Saturday, January 22, 2022

ባለፉት ሶስት ወራት በኢትዮጵያ 70ሺ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች የሳይበር ጥቃት ሰለባ ሆነዋል

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

ተቀማጭነቱን በሩስያ ሞስኮ ከተማ ያደረገው ካስፐርስኪ ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አጠቃላይ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ውስጥ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ወደ 70ሺ የሚሆኑት የኢንተርኔት ጥቃት ሰለባ እንደነበሩ ገልጿል። የፀረ ሳይበር ጥቃት አገልግሎትን የሚሰጠው ካስፐርስኪ በተለያዩ አገራት የተደረጉ የሳይበር ጥቃቶችን በየእለቱ ከመዘገበ በኋላ በዓመት አራት ጊዜ በሚያወጣው ሪፖርቱ ላይ ዝርዝሩን ይፋ ያደርጋል።

የሳይበር ጥቃቶቹ በአብዛኛው የሚመነጩት ከኢትዮጵያ ውጭ ሲሆን አላማቸውም የተጠቃሚዎችን የኢሜል፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራምና የመሳሰሉቱን ፓስወርዶች፤ እንዲሁም የባንክ አካውንት መረጃዎችን፣ የመንግስትና የግል ተቋማት ዲጂታል መረጃዎችን ወ.ዘ.ተ ለመስረቅ ታስቦ ነው። ጥቃት ፈፃሚዎቹ እነዚህን መረጃዎች ለማግኘት የተለያዩ ዘዴዎችን የሚጠቀሙ ሲሆን የስራ ወይም ሌላ አስቸኳይ የሚመስሉ ኢሜሎችን ልከው ተጠቃሚዎች ሊንክ በመጫን ማሳሳቻ ወደሆኑ ድህረገፆች እንዲገቡ በማድረግ፣ አንዳንዴም ሎተሪ ደርስዎታል ወይም ስሞትን እጣ ውስጥ ያስገቡ በሚል የተጠቃሚዎችን መረጃ መሰብሰብ ብሎም በቪድዮና በተለያዩ ሰነዶች መልክ የተዘጋጁ ቫይረሶችን ወደ ኮምፒተራቸው ወይም ስልካቸው እንዲጭኑ ማታለል ይገኙበታል።

በተለይም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከመጣ ጀምሮ ሕብረተሰቡ ስለ በሽታው ለማወቅ ያለውን ጉጉት ከግምት በማስገባት ስለ ኮቪድ መረጃ የሚያስተላልፉ በማስመሰል ሊንክ እንዲጫኑ ወይም ሰነዶችን ወደ ኮምፒተሮችና ስልኮች እንዲጭኑ የሚገፋፉ የተለያዩ የኢሜል መልዕክቶች ወደ ተጠቃሚዎች ተልከዋል። ይህንን ተከትሎም እስከ 70ሺ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በነዚህ መልዕክቶች እንደተታለሉና የግልና የመንግስት ተቋማት መረጃዎችም የመሰረቅ ዕድል እንደነበራቸው ሪፖርቱ ያሳያል።

የሳይበር ጥቃት ፈፃሚዎች አብዛኛውን ጊዜ በቀድሞ የሶቭየት ሕብረት ግዛቶች ውስጥ የመሸጉ ሲሆን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን እንደ ቻይናና ህንድ ያሉ የእስያ አገራት እንዲሁም የመካከለኛ ምስራቋ ኢራን፣ ብሎም ናይጄርያና ጋናን የመሳሰሉ የአፍሪካ አገራት በተወሰነ መልኩ ለጥቃት ፈፃሚዎቹ መሸሸግያ እየሆኑ መጥተዋል። እነዚህ የሳይበር ሌቦች በጅምላ የሚያገኟቸውን የግለሰቦችና የተቋማት ፓስወርዶች፣ የኤቲኤም፣ የባንክ ደብተርና የፓስፖርት ቁጥሮች ወ.ዘ.ተ ለሶስተኛ ወገን አሳልፈው የሚሸጡ ሲሆን ይህን መረጃ ስራዬ ብለው የሚገዙት እነዚህ ሶስተኛ ወገኖችም ለተለያዩ ወንጀሎች እንደሚጠቀሙበት ይነገራል።

የካስፐርስኪ ሪፖርት እንደሚያሳየው ደቡብ አፍሪካ ከ600 መቶ ሺ በላይ ነዋሪዎቿ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ለሳይበር ጥቃት በመዳረጋቸው ከአፍሪካ ቀዳሚውን ስፍራ ስትይዝ ኬንያና ግብፅም በበኩላቸው እያንዳንዳቸው ከ500 ሺ በላይ የሚሆኑት ዜጎቻቸው የጥቃቱ ሰለባ ሆነውባቸዋል። ኢትዮኖሚክስ

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -