ ንብረቶች በየ አመቱ ዋጋቸው ከ20 እስከ 50 ፐርሰንት ድረስ ሲጨምር ይታያል። በተለይም እንደ አዲስ አበባ ባሉት ትላልቅ ከተሞች ካለው የመሬት እጥረት እና የገጠር ህዝብ ወደ ከተማ ፍልሰት ጋር በተያያዘ እየተባባሰ የመጣው እጥረት የመሬት እና የቤትን ዋጋ እጅጉን እያናረው ይገኛል። ይህ የዋጋ ንረት ከከተሞችም አልፎ በየገጠሩ እየታየ ይገኛል። በአሁኑ ሰዐት በአዲስ አበባ ከተማ በ1 ሚልየን ብር ባለ 1 መኝታ ቤት ኮንዶሚንየም በከተማው ዳርቻ አካባቢዎች ላይ መግዛት የሚቻል ሲሆን ባለፉት አመታት በታየው የዋጋ ጭማሪ ላይ በመመስረት ዛሬ በ1 ሚልየን ብር የሚገዙት ኮንዶሚንየም ከአንድ አመት በሁዋላ ከ 1.2 እስከ 1.3 ሚልየን ብር ሊያወጣሎት ይችላል። ይህም በባንክ ከሚገኘው የወለድ መጠን ጋር ሲነፃፀር ከ3 እስከ 4 እጥፍ የበለጠ ይሆናል።

No photo description available.


2ኛ. ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት ከ10 አመት በላይ አገልግለው ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ መኪኖች ላይ ከፍተኛ ቀረጥ ለመጫን በዝግጅት ላይ ይገኛል። ይህም ማለት ከዚህ በፊት በ500 ሺ ብር ይሸጥ የነበረ የ2008 ሞዴል ወይም ከዛ በፊት የተሰራ መኪና በቅርብ በሚጣልበት ቀረጥ ምክንያት ወደ አገር ውስጥ ከገባ በ1 ሚልየን ብር የሚሸጥ ይሆናል ማለት ነው። እርሶ ፈጥነው አሁን በአገር ውስጥ ያለ ያገለገለ መኪና ገዝተው ከሆነ አዲሱን ቀረጥ ተከትሎ በሚመጣው የዋጋ ጭማሪ አትርፈው መኪናዎትን ሊሸጡ ይችላሉ። ይህም የ100 ፐርሰንት ትርፍ ይሆናል ማለት ነው።
3ኛ. ባለፉት 17 ቀናት የኢትዮጵያ ብር ከዶላር ጋር ሲነፃፀር በየቀኑ በ10 የአሜሪካ ሳንቲም እየወረደ ቆይቶ ዛሬ በዋናው የባንክ ዝርዝር 1 የአሜሪካን ዶላር በ31 ብር ከ24 ሳንቲም እየተዘረዘረ ይገኛል። ይህም የኢቶጵያ ብሄራዊ ባንክ ብርን በከፍተኛ ፍጥነት እያወረደው እንደሆነ ያሳያል። በብላክ ማርኬት ላይ የብር የመግዛት አቅም ከዋናው የባንክ ዝርዝር በባሰ መልኩ እየወረደ የሚገኝ ሲሆን በአንድ አመት ውስጥ አንድ ዶላር ከ34 ብር ወደ 41 ብር ከፍ ብሏል። ይህም ዶላርን ከአንድ አመት በፊት ገዝቶ ላቆየ ሰው ከ20 ፐርሰንት በላይ ትርፍን ያስገኛል። ከዚህ በመነሳት አሁን ባለው ዋጋ ዶላር ገዝቶ ማስቀመጥ ከአንድ አመት በሁዋላ እስከ 20 ፐርሰንት ሊደርስ የሚችል ትርፍ ያስገኛል።

No photo description available.


4ኛ. ወርቅ እጅግ ተፈላጊ እና ክቡር ከሆኑ መዐድናት አንዱ ነው። የወርቅ ዋጋ ብዙውን ጊዜ በዓለም ተመሳሳይ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ያደጉት አገራት ኢኮኖሚ ችግር ውስጥ በሚወድቅበት ወቅት ዋጋው ይጨምራል። ለዚህም ምክክንያቱ የአለም ባለሃብቶች የኢኮኖሚ መዋዠቅ በሚያጋጥምበት ወቅት ገንዘባቸውን ከባንኮች፣ ከአክስዮን ገበያ እንዲሁም ከተለያዩ አገራት ገንዘቦች ወደ ወርቅ ሲያዘዋውሩ የወርቅ ፍላጎት የሚጨምር በመሆኑ የወርቅ ዋጋ ይጨምራል። በአሜሪካ ላለፉት 10 አመታት ኢኮኖሚው እያደገ የቆየ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታዩ ያሉ አሃዞች ግን ሌላ የኢኮኖሚ መዋዠቅ ሊያጋጥም እንደሚችል እያመለከቱ ይገኛሉ። በአማካይ አሜሪካ በየ አስር አመቱ ኢኮኖሚዋ መቀዛቀዝ የሚያጋጥመው መሆኑ እና ያለፈው ችግር ካጋጠመ 10 አመት ማለፉ በቅርቡ ይህ ሁኔታ መከሰቱ እንደማይቀር ብዙ ኢኮኖሚስቶች ይናገራሉ። ባለፈው አመት ብቻ በአለም ገበያ የ1 ኪሎ ወርቅ ዋጋ ከ40 ሺ ዶላር ወደ 47 ሺ ዶላር ከፍ ብሏል። ይህም የ17 ፐርሰንት ጭማሪን ያሳያል። የወርቅ ዋጋ በአለም ላይ በሚጨምርበት ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥም ዋጋ በተመሳሳይ መልኩ ስለሚጨምር ገንዘቦን ከባንክ አውጥተው ወርቅ እንዲገዙ ይመከራል።

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

በአክሱም ከተማ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

  ተቀማጭነቱን በለንደን ከተማ ያደረገውና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ክትትል የሚያደርገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰአታት በፊት ባወጣው ባለ 25...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊል ድርሻ ለቱርክ መንግስት ሊሸጥ ነው

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እስከ ግማሽ የሚጠጋ የባለቤትነት ድርሻ ለቱርክ...

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሸጠችው ቦንድ ዋጋው እያሽቆለቆለ ነው

ከውጭ ባለሃብቶች 1 ቢልዮን ዶላር ለመበደር በ2007 እ.ኢ.አ ኢትዮጵያ የሸጠችው ቦንድ በአየርላንድ የቦንድ ገበያ ላይ ባለሃብቶቹ እርስ በርስ የሚገበያዩበት ዋጋ ማሽቆልቆሉን ቀጥሏል። ከሶስት ሳምንታት...

ኤርትራ፤ ከተራራው ጀርባ ጠልቃ የቀረችው ሰሜናዊት ኮኮብ

  ኤርትራ ከባህር በሯ በዘለለ፤ ምድሯ ጥቅም የለውም የሚለው አስተሳሰብ ከኢትዮጲያ ጋር ፍቺ ሳትፈጽም በፊት ገዢ ሃሳብ ሆኖ ነው የኖረው፡፡ በደርግ ጊዜ የኢትዮጲያ ፕሬዝዳንት የነበሩት...

ኢኮኖሚያዊ ህልሙ በፖለቲካ ይጨናገፍ ይሆን?

  በ2013 እ.ኤ.አ. የአዲስ አበባ መስፋፋት የኦሮሚያ ገበሪዎችን አፈናቅሏል በሚል የተጀመረው የጸጥታ አለመረጋጋት ሰባት አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ይህ አመጽ አሁን ያሉትን ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ስልጣን አምጥቶ...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -