Saturday, January 22, 2022

የኮሮና ቫይረስ የነዳጅ ዋጋን ቁልቁል ሊለቀው ይችላል! ዓለም እንቅስቃሴዋ እየቀዘቀዘ መጥቷል

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የንግድና ኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎች በተለያዩ የዓለም ክፍላት በተለይም በቻይና በመቀዛቀዙ በዓለም ገበያ ላይ የነዳጅ ፍላጎት እንዲቀንስ አስገድዶታል፡፡ ይህ የፍላጎት መቀነስ ያሳሰባት ነዳጅ በማውጣት ከዓለም ሦስተኛ ደረጃን የያዘችው ሳውዲ አረብያ ከጥቂት አመታት በፊት በነዳጅ ማውጣት የበለጠቻት ሩስያን “የዋጋ መውረድን ለመግታት ተባብረን የነዳጅ አቅርቦትን እንቀንስ” የሚል ጥያቄ ባሳለፍነው አርብ በኦስትርያ ቭየና በተካሄደ ስብሰባ ላይ ብታቀርብም ሩስያ ይህንን ሃሳብ ባለመቀበሏ ሳውዲንና ሌሎች የነዳጅ ባለሃብት አገራትን ስጋት ውስጥ ጥሏል፡፡ በሳውዲና የሩስያ ሚንስቴሮች መካከል የተደረገውን ድርድር መጠናቀቅ ተከትሎም የዓለም የነዳጅ ዋጋ በፍጥነት እየወረደ ይገኛል፡፡

Image may contain: sky, outdoor and nature

ከሁለት ወራት በፊት በ68 ዶላር ሲሸጥ የነበረው አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዛሬ በ45 ዶላር እየተሸጠ ነው፡፡ ሆኖም ገና በመስፋፋት ላይ ያለው የኮሮና ቫይረስ በየ እለቱ አዳዲስ አገራትን እየበከለ ከቤጂንግ እስከ ሚላን ብሎም እስከ ኒውዮርክ ድረስ በንግድ፣ በቱሪዝምና በኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎች ላይ እያሳደረ ያለው ከፍተኛ ተፅዕኖ በመባባሱ የዓለም ኢኮኖሚ ወደባሰ ቀውስ ሊያመራ ሲችል የነዳጅ ዋጋም ከዚህ የባሰ የዋጋ መውረድ ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ ቫይረሱ እያስከተለ ያለው ችግር በዚህ ደረጃ ከቀጠለ አብዛኛውን ገቢያቸውን ነዳጅ በመሸጥ የሚያገኙ እንደ ሳውዲ፣ ክዌት፣ ኢራቅ፣ ናይጄርያ፣ አንጎላና ቬንዝዌላ የመሳሰሉት አገራት የውጭ ምንዛሬ ገብያቸው መመናመኑ አይቀሬ ነው፡፡

በእርግጥ የኮሮና ቫይረስ ያባብሰው እንጂ የነዳጅ ዋጋ ቀስ በቀስ መውረድ ከጀመረ አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ለዚህም ዋነኛዋ ምክንያት አሜሪካ ስትሆን የሁለተኛው የአለም ጦርነት ፍፃሜን ተከትሎ የዓለማችን ሃያሏ አገር ሆና የቆየችው አሜሪካ ከውጭ አገራት ነዳጅ በመሸመት ለአስርት አመታት በአለም ቀዳሚዋ ሆና ኖራለች፡፡ ነገር ግን አሜሪካ ባለፉት ጥቂት አመታት እንደ ቴክሳስና ኖርዝ ዳኮታ ካሉት ግዛቶቿ እያወጣች ያለችው ነዳጅ ሳውዲንና ሩስያን በልጣ የዓለም አንደኛ ነዳጅ አውጪ አገር እንድትሆን አስችሏታል፡፡ በአብዛኛው በግል ኩባንያዎች ይዞታ ካሉ ጉድጓዶች የሚገኘው የአሜሪካ ነዳጅ ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በከፍተኛ መጠን መቅረቡን ተከትሎ ዋጋ እንዲቀንስ ተፅዕኖን ሲያደርስ ታይቷል፡፡

No photo description available.

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም በፀሃይ ብርሃን የሚሰሩ የሃይል ማመንጫዎች በአንዳንድ የዓለማችን አካባቢዎች እየተስፋፉ የመጡ ሲሆን እንደ ሸንዘን በተባሉት የቻይና ታላላቅ ከተሞች ደግሞ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ብቻ በስራ ላይ እንዲውሉ የሚደነግጉ ህጎች ወጥተዋል፡፡ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በሚቀጥሉት 20 አመታት በምዕራቡ ዓለም ከተሞች ከሚታዩት ተሽከርካሪዎች ግማሾቹ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰሩ ይሆናሉ፡፡ ከነዚህ 20 አመታት በኋላም ባለፈው ክፍለ ዘመን ከአመት ወደ አመት ሲጨምር የኖረው የዓለም የነዳጅ ፍጆታ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በቋሚነት ማሽቆልቆል እንደሚጀምር ይጠበቃል፡፡

ታድያ በዚህ ሁኔታ ላይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ድንገት መከሰቱ የነዳጅ ባለሃብት አገራት አብረው በመስራትና አቅርቦትን በመቀነስ በብዙ ጥረት የነዳጅ ዋጋ ቁልቁል እንዳይወርድ አስደግፈውለት የነበረውን ታኮ ከጥቅም ውጪ ያደረገው ይመስላል፡፡ አብዛኛዎቹን ዜጎቿን ከነዳጅ በሚገኝ ገቢ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ከፍተኛ ደሞዝ እየከፈለች የምታሰራው ሳውዲ ገቢዋ ሲቀንስ ሊያስከትል የሚችለውን የበጀት መቃወስ በመፍራት የዋጋ መቀነስን ለማካካስ ወደ ውጪ የምትልከውን የነዳጅ መጠን ሰሞኑን ጨምራለች፡፡ ሩስያም በበኩሏ የነዳጅ አቅርቦቷን እንደምትጨምር የሚጠበቅ ሲሆን ሌሎች የአረብ አገራትም ይህንን መከተላቸው አይቀሬ በመሆኑ ዓለም በነዳጅ እየተጥለቀለቀች ዋጋም ቁልቁል መውረዱን ይቀጥላል ተብሎ ይገመታል፡፡ ታሪካዊ የዋጋ አሃዞችን በመመልከት የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ እስከ 26 ዶላር የመውረድ እድሉም የሰፋ ነው፡፡
የነዳጅ ዋጋ ሲያሽቆለቁል አብዛኛው ገቢያቸውን ለውጭ ገበያ በማቅረብ የሚያገኙት አገራት የኢኮኖሚ ቀውስ እንደሚያጋጥማምቸውና ተያይዞም የፖለቲካ አለመረጋጋት እንደሚከተል ከታሪክ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተለይም እንደ ደቡብ ሱዳን፣ ናይጄርያና ኢኳቶርያል ጊኒ የመሳሰሉ የዋጋ መቀነስን ለማካካስ በተለያዩ ምክንያቶች በቀላሉ አቅርቦትን የመጨመር አቅም የሌላቸው አገራት ዋጋ በቀነሰ ቁጥር አስጊ ወደሆነ አለመረጋጋት የማምራት እድላቸው እየሰፋ ይሄዳል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ፓኪስታን፣ ሕንድ፣ ባንግላዲሽ፣ ብራዚልና ሌሎች ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላቸውና ሙሉ በሙሉ ነዳጅን ከውጭ የሚያስገቡ አገራት በአንፃሩ ይጠቀማሉ፡፡ በተለይም የውጭ ምንዛሬ እጥረት ያለባቸው እንደ ኢትዮጵያና ፓኪስታን ያሉት ታዳጊ አገራት ለነዳጅ ግዢ ከሚያውሉት ከፍተኛ የዶላር መጠን መቀነስ ተጠቃሚ ሲሆኑ እንደ ሕንድና ቱርክ ያሉት ደግሞ በአረብ አገራት በሚከሰተው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ወደነዚሁ አገራት በሚልኩት ከፍተኛ መጠን ያለው ምርት ላይ ተፅዕኖ ስለምያሳድር የነዳጅ ዋጋ መቀነስ በቀጥታ ቢጠቅማቸውም ዞሮ ዞሮ ግን የጉዳቱ ተካፋይ መሆናቸው አይቀርም፡፡

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -