Saturday, January 22, 2022

የኢትዮጵያና የኬንያ አለመግባባት የሱማልያን ፖለቲካ ይበልጡን እያወሳሰበው ይገኛል

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ ነበር በደቡባዊ የሱማልያ ክፍል ውስጥ በሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻ በምትገኘው ኪስማዮ ከተማ አየር ማረፍያ አንድ አውሮፕላን ለማኮብኮብ በዝግጅት ላይ ነው። ሆኖም በአየር ማረፍያው የሚሰሩ ባለስልጣናት መኪኖቻቸውን የአየር ማረፍያ አስፋልቱ ላይ በማቆም አውሮፕላኑ ማረፍያ እንዲያጣ ያደርጋሉ። ቀጥሎም ባለስልጣናቱ ከአውሮፕላኑ ፓይለት ጋር በሬድዮ በመገናኘት በአየር ማረፍያው ላይ ማረፍ እንደማይችል እና ወደመጣበት እንዲመለስ ካልሆነም ሌላ ቦታ ፈልጎ እንዲያርፍ መልዕክት ያስተላልፋሉ። አማራጭ ያጣው ፓይለትም ከኪስማዩ ስድስት መቶ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ባይዶዋ በመሄድ አውሮፕላኗን ያሳርፋታል። ይህ አውሮፕላን ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ሲሆን በውስጡ ያሳፈረውም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትን ነበር።

የኪስማዮ ከተማ የምትገኘው በሱማልያ ካሉት ስድስት የፌደራል ክልሎች አንዷ በሆነችው ጁባላንድ ውስጥ ከመሆኑም በተጨማሪ የክልሉ ዋና ከተማ በመሆን ታገለግላለች። ኬንያን በደቡብ አንዲሁም ኢትዮጵያን በምዕራብ የምታዋስነው ጁባላንድ የራሷ ክልላዊ መንግስት ያላት ቢሆንም ሞቇዲሾ ካለው የፌደራል መንግስት ጋር ከተኳረፈች አመታት ተቆጥረዋል። የጁባላንድ ክልል ኬንያን ከማዋሰኗ አኳያ ከኬንያ ጋር ጥብቅ ግንኙነት የፈጠረች ሲሆን በርካታ የኬንያ ወታደሮች በስፍራው ይገኛሉ። በኪስማዩ አየር ማረፍያ የኢትዮጵያውን አውሮፕላን ካጋጠመው ክስተት ቀደም ብሎ በአፍሪካ አንድነት ስር ባለው የአሚሶም ጦር የሚያገለግሉ አንድ ኢትዮጵያዊ ኮማንደር ኪስማዮ ኤርፖርትን ለሚጠብቁት የኬንያ ወታደሮች መልዕክት አስተላልፈው ነበር። ይህም መልዕክት ኢትዮጵያ በአየር ማረፍያው ወታደሮቿን ልታሰፍር እንደምትፈልግ እና የኬንያ ወታደሮች በዚህ ጣልቃ እንዳይገቡ የሚጠይቅ ቢሆንም ኤርፖርቱን የሚጠብቁት ኬንያውያን ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርገውት ነበር።

ኢትዮጵያም ሆነ ኬንያ ሱማልያ ውስጥ በአፍሪካ አንድነት ለሚመራው የአሚሶም ሰላም አስከባሪ ሃይል በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን በማዋጣት ፅንፈኛውን የአልሻባብ ቡድን በመዋጋት ላይ ናቸው። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከአሚሶም ውጪ የሆነ እና በቀጥታ ከአዲስ አበባ ትዕዛዝ የሚቀበል በሺዎች የሚቆጠሩ አባላት ያሉት ሰራዊት በሱማልያ አስፍራለች። ነገር ግን የጁባላንድ ክልል ጉዳይ በተለየ መልኩ ኬንያን ኢትዮጵያንና በሞቃዲሹ ያለውን የሱማልያ ፌደራል መንግስት አፋጧል።

ጁባላንድ የዛሬ ስምንት አመት አካባቢ ተመስርታ አሁን ያላትን ሰፊ ቅርፆ ይዛ ክልል የሆነችው በኬንያ ከፍተኛ ግፊትና ድጋፍ ነበር። በወቅቱ የኪስማዮ ከተማና አካባቢዋ በአልሻባብ ቁጥጥር ስር የነበሩ ቢሆንም ኬንያ ወታደሮቿን ልካ ከአህመድ ማዶቤ እና ደጋፊዎቹ ጋር በመሆን አካባቢውን ከአልሻባብ ነፃ አውጥታለች። አህመድ ማዶቤም በኬንያ እርዳታ የክልሉ አስተዳደርን ተረከቡ። በክልሉ ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር የያዙት በዳሩድ ስር በሆነው የኦጋዴን ዘር ሐረግ ያላቸው ሱማልያውያን በሞቇዲሾ ያለውን የፌደራል መንግስት ከተቆጣጠሩት የሃውዬ ዘር ህዝብ ጋር ባላቸው ከፍተኛ አለመተማመን ምክንያት የራሳቸው ግዙፍ ክልል በጁባላንድ እንዲመሰርቱ ከረዳቻቸው ኬንያ ጋር ትልቅ ፍቅር ውስጥ ገብተዋል ።

ታድያ ይቺ ከተመሰረተች አጭር ዕድሜን ያስቆጠረችው የጁባላንድ ክልል በሱማልያ የፌደራል መንግስት ሙሉ እውቅናን ያላገኘችና በጥርጣሬ የምትታይ ሆና ቆይታለች። ባለፈው ሚያዝያ የክልሉ መንግስት ባካሄደው ምርጫ ላይም የሱማልያ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመሆን የጁባላንድ ምርጫ እውቅና የሌለው መሆኑን እና ሊቆም እንደሚገባ ሲያስጠነቅቅ ቢቆይም ምርጫው የተካሄደ ሲሆን በስልጣን ላይ ያሉት አህመድ ማዶቤም በአሸናፊነት ክልሉን ማስተዳደር ቀጥለዋል። የአህመድ ማዶቤ ክልላዊ ስልጣን መራዘም ኬንያን ያስፈነጠዘ ቢሆንም ኢትዮጵያን እና የሱማልያ ፌደራል መንግስትን ስጋት ውስጥ ከቷል።

ኬንያ ከጁባላንድ የምታገኘው ጥቅም

በተደጋጋሚ የአልሻባብ ሽብር ጥቃት ሰለባ የሆነችው ኬንያ ብዙ ንፁሃን ዜጎቿን ከማጣቷ ባሻገር በቱሪዝም ዘርፏ ላይ አንዲሁም በሰሜናዊ ክፍሏ ላይ በምታደርጋቸው ልማታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አሳድሮባታል። ኬንያ በሕንድ ውቅያኖስ ላይ አዲስ ከተሰራው የላሙ ወደብ ጀምሮ ሰሜናዊ ኬንያን አቇርጦ በሁለት መስመር በመከፈል በአንድ በኩል ወደ የኢትዮጵያዋ ከተማ ሞያሌ በሌላ አቅጣጫ ደግሞ ወደ ደቡብ ሱዳን የሚያቀና የንግድ ኮሪደር እስከ ሰላሳ ቢልዮን ዶላር በሚያወጣ ወጪ እየገነባች ነው። ይህ ኮሪደር ከወደብ በተጨማሪ ሰፋፊ መንገዶችን፣ የመብራት ማሰራጫ መስመር እና ነዳጅ ከደቡብ ሱዳን የሚያመላልስ ቱቦን እንዲሁም የባቡር መስመርን ያካትታል። ታድያ የዚህ ኮሪደር ወደ ሱማሌ ድንበር መቅረብ በፕሮጀክቱ ላይ አልሻባብ ወይም ለወደፊት ሌላ በሱማልያ ሊፈጠሩ የሚችሉ ፅንፈኛ ቡድኖች ጥቃት ያደርሱበታል በሚል ከኬንያ ብሎም ፕሮጀግቱ ላይ ከሚሳተፉ ኢንቨስተሮች ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን አሳድሮ ቆይቷል። ስለዚህም ኬንያ እንደመፍትሄ ብላ የያዘችው በደቡባዊው የሱማልያ ክፍል የምትገኘውን ጁባላንድ ክልልን አጠናክራ በመደገፍ የተደራጀ እና በኬንያ ተፅዕኖ ስር ያለ መንግስት እንዲኖራት ነው። የጅባላንድ ክልል ኬንያን ከቀሪው የሱማልያ ክፍል ጋር ሙሉ ለሙሉ የሚታቆራርጥ በመሆኑ ይህች ክልል አልሻባብ ወደ ኬንያ ሳይገባ እዛው ሱማልያ ውስጥ ከመመከትም አልፎ የእርስ በርስ ጦርነት እና የፖለቲካ ቀውስ ለሰላሳ አመታት ከሚያሰቃየው ቀሪው የሱማያ ክፍል የሚመጣ ማንኛውም አይነት ችግር ጁባላንድ ከለላ ትሆነኛለች የሚል ተስፋ ኬንያ ሰንቃለች።

Image may contain: one or more people and outdoor

ከዚህም በተጨማሪ ይህንን የኬንያ እቅድ ይበልጡን የሚገፋፋ ነገር በዚህ ዓመት ተከስቷል።

በዚህ እየተገባደደ ባለው የፈረንጆች ዓመት መጀመርያ የሱማልያን ፈደራል መንግስት ከኬንያ ጋር የሚያጋጭ ጉዳይ ተፈጥሯል። ይህንን አለመግባባት ያመጣው ሁለቱ አገራት በህንድ ውቅያኖስ ላይ ባለ አንድ መቶ ሺ ካሬ ግዛት ላይ የይገባኛል ውዝግብ ውስጥ በመግባታቸው ነበር። ይህ መሬት የማይነካው የውሃ ግዛት ከስሩ ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ የተገኘበት ሲሆን ሱማልያ ተሽቀዳድማ የራሴ ግዛት በማለት እንግሊዝ ውስጥ ባካሄደችው ጨረታ ለተለያዩ የነዳጅ አውጪ ኩባንያዎች በሊዝ አከፋፍላዋለች። ይህ የሱማልያ ተግባር ያበሳጫት ኬንያ ከሞቇዲሾ በቀጥታ ወደ ናይሮቢ ይበሩ የነበሩ የመንገደኛ በረራዎችን ከመከልከል በተጨማሪ የተለያዩ የሱማልያ ባለስልጣናት ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ የጉብኝት ፍቃድ ከልክላ ነበር። ታድያ ይህ በህንድ ውቅያኖስ ላይ የሚገኝ በነዳጅ የተባረከ ግዛት በጁባላንድ አቅራብያ መሆኑ ኬንያ ይበልጡን በጁባላንድ ላይ ያላት ጣልቃ ገብነት እንዲጠናከር እያበረታታት ይገኛል። የኬንያና የሱማልያ የግዛት ውዝግብም ሁለቱን ጎረቤታሞች ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት ወስዷቸው ጉዳዩ ተንጠልጥሎ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ስጋት

ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ሱማልያ ጦሯን የላከችው በሚሊንየም መግብያ ሰሞን ነበር። በወቅቱ ሱማልያን ተቆጣጥሮ የነበረው ፅንፈኛ ቡድን ኦጋዴንን ወርሬ የሱማልያ ግዛት አደርጋለው ብሎ ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ማወጁን ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እስከ ሞቇዲሾ ድረስ ዘልቆ በመግባት ቡድኑን ደምስሶት የነበረ ቢሆንም በሱማልያውያን ዘንድ ኢትዮጵያ ላይ በተቀሰቀሰው ቁጣ ምክንያት አዲስ የተወለደው የአልሻባብ ቡድን ምስራቅ አፍሪካን ላለፉት 12 አመታት ሰላም ነስቷታል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ሱማልያ ውስጥ ሁለት አይነት ሰራዊት አሰማርታ ትገኛለች። በአንድ በኩል በሰላም አስከባሪው የአሚሶም ሃይል ስር ግዳጅ እየተወጣ የሚገኘው እስከ 5 ሺ የሚገመት ቁጥር ያለው ሰራዊት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ቁጥሩ በውል የማይታወቅ ነገር ግን ከ5 እስከ 8 ሺ የሚገመት እና በቀጥታ ከአዲስ አበባ ትእዛዝ የሚቀበል ሰራዊት አለ። በድምር ከ10ሺ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሰራዊት ታድያ አልሻባብን በየቦታው እየተዋጋ ቢሆንም በጁባላንድ ጉዳይ ግን ያለው የኢትዮጵያ ስጋት ከአልሻባብ ጋር የተገናኘ አይደለም። እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ሱማልያ ክልል የሚገኘው አብዛኛው የሱማሌ ህብረተሰብ የኦጋዴን የዘር ሐረግ ያለው ነው። ኦጋዴን የሚለው የአካባቢው ስም የመጣውም ከዚህ በመነሳት ነው። ይህ የኦጋዴን አካባቢ በሰባዎቹ መጀመርያ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም መሪ በነበሩበት ጊዜ በኢትዮጵያ እና በሱማልያ መካከል ተከስቶ ለነበረው ከባድ ጦርነት ዋነኛ መንስዔ የነበረ ሲሆን ከዛ በሁዋላም የኦጋዴን ነፃ አውጪ ኦብነግ ከጀመረው የትጥቅ ትግል ጋር ተያይዞ አካባቢው በከፍተኛ የፀጥታ ችግር ሲታወክ ቆይቷል።

No photo description available.

በአሁኑ ወቅት በሱማልያ የጁባላንድን በማስተዳደር ላይ የሚገኙት አህመድ ማዶቤም የዚህ አካባቢ ሰው እንደሆኑ የተለያዪ ጭምጭምታዎች ይሰማሉ። አብዛኛው የጁባላንድ ህዝብ እንደ ኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ህዝብ የኦጋዴን ዝርያ ያለው መሆኑና በኦጋዴኖች የምትመራ እና በኬንያ እርዳታ ከለት ወደ እለት እየተጠናከረች የመጣችው ጁባላንድ በምስራቅ አፍሪካ ላሉት ሌሎች የኦጋዴን ዘር ሐረግ ላላቸው ሱማሌዎች ተምሳሌት እንዳትሆን እንዲሁም በሁዋላ በራስዋ ግዛት ውስጥ ባለው የሱማልያ ክልል ቀስ በቀስ አዲስ ስሜትን እንዳይጭር ኢትዮጵያ ትሰጋለች። በኢትዮጵያ የሱማሌ ክልል እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለመገንጠል አላማ ያላቸው ኣካላት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ከመቆየታቸውም በተጨማሪ የተለይዩ በሱማልያ እና ኬንያ ያሉ ሱማሌ ፖለቲከኞች ታላቇ ሱማልያ መመስረት አለባት የሚል አቇም እንደሚያንፀባርቁ የሚታወቅ ነው። ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ መንግስት ጁባላንድን የሚያስተዳድረው በአህመድ ማዶቤ የሚመራ ክልላዊ መንግስት ስልጣን ላይ መቆየት የለበትም የሚል አቇም ይዞ ሞቇዲሾ ከሚገኘው የፌደራል መንግስት ጋር በመሻረክ እንቅስቃሴ ጀምሯል። ኬንያም በበኩሏ በኢትዮጵያ አቇም ቅሬታ ላይ ከመውደቅም አልፎ የጎረቤቷን እንቅስቃሴ በአይነ ቁራኛ እየተከታተለች ትገኛለች።

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -