አሜሪካ አዲስ አምባሳደር ወደ ኢትዮጵያ ልትልክ ነው

0

በኢትዮጵያ ቆይታቸው 3ኛ አመታቸውን እያገባደዱ ያሉትን የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሬይነርን ለመተካት አሜሪካ አዲስ እጩ መርጣለች፡፡ የሕንድ ዘር ያላቸው ጊታ ፓሲ ተወልደው ያደጉት በኒውዮርክ ሲሆን በፈረንሳይኛ ቋንቋ የማስተርስ ዲግሪ አላቸው፡፡ አዲሲቷ እጩ ከዚህ በፊት በጅቡቲና በቻድ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በተጨማሪም በህንድ፣ ባንግላዲሽ፣ አፍጋኒስታን፣ ጀርመን፣ ጋናና ሉሎች አገራት በተለያዩ ሃላፊነቶች አገልግለዋል፡፡ የአሜሪካ አምባሳደሮች በተቻለ መጠን በአንድ አገር ከ3 ዓመት በላይ እንዳይቆዩ የሚደረግ ሲሆን ይህም አምባሳደሮቹ አሜሪካን ለመወከል በተላኩበት አገር የተለየ ቁርኝት እንዳይፈጥሩና የአገራቸውን ጥቅም አሳልፈው እንዳይሰጡ ለመከላከል ነው፡፡ የአሜሪካው ሴነት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ በፕሬዝዳንት ትራምፕ የታጩትን አምባሳደር ተቀብሎ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/1/1b/Geeta_Pasi_US_State_Dept_photo.jpg/1200px-Geeta_Pasi_US_State_Dept_photo.jpg

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here