Saturday, January 22, 2022

ብዙ ትኩረት ያልተሰጠው የድሬዳዋ ፕሮጀክት ጥቅሙ ከህዳሴ ግድብ አይተናነስም

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

ላለፉት ስምንት ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ትኩረትን አግኝቶ የቆየ ዋነኛ ጉዳይ ቢኖር የህዳሴ ግድብ ነው፡፡ ሆኖም ብዙ ትኩረት ያልተሰጠው በድሬዳዋ ከተማ አራት ቢልየን ዶላር በሚጠጋ ወጪ እየተገነባ ያለ አንድ ግዙፍ የእህል ማዳበርያ ፋብሪካ ግድቡን የሚያስንቅ ጥቅም ለኢትዮጵያ ይዞ ሳይመጣ አይቀርም፡፡

የኢትዮጵያ ገበሬዎች ለአንድ ሄክታር የስንዴ እርሻ የሚጠቀሙት የማዳበርያ መጠን በአማካይ 57 ኪሎግራም ለበቆሎ እርሻ ደግሞ 34 ኪሎግራም ነው። ይህ ዝቅተኛ የማዳበርያ አጠቃቀም ከ40 ሚልዮን በላይ ገበሬዎች ባሉባት አገር ከዓመት ዓመት የስንዴ እና የሌሎች ግብርና ውጤቶች እጥረት እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። በአንፃሩ በአውሮፓ ሃገራት የሚገኙ ገበሬዎች በአማካይ ለአንድ ሄክታር የስንዴ ምርት 150 ኪሎግራም ማዳበርያ እና ለበቆሎ ደግሞ እስከ 300 ኪሎ ይጠቀማሉ። ይህ የአውሮፓውያን ከፍተኛ የማዳበርያ አጠቃቀም ከኢትዮጵያ በሶስት እጥፍ የሚበልጥ በመሆኑ አጅግ በጣም ጥቂት ከሆኑ ገበሬዎች ከፍተኛ የሆነ ምርት አንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

እስከ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ለጥቅም የሚውለው ማዳበርያ ወደ አገር ውስጥ የሚገባው ከውጭ ሲሆን እስከ ጅቡቲ ድረስ በመርከብ ተጉዞ ወደብ ከደረሰ በሁዋላ በአገር አቋራጭ የጭነት መኪኖች ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ይሰራጫል። ለማዳበርያ ግዢ መንግስት በዓመት ከ500 ሚልዮን ዶላር በላይ አንደሚያወጣ አሃዞች ያመለክታሉ። ሆኖም ከዚህ ገንዘብ ግማሽ የሚሆነው ማዳበርያውን በመርከብ እና ጭነት መኪኖች ለማጓጓዝ ይውላል። ይህ ከፍተኛ የማጓጓዣ ወጪ ኢትዮጵያ ካለባት የዶላር እጥረት ጋር ተደምሮ በቂ ማዳበርያ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ ምክንያት ሆኗል።

Image may contain: mountain, sky, grass, cloud, outdoor and nature

ይህን ችግር በከፊሉም ቢሆን በዘላቂነት ሊፈታ የሚችል አንድ ትልቅ ፕሮጀክት በግምባታ ላይ ይገኛል። ከ3 አመት በፊት የሞሮኮው የማዳበርያ አምራች ኩባንያ ኦሲፒ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በገባው ስምምነት መሰረት በ3.7 ቢልዮን ዶላር ወጪ በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ የማዳበርያ ፋብሪካ በመገምባት ላይ ይገኛል። ይህ ግንባታ በሁለት ዙር የሚጠናቀቅ ሲሆን በአጠቃላይ እስከ 3.8 ሚልዮን ቶን ማዳበርያ የማምረት አቅም ይኖረዋል። ኦሲፒ እና የኢትዮጵያ መንግስት በፋብሪካው ላይ ድርሻ የሚኖራቸው ሲሆን ማደበርያውን ለማምረት የሚያስፈልጉ 3 ንጥረ ነገሮች ፖታሽ፣ ፎስፌት፣ አና ናይትሮጅን ናቸው። ከአመታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ በአፋር ክልል የተገኘው የፖታሽ ማዓድን የፋብሪካውን የፖታሽ ፍጆታ ሙሉ በሙሉ የመሸፈን ብቃት አለው። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለፋብሪካው ናይትሮጅን የምታቀርብ ይሆናል። ሶስተኛው ለማዳበርያ ምርት ተፈላጊ ንጥረ ነገር ፎስፌት ሲሆን ኦሲፒ በቀጥታ ከሞሮኮ በበመርከብ አንደሚያስመጣ ገልጿል። ጅቡቲም ይህንን ፎስፌት ለማስተናገድ ወደቧን ለማደስ ተስማምታለች።

ለፋብሪካው የሚያስፈልጉት አነዚህ ሶስት ማዓድናት በዚህ መልኩ መቅረባቸው በራሱ ልዩ ጠቀሜታ አለው። አንደሚታወቀው በኢትዮጵያ በርካታ የኢንዱስትሪ መንደሮች ተገንብተው ለኢንቨስተሮች የተላለፉ ቢሆንም ለፋብሪካዎቹ የሚያስፈልገው አብዛኛው ጥሬ እቃ የሚገባው ከውጪ በመሆኑ ባጋጠመው ከፍተኛ የዶላር እጥረት ምክንያት ብዙ ፋብሪካዎች ስራ ለማቆም ወይም ለመቀነስ ተገደዋል። ነገር ግን ለዚህ የማዳበርያ ፋብሪካ የሚቀርቡት 3 መዓድናት በአገር ውስጥ የሚገኙ እና ሶስተኛው ደግሞ ከሞሮኮ የሚመጣ መሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት እና ሞሮኳዊው ኦሲፒ ከውጪ በሚመጡ ጥሬ እቃዎችላይ ጥገኛ እንዳይሆኑ ይረዳቸዋል።

ሆኖም ይህ ፋብሪካ በኢትዮጵያ ያለውን የማዳበርያ እጥረት የማቃለል ብሎም ሙሉ ለሙሉ ችግሩን የመፍታት አቅም ቢኖረውም የሚመረተው ማዳበርያ ገበሬዎች ጋር ደርሶ የተፈለገውን ያክል ለውጥ ለማምጣት የተለያዩ መሰናክሎች መጋረጣቸው አይቀሬ ነው። ከነዚህም አንዱ እና ዋነኛው በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ ችግር ነው። በአገሪቱ በተለያዩ ክፍሎች እየታዩ ያሉት ግጭቶች ገበሬው ምርቱን ወደ ከተሞች እንዳያቀርብ ሲያስተጓጉሉት ቆይተዋል። የመንገዶች መዘጋት እና የጭነቶች በየቦታው መዘረፍ ማዳበርያውን በቀጥታ ለገበሬዎች ማድረስ እንዳይቻል ምክንያት ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም ላለፉት 15 አመታት ሲሰራበት የነበረው የማዳበርያ ስርጭት መዋቅር በሙስና የተጨማለቀ እና በፖለቲካ አባልነት ላይ ተመስርቶ የነበረ ሲሆን ይህ መዋቅር ተሻሽሎ ቢሮክራሲ ባልበዛበት መልኩ ለገበሬዎች የሚቀርብ ካልሆነ ፋብሪካው የሚያቀርበው ከበቂ በላይ የማዳበርያ ምርት በአግባቡ ጥቅም ላይ ሳይውል ሊቀር ይችላል። ለዚህ መፍትሄ ከሚሆኑት አንዱ የማዳበርያ ስርጭትን ከምንግስት እጅ ወደ ግል ነጋዴዎች ማዘዋወር ሲሆን ሆኖም መንግስት ሙሉ ለሙሉ እራሱን ከስርጭቱ ከማግለል ይልቅ የማዳበርያ ንግድ በተወሰኑ ነጋዴዎች እጅ አንዳይወድቅ በህግ ላይ የተመሰረተ ቁጥጥር ማድረግ አንዲሁም በተወሰነ መልኩ ለገበሬዎች ድጎማ በማድረግ ቢሳተፍ የአገሪቱ የግብርና ዘርፍ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ይረዳል።

ሌላው ለወደፊት ሊያጋጥም የሚችል መሰናክል ሞሮኮ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ነው። ከላይ እንደተገለፀው ለድሬዳዋው ፋብሪካ እንደ ጥሬ እቃነት ከሚያገለግሉት 3 መዓድናት ውስጥ አንዱ የሆነው ፎስፌት ከሞሮኮ በቀጥታ የሚመጣ ይሆናል። በዓለም ላይ ካለው የፎስፌት ሃብት ውስጥ ከ70 ፐርሰንት በላይ የሚሆነው በሞሮኮ የሚገኝ ነው። ታድያ ሞሮኮ ካላት ከዚህ ሃብት ውስጥ የተወሰነው በምዕራባዊ ሰሃራ ሪፐብሊክ ሲሆን ይህች አነስተኛ አገር በሞሮኮ በሃይል እየተገዛሁ ነው በሚል ለነፃነቷ ስትታገል ቆይታለች። ከቅርብ ጊዝያት ወዲህ ደግሞ ወደ ትጥቅ ትግል እስከ መግባት ሊደርሱ አንደሚችሉ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የተደራጁ ኣካላት በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ። ከዚህም በመነሳት በአሜሪካ የሚገኝ አንድ የማዳበርያ ፋብሪካ ከዚህ በፊት ከሞሮኮ ሲገዛ የነበረውን ፎስፌት አቋርጦ ሌላ አቅራቢ ለመፈለግ ተገዷል። እንደዚህ አይነት የፖለቲካ ቀውስ ከሞሮኮ የሚመጣውን የፎስፌት አቅርቦት እንዳያስተጓጉለው የኢትዮጵያ መንግስት ቀድሞ አማራጭ በማስቀመጥ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል።

በተመሳሳይ መልኩ ኢትዮጵያ ለፋብሪካው የምታቀርበው የፖታሽ መዓድን የሚገኘው በአፋር ክልል ወደ ኤርትራ ድንበር አቅራብያ በመሆኑ በአፋር ክልል እና በፌደራል መንግስት መካከል በአግባቡ ስምምነት ሊደረስ እና አንዲሁም የአፋር ክልል ነዋሪዎች በአካባቢው ከሚወጣው ማዓድን ተገቢውን ጥቅም የሚያገኙበት ሁኔታ ከአሁኑ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

አሁን በግንባታ ላይ ያለው ፋብሪካ በሚቀጥሉት 3 አመታት የመጀመርያው ዙር ተጠናቆ ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ሁለተኛው ዙር ተጠናቆ በአጠቃላይ ፋብሪካው የሚያመርተው 3.8 ሚልዮን ቶን ማዳበርያ ኢትዮጵያ ለእህል ምርት ከሚያስፈልጋት የማዳበርያ መጠን ከሁለት እጥፍ በላይ ሲሆን ቀሪው ደግሞ ሌሎች የማዳበርያ ውድነት ለሚያሰቃያቸው የጎረቤት አገራት በመሸጥ ከፍተኛ የዶላር ገቢ ያስገኛል የሚል ተስፋ አለ።

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -