Monday, April 12, 2021

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን እርዳታ በከፊል አገደች

Must Read

በአክሱም ከተማ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

  ተቀማጭነቱን በለንደን ከተማ ያደረገውና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ክትትል የሚያደርገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰአታት በፊት ባወጣው ባለ 25...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊል ድርሻ ለቱርክ መንግስት ሊሸጥ ነው

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እስከ...

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሸጠችው ቦንድ ዋጋው እያሽቆለቆለ ነው

ከውጭ ባለሃብቶች 1 ቢልዮን ዶላር ለመበደር በ2007 እ.ኢ.አ ኢትዮጵያ የሸጠችው ቦንድ በአየርላንድ የቦንድ ገበያ ላይ ባለሃብቶቹ እርስ በርስ የሚገበያዩበት...

ፎረን ፖሊሲ የተባለውና በአሜሪካ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው በዋሺንግተን ዲሲ የሚታተም መፅሄት ዛሬ እንደዘገበው የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ማይክ ፖምፔዮ አገራቸው ለኢትዮጵያ ከምትሰጠው ዓመታዊ የገንዘብ እርዳታ ላይ እስከ 130 ሚልዮን ዶላር የሚሆነው እንዲታገድ ማፅደቃቸውን ዘግቧል። ከሁለት ቀናት በፊት በሱዳን ተገኝተው ከአገሪቱ መሪዎች ጋር የተወያዩት ማይክ ፖምፔዮ ካርቱም በነበሩበት ወቅት በተመሳሳይ ሰዓት በከተማዋ ከተገኙት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር ይገናኛሉ የሚል ግምት የነበረ ቢሆንም ሳይገናኙ መቅረታቸውን ኢትዮኖሚክስ ለመረዳት ችሏል።

ባሳለፍነው የ2019 የፈረንጆች ዓመት 824 ሚልዮን ዶላር በእርዳታ መልክ ለኢትዮጵያ የሰጠችው አሜሪካ ከዚህኛው ዓመት ላይ 130 ሚልዮን ዶላር ለመቀነስ የወሰነችው ከሱዳንና ከግብፅ ጋር ስምምነት ላይ ሳይደረስ የህዳሴ ግድብ ሙሌት መጀመሩን ተከትሎ ነው። እገዳው በአብዛኛው የሚደረገው ለፀረ ሽብርና ፀጥታ ነክ፣ እንዲሁም ህገ ወጥ የሰው ዝውውርን ለመከላከል በሚውለው የእርዳታ ገንዘብ ላይ ሲሆን የሰብአዊ እርዳታን ማለትም ረሃብን፣ ድንገተኛ አደጋንና እንደ ኤች አይ ቪ ያሉ በሽታዎችን ለማዋጋት የሚውለውን አይመለከትም።

የዛሬ ዘጠኝ ዓመት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መሠረት ከተጣሉበት ቀን ጀምሮ ኢትዮጵያ ይዛው የነበረውን ሶስተኛ አካልን ለድርድር ያለማስገባት አቋሟን ቀይራ ባሳለፍነው የካቲት ወር ወደ ዋሽንግተን ለድርድር ተወካዮቿን የላከች ቢሆንም በዶናልድ ትራምፕ የተመረጡት አሜሪካዊ አደራዳሪና የዓለም ባንክ በድርድሩ ወቅት ሙሉ ገለልተኝነት አላሳዩም በሚል የኢትዮጵያ ተወካዮች ድርድሩን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የአሜሪካ ግምዣ ቤት ዋና ተጠሪና የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቅርብ ወዳጅ የሆኑት ከአደራዳሪዎቹ አንዱ ስቲቭ ሚዩንሽን ከግብፅና ከሱዳን ጋር ዘላቂ ስምምነት ከመደረሱ በፊት ኢትዮጵያ የግድቡን የውሃ ሙሌት መጀመር የለባትም የሚሉ ማስጠንቀቅያ አዘል መልዕክቶችን በተደጋጋሚ ሲልኩ ታይተው ነበር።

ይሁን እንጂ የአሜሪካው ፕሬዝዳንትና አደራዳሪው ስቲቭ ምዩንሽን ካገራቸው የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለግብፅ አድልታችኋል የሚል ትችት በወቅቱ ተሰንዝሮባቸው የነበረ ሲሆን በርካታ የአሜሪካ ፖለቲከኞችም ፕሬዝዳንቱ በመጪው ምርጫ ያላቸውን እድል ለማስፋት ካላቸው ፍላጎት በመነሳት ኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን ፍትሃዊነት የጎደለው ተግባር እንዲያቆሙ ተጠይቀዋል። ለግብፅ አድልኦን አሳይቷል በሚል የድርድር ሂደቱን ከተቃወሙት አሜሪካውያን ውስጥም 7 የሚሆኑ የቀድሞ ዲፕሎማቶችና አምባሳደሮች፤ እንዲሁም በተወካዮች ምክር ቤት የጥቁር አሜሪካውያን አባላት ማህበር ይገኙበታል። በተጨማሪም ስቴት ዲፓርትመንት የተባለው የውጭ ጉዳይ መስራቤት በድርድሩ ላይ እንዲሳተፍ በፕሬዝዳንት ትራምፕ አለመጋበዙም ሆነ በሂደቱ ላይ በቂ መረጃ እንዲያገኝ አለመደረጉ በመስራቤቱ የሚሰሩ በርካታ ባለ ልምድ ዲፕሎማቶችን ቅር ሲያሰኝ እርዳታ ለማገድ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ጥረት እስከ ማድረግ ደርሰው እንደነበርም ተሰምቷል።

በህዳሴ ግድብ ጉዳይ በዋይት ሃውስና በተቀሩት የመንግስት ተቋማት መካከል ያለው የሃሳብ ልዩነት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢትዮጵያ ላይ ተጨማሪ የእርዳታ እገዳ ለማድረግ ቢሞክሩ እንኳን ምክር ቤቱ ውድቅ እንደሚያደርግባቸው የሚያመላክት ነው። ስለዚህም ዛሬ ይፋ ከሆነው እገዳ ባለፈ ፕሬዝዳንቱ ኢትዮጵያ ላይ ተጨማሪ ግፊት ለማድረግ ከፈለጉ እንደ የዓለም ባንክ ያሉ ተቋማትን ተጠቅመው በእጅ አዙር ማስፈራራት ወይም ደግሞ የምክር ቤቱን ፈቃድ የማይጠይቁ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሜሪካ የሚያደርጋቸውን በረራዎች ማስቆም፣ አሜሪካውያን ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሄዱ ማስፈራራትና የመሳሰሉትን ዘዴዎች እስከመጠቀም ሊደርሱ ይችላሉ።

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

በአክሱም ከተማ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

  ተቀማጭነቱን በለንደን ከተማ ያደረገውና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ክትትል የሚያደርገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰአታት በፊት ባወጣው ባለ 25...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊል ድርሻ ለቱርክ መንግስት ሊሸጥ ነው

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እስከ ግማሽ የሚጠጋ የባለቤትነት ድርሻ ለቱርክ...

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሸጠችው ቦንድ ዋጋው እያሽቆለቆለ ነው

ከውጭ ባለሃብቶች 1 ቢልዮን ዶላር ለመበደር በ2007 እ.ኢ.አ ኢትዮጵያ የሸጠችው ቦንድ በአየርላንድ የቦንድ ገበያ ላይ ባለሃብቶቹ እርስ በርስ የሚገበያዩበት ዋጋ ማሽቆልቆሉን ቀጥሏል። ከሶስት ሳምንታት...

ኤርትራ፤ ከተራራው ጀርባ ጠልቃ የቀረችው ሰሜናዊት ኮኮብ

  ኤርትራ ከባህር በሯ በዘለለ፤ ምድሯ ጥቅም የለውም የሚለው አስተሳሰብ ከኢትዮጲያ ጋር ፍቺ ሳትፈጽም በፊት ገዢ ሃሳብ ሆኖ ነው የኖረው፡፡ በደርግ ጊዜ የኢትዮጲያ ፕሬዝዳንት የነበሩት...

ኢኮኖሚያዊ ህልሙ በፖለቲካ ይጨናገፍ ይሆን?

  በ2013 እ.ኤ.አ. የአዲስ አበባ መስፋፋት የኦሮሚያ ገበሪዎችን አፈናቅሏል በሚል የተጀመረው የጸጥታ አለመረጋጋት ሰባት አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ይህ አመጽ አሁን ያሉትን ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ስልጣን አምጥቶ...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -