Saturday, January 22, 2022

አሜሪካ በቻይና ሰራሹ ቲክቶክ ላይ የጣለችው እገዳ ከሰኞ ጀምሮ ይተገበራል

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

ባይትዳንስ በተባለው ቻይናዊ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ተሰርቶ ባለፉት ሁለት ዓመታት በመላው ዓለም ተወዳጅነትን ያተረፈው የማህበራዊ መገናኛ አውታር ቲክቶክ በአሜሪካውያን ስልኮች ላይ እንዳይጫን የሚከለክለው እገዳ ከመጭው ሰኞ ጀምሮ የሚተገበር ይሆናል ። ይህ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ የመጣው ቀጥተኛ ትእዛዝ አሜሪካ ከቻይና ጋር የገባችበት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተካረረ የመጣ የኢኮኖሚና ቴክኖሎጂ ቀዝቃዛ ጦርነት አካል ሲሆን ከመጭው ሕዳር 3 ጀምሮ ደግሞ ቲክቶክን ቀድመው በስልካቸው ከጫኑ አሜሪካውያን ስልክ ላይ ከነአካቴው የሚሰወር ይሆናል።

እንደ ፕሬዝዳንቱና አስተዳደራቸው እምነት በአሜሪካውያን ዘንድ እየጨመረ የመጣው የቲክቶክ ተወዳጅነት ምናልባት ለቻይና መንግስት የመረጃ መሰብሰብያ እድል ሊፈጥርና የአገራቸውን ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ነው። ይህ የማህበራዊ መገናኛ አውታር በአሜሪካ ብቻ ከ100 ሚልዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን አጠቃላይ ዋጋውም እስከ 50 ቢልዮን ዶላር እንደሚያወጣ ይገመታል። የቲክቶክ በአሜሪካ መታገድ በገቢው ላይ ትንሽ የማይባል አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚፈጥርበት የተረዳው የቴክኖሎጂው ባለቤት ኩባንያ ባይትዳንስ ቲክቶክን ለብቻው ነጥሎ እራሱን የቻለ ኩባንያ አድርጎ ሊያቋቁመውና የሚበዛውን ድርሻ ለአሜሪካውያን ባለሃብቶች በመሸጥ የስራ ሂደቱም ለአገር ደህንነት አስተማማኝ በሆነ መልኩ ሙሉ በሙሉ በአሜሪካውያን እንዲከናወን ሃሳብ ያቀረበ ቢሆንም የዶናልድ ትራምፕ መንግስት ግን ይህንን ሃሳብ ለመቀበል በማቅማማት ላይ ይገኛል።

አሜሪካ ትቅደም የሚል ፖለቲካ የሚያራምዱት ሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንት ትራምፕ እራሳቸውን ፀረ ቻይና በሆኑ አማካሪዎችና ባለስልጣናት በመክበባቸው ወደ ዋይት ሃውስ ገብተው ብዙም ሳይቆዩ ነበር ከቻይና ጋር አተካራ ውስጥ የገቡት። ይሁን እንጂ በቻይና እየታየ ያለው ፈጣን የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ እድገት የፈጠረው ስጋት በፕሬዝዳንት ትራምፕ ብቻ ሳይወሰን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞችንም ጭምር እያሳሰበ ይገኛል። ከሁለት ቀናት በፊት የፕሬዝዳንቱ ተቃዋሚ የሆነው የዴሞክራቲክ ፓርቲ በአገሪቱ ምክር ቤት ባሉት አባሎቹ በኩል አሜሪካ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት 350 ቢልዮን ዶላር ለኢንዱስትሪና መሠረተ ልማቶች በመመደብ ከቻይና እያየለ የመጣውን ፉክክር እንድትቋቋም ሰሞኑን አዲስ ሃሳብ አቅርቧል።

በተለይም አዲሱን የ5ጂ ኔትዎርክ ቴክኖሎጂ በመገንባት ላይ ቻይና አሜሪካን ቀድማት መሄዷ በዋሽንግተን ዲሲ ከፍተኛ ስጋትን የፈጠረ ሲሆን ለ5ጂ ኔትዎርክ የሚሆነውን ቴክኖሎጂ በዋነኛነት እየገነባ ያለውን ህዋዌይ የተሰኘ የቻይና ኩባንያ ከአሜሪካ ከማባረርም አልፎ የአገር ውስጥ የግል ኩባንያዎች ለህዋዌይ ምንም አይነት ተጓዳኝ ምርቶችን እንዳይሸጡ አሜሪካ ማዕቀብ ጥላለች።

ይህንን ተከትሎም የቲክቶክ ባለቤት ባይትዳንስ የዶናልድ ትራምፕን መንግስት በዋሽንግተን ዲሲ የፌደራል ፍርድቤት በትላንትናው እለት መክሰሱን አሳውቋል። የአሜሪካው የንግድ ጋዜጣ ብሎምበርግ እንደዘገበው የቻይናው ኩባንያ በክሱ ላይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቲክቶክ ላይ የጣሉት እገዳ እሳቸው እንዳሉት ከአገር ደህንነት ጋር የተያያዘ ሳይሆን ምርጫ እየተቃረበ በመምጣቱ ለፖለቲካ ትርፍ ተብሎ የተደረገ ውሳኔ እንደሆነና ስለዚህም ፕሬዝዳንቱ የስልጣን ገደባቸውን ጥሰው የሰጡት ትእዛዝ ነው የሚል ስሞታ አቅርቧል። ሆኖም የፌደራል ፍርድቤት የፕሬዝዳንት ውሳኔን የመቀልበስ አቅም ይኑረው እንጂ የደህንነት ስጋት ከሚል ምክንያት ጋር የተያያዙ ውሳኔዎችን ለመቀልበስ ያለው ሂደት ግን እጅጉን የተወሳሰበ ነው።

አዲሱ እገዳ ከቲክቶክም በተጨማሪ ዊቻት የተባለውን ሌላኛውን የማህበራዊ መገናኛ አውታር የሚያጠቃልል ነው። ዊቻት ለቻይናውያን እንደ የማህበራዊ መገናኛ አውታር ከማገልገሉም በተጨማሪ በስልክ የገንዘብ መላላኪያ አገልግሎትን 1 ቢልዮን ለሚጠጉ ተጠቃሚዎቹ ይሰጣል። በአሜሪካም የቲክቶክን ያህል እውቅና አይኑረው እንጂ ከ3 ሚልዮን በላይ በአብዛኛው የቻይና የዘር ሓረግ ያላቸው የአሜሪካ ዜጎችና ነዋሪዎች ይጠቀሙበታል።

ከሁለት ወራት በኋላ በሚድረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዳግም ለመመረጥ የሚወዳደሩት ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ጄ ትራምፕ የአገር ተቆርቋሪና ቻይናን ከመጋፈጥ ወደኋላ የማይሉ እንደሆኑ ለደጋፊዎቻቸው ለማሳየት ያገኙትን እድል ሁሉ ከመጠቀም ወደኋላ እንደማይሉ አስመስክረዋል። ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ በእሳቸው እውቅና በቴክሳስ ክልል የነበረው የቻይና ቆንስላ ፅህፈት ቤት ተዘግቷል፣ በአጭር ጊዜ ቪዛ ለትምህርት ወደ አሜሪካ በሚመጡ ቻይናውያን ላይ የተለያዩ መጉላላቶች እንዲፈፀሙ ተደርጓል፣ በአወዛጋቢዋ የቻይና ግዛት ሆንግኮንግ ውስጥ ለተነሳው አመፅ ፕሬዝዳንቱ በይፋ ድጋፍ አድርገዋል፣ ብሎም የተራቀቁ የአሜሪካ ቴክኖሎጂዎች ለቻይና ኩባንያዎች ምንም አይነት እቃ እንዳይሸጡ ለማስተጓጎል በተደጋጋሚ ሞክረዋል።

የ77 ዓመቱ የቀድሞ የፕሬዝዳንት ኦባማ ምክትልና ዛሬ ፕሬዝዳንት ትራምፕን በምርጫ ላይ የሚፎካከሩት የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባሉ ጆ ባይደን በበኩላቸው ቲክቶክ ለአሜሪካ ደህንነት በእርግጥ የሚያሰጋ መሆኑን ቢያምኑም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቻይና ላይ እየወሰዷቸው ያሏቸው እርምጃዎች ብስለት የጎደላቸውና ከመፍትሄ ይልቅ ቻይናን የሚጠቅሙ በአንፃሩ ደግሞ የአሜሪካን ኢኮኖሚ የሚጎዱ ናቸው የሚል ትችት ሲያቀርቡ ይሰማሉ። ታድያ ይህን የጆ ባይደን ትችት የሰሙት ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ምርጫ ተሸንፈው ስልጣናቸውን ለዴሞክራቱ ተፎካካሪያቸው አሳልፈው ከሰጡ ለቻይና ትልቅ የምስራች እንደሚሆንና የጆ ባይደን መልፈስፈስ አሜሪካንን አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል ለደጋፊዎቻቸውና ለተቃዋሚዎቻቸው አስጠንቅቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሰኞ በኋላ ቲክቶክም ሆነ ዊቻትን ወደስልክ መጫን አይቻልም የሚለውን ዜና ተከትሎ አሜሪካውያን ከእገዳው በፊት ለመጫን በእሽቅድድም ላይ ይገኛሉ። ከስልክ አፕሊኬሽኖች ጋር የተያያዙ አሃዞችን የሚመዘግበው ሴንሰር ታወር የተባለ ድህረ ገፅ እንደሚያሳየው ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ከ400 ሺ በላይ ሰዎች ቲክቶክን እንዲሁም ከ18ሺ በላይ ሰዎች ደግሞ ዊቻትን በስልካቸው ላይ ጭነዋል።

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -