Wednesday, May 25, 2022

አሜሪካ በዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ላይ የያዘችው ቂም

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

የኮሮና ቫይረስ ወደ አሜሪካ ተዛምቶ ኒውዮርክ ከተማን ማሸበር በጀመረበት ሰሞን የአሜሪካ የዜና አውታሮችን እረፍት ነስተው ከነበሩት ጉዳዮች አንዱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዓለም የጤና ድርጅት ዋና ስራ አስክያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ላይ ሲያወርዱት የነበረውን የስድብ ጋጋታ እየተከታተሉ መዘገብ ነበር፡፡

ከከፍተኛ ትንቅንቅ በኋላ ግዙፉን የጤና ተቋም መምራት ከጀመሩ ሦስተኛ አመታቸውን የያዙት ዶ/ር ቴድሮስ ከአሜሪካ መንግስት ጋር ወደ አተካራ የገቡት ገና በተመረጡ በጥቂት ቀናቶች ውስጥ ነበር፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ የጤና ተቋሙ መሪ ለመሆን በቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት የቻይናዋ ግዛት ታይዋን በተቋሙ እንደ አንድ ሉአላዊት አገር በአባልነት መሳተፍ አለብኝ በሚል ጥያቄ ከከፍተኛ የአሜሪካ ድጋፍ ጋር በተቋሙ ላይ ግፊት እያደረሰች ነበር፡፡ የታይዋን አባል የመሆን ፍላጎት የሚመነጨው ከጤና ተቋሙ ለምታገኘው ድጋፍ በመጓጓት አይደለም፡፡ ይልቅ በአንድ ዓለም አቀፍ ተቋም የታይዋን አባል መሆን ከቻይና ተላቃ ሙሉ ሉአላዊት አገር ለመሆን በምታደርገው ትግል ላይ በዓለም መድረክ እውቅናን ስለሚያሰጣት ነው፡፡ የታይዋን እራስዋን የቻለች አገር መሆን ከለት ወደ እለት እየተቀናቀነቻት የመጣችውን ቻይናን ያዳክምልኛል ብላ የምታምነው አሜሪካም ለታይዋን በመወገን በጤና ተቋሙ አመራር ላይ ትልቅ ተፅዕኖን ለማሳደር ስትሞክር ቆይታለች፡፡ የተባበሩት መንግስታት አንድ አካል የሆነው የዓለም የጤና ድርጅትም በበኩሉ በተባበሩት መንግስታት እውቅና የሌላትን ታይዋን አባል አድርጎ የመቀበል ግዴታም ሆነ መብት የለኝም የሚል አቋም ይዞ የቆየ ሲሆን ለታዛቢነት ቢሆን እንኳን እንደ በፊቱ ቻይና ሳትፈቅድ ትንሿን አገር እንደማይጋብዝ በተደጋጋሚ ተናግሯል፡፡

በዚህ መሃል ነበር ዶ/ር ቴድሮስ ከካናዳዊቷ የቀድሞ የዓለም የጤና ተቋም ዋና ዳይሬክተር ማርጋሬት ቻን ስልጣንን የተረከቡት፡፡ የስልጣን ወንበሩን በተቆናጠጡ በሁለተኛው ቀንም ተቋሙ ታይዋንን በአባልነት እንደማይቀበልና በጉባኤዎቹ ላይም በቻይና መወከል እንዳለባት ገለፁ፡፡ ቀድሞውኑም በምርጫ ውድድሩ ጊዜ ዶ/ር ቴድሮስ እንዲመረጡ ፍላጎት ያልነበራት አሜሪካም በመግለጫቸው በመበሳጨት በይፋም ሆነ በግል ጫና ለማድረግ ብዙ ሞከረች፡፡ ይህም ሳይሳካ ሲቀር በተለያዩ የዜና አውታሮቿ በዶ/ር ቴድሮስ ላይ በስም ማጥፋት ዘመቻ ላይ ተጠምዳና ለቦታው ብቃት እንደሌላቸው ስትሰብክ ቆየች፡፡

በ30 ዓመታት ውስጥ ከድህነት እራሷን አውጥታ ዛሬ ከዓለም ሃያላን ተርታ የተሰለፈችው ቻይና ለሃብታሟ አሜሪካ ራስ ምታት ከሆነችባት ሰነባብታለች፡፡ ግዙፍና ዘመናዊ ጦርን ከመገንባትም አልፎ በቴክኖሎጂ፣ በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ አሜሪካን እየተፎካከረች የመጣችው ቻይና በተለይም የአለም ሃገራትን በመሠረተ ልማት ለማስተሳሰር የጀመረችው ፕሮጀግት እንዲሁም 5G በሚባለው አዲስና የተራቀቀ ቴክኖሎጂ የደረሰችበት ርቀት አደጋ ፈጥሮብናል የሚለው ሃሳብ በተለምዶ በተቃርኖ የሚቆሙትን የዴሞክራትና ሪፐብሊካን የአሜሪካ ፓርቲዎች ያስማማ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ይህንንም ስጋት ለማቃለል የአሜሪካ መንግስት የተለያዩ ፀረ ቻይና አካላትን መደገፍ፣ የቻይናን ኢኮኖሚ ዕድገት ለማሰናከል መንቀሳቀስ፣ ብሎም የአውሮፓና ሌሎች አገራትን አስተባብሮ ቻይና ላይ ማሳመፅን ተያይዞታል፡፡

ታድያ ዘንድሮ የተከሰተው ምንጩ ከቻይና የሆነ የኮሮና ወረርሽኝ የአሜሪካና ቻይናን ፍጥቻ ወደተካረረ ዙር የወሰደው ይመስላል፡፡ በዚህ ግርግርም ዶ/ር ቴድሮስ የሚመሩት የዓለም የጤና ድርጅት መሃል ገብቷል፡፡ ዉሃን በሚባለው የቻይና ግዛት የመነጨው የኮሮና ቫይረስ አጀማመሩን አይተው በመስጋት ማስጠንቀቅያ ሲያሰሙ የነበሩት ዶክተሮች በኮሚኒስቱ ፓርቲ የታሰሩ ሲሆን በአካባቢው ያለውን ሁኔታ ዓለም እንዳያውቀው አፍኖ የያዘው የቻይና መንግስት በወቅቱ ከዓለም የጤና ድርጅት ጋርም ሆነ ከሌሎች አገራት ጋር ተቀናጅቶ ቢረባረብ ኖሮ በሽታው ገና ከእንጭጩ ማጥፋት የሚቻልበት እድል ነበር በማለት አሜሪካንን ጨምሮ ከምዕራባውያን በኩል ወቀሳ ይሰማል፡፡ከአሜሪካ የሚወጠኑባት በርካታ ሴራዎች ስጋት ውስጥ የከተቷት ቻይና የትራምፕ መንግስት ወረርሽኙን እንደ እድል በመጠቀም ድንጋጤ ለመፍጠርና የቻይናን የንግድ ዘርፍም ሆነ አጠቃላይ ኢኮኖሚ ለመጉዳት ሊጠቀምበት ይሞክራል ከሚል ፍራቻ በሽታውን አደባብሳ ብቻዋን ልታጠፋው ሞክራለች፡፡

ሆኖም ይህ ትልቅ የቻይና ስህተት የኮሮና ቫይረስ ከዉሃን ግዛት ተሻግሮ ወደተለያዩ አገራት እንዲዛመት በማስቻሉ ዛሬ ዓለማችንን የፊጥኝ አስሯት ይገኛል፡፡ ቻይና ከስህተቷ በመማር በቀጣይ ያደረገቻቸው ውሳኔዎች ማለትም ወረርሽኙ በፍጥነት እየተዛመተበት ያለውን ያገሪቱን ክፍል ሙሉ በሙሉ ዘግታ ከሌሎች አካባቢዎች አቆራርጣ ማቆየቷና የተራቀቀ ቴክኖሎጂን ከጠንካራ የፀጥታ መዋቅር ጋር አቀናጅታ መስራቷ በሽታው በአሜሪካና በአውሮፓ ያደረሰውን ያክል ጉዳት በቻይና ሳያደርስ ቀርቷል፡፡ የቻይና መንግስት አሃዞች የሚይሳዩት ከ5ሺ ያነሰ የህይወት መጥፋት ከኮሚኒስት ፓርቲው ዝቅተኛ ተአማኒነት አንፃር ሲታይ አመኔታ የሚጣልበት ባይሆንም የተደበቀው የሟቾች ቁጥር ተደምሮም ቢሆን ይህ ነው የሚባል ጉዳት ቻይና እንዳልደረሰባት ብዙዎች ይስማማሉ፡፡

ይህንንም ተከትሎ ቻይና ላሳየችው ውጤታማ አሰራር ከፍተኛ አድናቆትን በይፋ የሰጡት ዶ/ር ቴድሮስ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጀምሮ ከበርካታ የምዕራቡ ዓለም ፖለቲከኞች ዘንድ ተቃውሞን አስነስቶባቸዋል፡፡ በሽታው አደገኛ ደረጃ በደረሰበትና በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ዜጎች እየሞቱ በነበሩበት ሰዓት ቀድመው ባለመዘጋጀታቸው ብሎም የባለሙያዎችን ማስጠንቀቅያ ሲያጣጥሉ በመቆየታቸው ትልቅ የአገር ውስጥ ተቃውሞ የገጠማቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለችግሮቻቸው ሁሉ የዓለም የጤና ድርጅትንና ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስን ተጠያጊ ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በተደጋጋሚ ዶ/ር ቴድሮስን የቻይና አጎብዳጅ በማለት የወነጀሉ ሲሆን በቅርቡም አገራቸው አሜሪካ ለጤና ተቋሙ የምታደርገውን ከሁለት መቶ ሚልዮን ዶላር በላይ አመታዊ ድጎማ እንድታቋርጥ ከማድረግም አልፈው አሜሪካ ሙሉ በሙሉ ከአባልነቷ እራሷን እንድታገል ተእዛዝ ሰጥተዋል፡፡

የተለያዩ በዶ/ር ቴድሮስ ስር ያሉ የጤና ተቋሙ ሃላፊዎች ከጋዜጠኞች ጋር በድብቅ ባደረጓቸው ቃለ መጠይቆች የዶ/ር ቴድሮስ ቻይናን ማሞገስ ከፖለቲከኛነታቸውና ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት ከነበራቸው የዲፕሎማት ፀባይ የተነሳ ነው ሲሉ ይናገራሉ፡፡ ዶ/ሩ ቻይናን በጥሩ ሁኔታ ለማሞካሸት የፈለጉት የቻይና መንግስት በጤና ተቋሙ ላይ ቅሬታ እንዳያድርበትና ጠንካራ ግፊት ከተደረገበት ከተቋሙ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዳያቋርጥ ይህም ከቻይና የጤና ተቋማት ከፍተኛ ትብብር በሚያስፈልግበትና የጤና ተቋሙ ሰራተኞች በአገሪቱ ተንቀሳቅሰው መስራት ወሳኝ በሆነበት ሰዓት ትልቅ መሰናክልን እንዳይፈጥር ከመስጋት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ በአሜሪካ የመገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ድህረ ገፆች ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶባቸው ይገኛሉ፡፡ ይባስ ብሎም እለታዊ መግለጫ ሲሰጡ ከቆዩባቸው ቀናት በአንዱ በህይወታቸው ላይ ዛቻ እየተደረገባቸው እንደሆነና የተለያዩ ዘርን መሠረት ያደረጉ ስድቦች እየደረሱባቸው እንደሆነ ይፋ አድርገዋል፡፡ በዚህ መግለጫቸው አብዛኛው ስድብ እየደረሰባቸው ያለው ከታይዋን አካባቢ መሆኑን ተናግረው ነገር ግን ስራቸውን ከመስራት ወደኋላ እንደማይሉና በጥቁርነታቸው እንደሚኮሩ ገልፀዋል፡፡

ከ4 ወራት በኋላ በአሜሪካ ለሁለተኛ ግዜ ለመመረጥ የሚወዳደሩት ፕሬዝዳንት ትራምፕም አገራቸው እራሷን ካገለለችበት ወደ የዓለም የጤና ድርጅት እንድትመለስ ከመወሰናቸው በፊት መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ያሳወቁ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም የተቋሙ ከቻይና ተፅዕኖ መላቀቅና የዶ/ር ቴድሮስ ከስልጣን መውረድ ይገኙበታል፡፡ ለጊዜው ግን ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዶ/ር ቴድሮስ ላይ ጥርሳቸውን እንደነከሱ አሉ፡፡

- Advertisement -

1 COMMENT

  1. I think this is among the most important information for me. And i’m glad reading your article. But should remark on some general things, The site style is perfect, the articles is really excellent : D. Good job, cheers

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -