Monday, April 12, 2021

ኪሳራ ያደቀቀው የኬንያ አየር መንገድ ወደ መንግስት ሙሉ ይዞታ ሊመለስ ተቃርቧል

Must Read

በአክሱም ከተማ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

  ተቀማጭነቱን በለንደን ከተማ ያደረገውና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ክትትል የሚያደርገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰአታት በፊት ባወጣው ባለ 25...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊል ድርሻ ለቱርክ መንግስት ሊሸጥ ነው

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እስከ...

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሸጠችው ቦንድ ዋጋው እያሽቆለቆለ ነው

ከውጭ ባለሃብቶች 1 ቢልዮን ዶላር ለመበደር በ2007 እ.ኢ.አ ኢትዮጵያ የሸጠችው ቦንድ በአየርላንድ የቦንድ ገበያ ላይ ባለሃብቶቹ እርስ በርስ የሚገበያዩበት...

ላለፉት 7 ዓመታት ትርፍ ማስመዝገብ ሳይችል ከተደጋጋሚ ኪሳራ መውጣት ያልቻለው የኬንያ አየር መንገድ በግል ይዞታ ያለው 51 ፐርሰንት የሚሆነው ድርሻ በመንግስት እጅ ካለው 49 ፐርሰንት በመጠቃለል ሙሉ በሙሉ የመንግስት ለመሆን ተቃርቧል፡፡ አየር መንገዱ ከዚህ በፊት ገብቶበት የነበረው ውዝፍ ዕዳና ተደጋጋሚ ኪሳራ ሳያንስ አሁን ደግሞ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ይዞበት የመጣው ችግር ህልውናውን አደጋ ውስጥ አስገብቶታል፡፡ ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት ብቻ 130 ሚልዮን ዶላር የከሰረው አየር መንገድ ኮሮናን ተከትሎ በመጣ የስራ መቀዛቀዝ ምክንያት ያለበትን የብድር ክፍያም ሆነ የሰራተኛ ደሞዝ መክፈል ባለመቻሉ ከ5 ወራት በፊት የ5 ቢልዮን ሽልንግ (47 ሚልዮን ዶላር) ድጋግፍ ከኬንያ መንግስት ተደርጎለት ነበር፡፡ ለዋና ስራ አስክያጆቹ በወር እስከ 70ሺ ዶላር የሚጠጋ ደሞዝ የሚከፍለው አየር መንገድ ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት ፖላንዳዊ ዜግነት ላላቸው ዋና ስራ አስኪያች ኮንትራታቸው ሳያልቅ በማሰናበቱ የ100ሺ ዶላር ተጨማሪ ካሳ ከፍሏቸው ነበር፡፡

በናይሮቢ የአክስዮን ገበያ ላይ የሚሻሻጠው የአየር መንገዱ አክስዮኖን በሁለት ዓመት ውስጥ የአንዱ አክስዮን ዋጋ ይገበያይ ከነበረበት 9.65 ሽልንግ ወርዶ በ2.50 ሽልንግ እየተሸጠ ይገኛል፡፡ የአክስዮኑን ዋጋ መርከስ ተከትሎ የአየር መንገዱ ጉዳይ አሳስቦት ለቆየው የኬንያ መንግስት እድል የተፈጠረ ሲሆን በግል ይዞታ ያለውን የውጭና ያገር ውስጥ ባለሃብቶች ድርሻ በመግዛት ሙሉ በሙሉ ሊጠቀልለው ወስኖ በፓርላማ ለማፀደቅ እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡ ከግል ባለድርሻዎች ዋናው የሆነው የሆላንዱ አየር መንገድ ኬ ኤል ኤም በበኩሉ ድርሻውን ለመንግስት ሸጦ ለመሄድ ተስማምቷል፡፡

የኬንያ አየር መንገድ በከፊል ለአገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች የተሸጠው ከ24 ዓመታት በፊት ሲሆን አገሪቱን ለኪሳራ እየዳረገ ነው በሚል ከዓለም ባንክና ከዓለም የገንዘብ ድርጅት በመጣ ከፍተኛ ግፊት ነበር የያኔው በዳንኤል አራፕሞይ የሚመራ መንግስት ለሽያጭ ያቀረበው፡፡ ያኔ አየር መንገዱ የተሸጠበት አካሄድ በተወሰነ መልኩ ግልፅነት ጎድሎት እንደነበረና ኬንያን በእዳ ጠምጥመው ይዘዋት ለነበሩት የአውሮፓ መንግስታት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአየር መንገዱ ድርሻ እንደተሸጠላቸው በወቅቱ ሽያጩን ሲቃወሙ የነበሩ ኬንያውያን ይናገራሉ፡፡ የአየር መንገዱን በከፊል መሸጥ ተከትሎም ከመጡት ተጓዳኝ ችግሮች አንዱ የበርካታ ኬንያውያን ከስራ መባረር ይገኝበታል፡፡

ዛሬ አየር መንገዱን ዳግም በእጁ ለማድረግ የወሰነው የኬንያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንደ ፈለግ በመከተል ሊያስተዳድረው እንዳሰበ ያሳወቀ ሲሆን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታም ናይሮቢን በአካባቢው የመንገደኞች መናኸርያ የማድረግ፣ ለኬንያውያን የስራ እድል የመፍጠርና ኢኮኖሚን የማሳደግ አላማ እንዳላቸው ተነግሯል፡፡

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

በአክሱም ከተማ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

  ተቀማጭነቱን በለንደን ከተማ ያደረገውና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ክትትል የሚያደርገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰአታት በፊት ባወጣው ባለ 25...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊል ድርሻ ለቱርክ መንግስት ሊሸጥ ነው

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እስከ ግማሽ የሚጠጋ የባለቤትነት ድርሻ ለቱርክ...

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሸጠችው ቦንድ ዋጋው እያሽቆለቆለ ነው

ከውጭ ባለሃብቶች 1 ቢልዮን ዶላር ለመበደር በ2007 እ.ኢ.አ ኢትዮጵያ የሸጠችው ቦንድ በአየርላንድ የቦንድ ገበያ ላይ ባለሃብቶቹ እርስ በርስ የሚገበያዩበት ዋጋ ማሽቆልቆሉን ቀጥሏል። ከሶስት ሳምንታት...

ኤርትራ፤ ከተራራው ጀርባ ጠልቃ የቀረችው ሰሜናዊት ኮኮብ

  ኤርትራ ከባህር በሯ በዘለለ፤ ምድሯ ጥቅም የለውም የሚለው አስተሳሰብ ከኢትዮጲያ ጋር ፍቺ ሳትፈጽም በፊት ገዢ ሃሳብ ሆኖ ነው የኖረው፡፡ በደርግ ጊዜ የኢትዮጲያ ፕሬዝዳንት የነበሩት...

ኢኮኖሚያዊ ህልሙ በፖለቲካ ይጨናገፍ ይሆን?

  በ2013 እ.ኤ.አ. የአዲስ አበባ መስፋፋት የኦሮሚያ ገበሪዎችን አፈናቅሏል በሚል የተጀመረው የጸጥታ አለመረጋጋት ሰባት አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ይህ አመጽ አሁን ያሉትን ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ስልጣን አምጥቶ...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -