Monday, April 12, 2021

አሜሪካ ለ27 ዓመታት ሱዳን ላይ ጥላ የቆየችውን ማእቀብ ለማንሳት ተቃርባለች

Must Read

በአክሱም ከተማ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

  ተቀማጭነቱን በለንደን ከተማ ያደረገውና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ክትትል የሚያደርገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰአታት በፊት ባወጣው ባለ 25...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊል ድርሻ ለቱርክ መንግስት ሊሸጥ ነው

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እስከ...

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሸጠችው ቦንድ ዋጋው እያሽቆለቆለ ነው

ከውጭ ባለሃብቶች 1 ቢልዮን ዶላር ለመበደር በ2007 እ.ኢ.አ ኢትዮጵያ የሸጠችው ቦንድ በአየርላንድ የቦንድ ገበያ ላይ ባለሃብቶቹ እርስ በርስ የሚገበያዩበት...

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ቢሮ ዋና ፀሃፊ ማይክ ፖምፔዮ በትላንትናው እለት በዋሺንግተን ዲሲ ባደረጉት ንግግር አሜሪካ በሱዳን ላይ ላለፉት 27 ዓመታት ጥላው የቆየችው የኢኮኖሚ ማዕቀብ በመጭዎቹ ጥቂት ሳምንታት ሊነሳ እንደሚችል ገልፀዋል፡፡ ማይክ ፖምፔዮ ይህንን የተናገሩት ትላንትና ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብዱላህ ሃምዶክ ጋር በስልክ ከተወያዩ በኋላ ነው፡፡ አሜሪካ ማዕቀቡን ለማንሳት እንቅስቃሴ የጀመረችው ለረዥም አመታት ሱዳንን ሲገዙ የነበሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር ከስልጣን መውረድን ተከትሎ ሲሆን ከማዕቀቡ መነሳት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉ ከአሜሪካ በኩል በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡

ከነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ የዛሬ 22 ዓመት በኬንያና በታንዛንያ በሚገኙት የአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ አልቃይዳ የተባለው አሸባሪ ቡድን በፈፀመውና 224 ሰዎች በተገደሉበት ጥቃት ላይ የሱዳን ተባባሪነት ነበረበት የሚል እምነት በአሜሪካውያን ዘንድ በመኖሩ ሱዳን ለሟቾቹ አሜሪካውያን ቤተሰቦች ካሳ መክፈል አለባት የሚል ነው፡፡ በወቅቱ የአልቃይዳ መሪና መስራች የነበረው ኦሳማ ቢንላደን በሱዳን ነዋሪነት በመነሳት በኤምባሲዎቹ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እቅድ በሚያወጣበት ጊዜ የሱዳን መንግስት እውቅና እንደነበር በመጥቀስ አሜሪካ ሱዳንን ስትከስ ኖራለች፡፡

የሱዳን የሽግግር መንግስት በአሁኑ ሰዓት በአገሪቱ በተከሰተው ከፍተኛ የኢኮኖሚ መዋዠቅ ምክንያት ትልቅ አጣብቂኝ ውስጥ የገባ ሲሆን አሜሪካ ማዕቀቡን እንድታነሳ ላለፈው 1 ዓመት በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ በሚገነባው የሕዳሴ ግድብ ላይ ሱዳን ከለት ወደለት እያሳየች የመጣችው ከቀድሞ ለየት ያለ አቋም በተወሰነ መልኩ ከአሜሪካ እየተደረገባት ካለ ከፍተኛ ጫና ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይገመታል፡፡ ሆኖም ከደቡብ ሱዳን መገንጠል በኋላ ዋና የውጭ ምንዛሬ ገቢ ምንጯ የነበረውን የነዳጅ ሃብት ያጣችው ሱዳን የአሜሪካ ማዕቀብ ስለተነሳላት ብቻ ከገባችበት ውስብስብ የኢኮኖሚ ሁኔታ በቀላሉ ትወጣለች ተብሎ አይጠበቅም፡፡ አገሪቱ የመደበችውን ዓመታዊ በጀት ለመሸፈን በመቸገሯ ብር ወደማተም ገብታለች፡፡

ይህንን ተከትሎም ባለፈው ወር የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት መጠን 114 ፐርሰንት መድረሱ በዚህ ከቀጠለ በአገሪቱ እንደ አዲስ የሕዝብ ተቃውሞ ሊያስነሳ ይችላል ብሎ የሰጋው የሽግግር መንግስት በተቻለ መጠን የውጭ እርዳታን ለማግኘት እየተጣጣረ ይገኛል፡፡ በዛሬው እለት “የሱዳን ወዳጆች የድጋፍ ስብስብ” በሚል ርእስ የቪድዮ ኮንፈረንስ በጀርመን መንግስት አስተባባሪነት የሚደረግ ሲሆን ሱዳን ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ታገኝበታለሽ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የሽግግር መንግስቱ በሲቪሎችና በወታደር ጀነራሎች ጥምረት የሚመራ ሲሆን በኢኮኖሚ መውደቅ ምክንያት የሚከሰት አለመረጋጋት ጀነራሎቹ የሲቪል አጋሮቻቸውን ወደጎን በመግፋት ሙሉ በሙሉ ስልጣን እንዲቆጣጠሩ ይረዳቸዋል የሚል ስጋት አለ፡፡ በተለይም እንደነ ግብፅና ሳውዲ አረብያ ያሉ አገራት ጀነራሎቹ የበለጠ ስልጣን በሽግግር መንግስቱ ውስጥ እንዲኖራቸው ከመፈለግ ጋር ተያይዞ የሱዳንን ውስጣዊ ሁኔታ ውስብስብ አድርጎታል፡፡

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

በአክሱም ከተማ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

  ተቀማጭነቱን በለንደን ከተማ ያደረገውና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ክትትል የሚያደርገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰአታት በፊት ባወጣው ባለ 25...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊል ድርሻ ለቱርክ መንግስት ሊሸጥ ነው

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እስከ ግማሽ የሚጠጋ የባለቤትነት ድርሻ ለቱርክ...

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሸጠችው ቦንድ ዋጋው እያሽቆለቆለ ነው

ከውጭ ባለሃብቶች 1 ቢልዮን ዶላር ለመበደር በ2007 እ.ኢ.አ ኢትዮጵያ የሸጠችው ቦንድ በአየርላንድ የቦንድ ገበያ ላይ ባለሃብቶቹ እርስ በርስ የሚገበያዩበት ዋጋ ማሽቆልቆሉን ቀጥሏል። ከሶስት ሳምንታት...

ኤርትራ፤ ከተራራው ጀርባ ጠልቃ የቀረችው ሰሜናዊት ኮኮብ

  ኤርትራ ከባህር በሯ በዘለለ፤ ምድሯ ጥቅም የለውም የሚለው አስተሳሰብ ከኢትዮጲያ ጋር ፍቺ ሳትፈጽም በፊት ገዢ ሃሳብ ሆኖ ነው የኖረው፡፡ በደርግ ጊዜ የኢትዮጲያ ፕሬዝዳንት የነበሩት...

ኢኮኖሚያዊ ህልሙ በፖለቲካ ይጨናገፍ ይሆን?

  በ2013 እ.ኤ.አ. የአዲስ አበባ መስፋፋት የኦሮሚያ ገበሪዎችን አፈናቅሏል በሚል የተጀመረው የጸጥታ አለመረጋጋት ሰባት አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ይህ አመጽ አሁን ያሉትን ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ስልጣን አምጥቶ...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -