Saturday, January 22, 2022

ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ የማይቀረው የኮሮና ወረርሽኝ የሚያስከትለው አለመረጋጋት ጉዳቱ ከበሽታው በላይ ይሆናል

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

በቻይና ዉሃን ተብላ በምትጠራው ክፍለ ሃገር ባሳለፍነው ታህሳስ ወር የተነሳው በአይነቱ ለየት ያለ የጉንፋን ወረርሽኝ በአጭር ጊዜ ውስጥ እስካሁን ከ80 ሺህ በላይ ሰዎችን ያጠቃ ሲሆን ከ2700 በላይ ሰዎችን ገድሏል። ይህ ኮሮና የሚል ስያሜ የተሰጠው አደገኛ ጉንፋን የቻይናን ድንበር አልፎ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ሌሎች 61 አገራት ተዛምቷል። ሆኖም ከነዚህ 62 አገራት ውስጥ 38 የሚሆኑት በጣት የሚቆጠሩ የቫይረሱ ተጠቂዎችን ያስመዘገቡ ቢሆንም በተቀሩት እንደ ደቡብ ኮርያ ኢራን እና ጣልያን የመሳሰሉት አገራት በሽታው በአስጊ ፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል።

በእርግጥ ቫይረሱ እስካሁን ከታየው በሚብስ ፍጥነት ሊስፋፋና እሁን ከደረሰበት እጅጉን የከፋ ደረጃ የመድረስ እድል ነበረው። ነገር ግን በኮሚኒስት ገዢ ፓርቲ የሚመራው የቻይና መንግስት ወረርሽኙ የተነሳበትን የዉሃን ክፍለ ሃገር ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ወደ 150 ሚልዮን የሚጠጋው የአካባቢው ነዋሪ ከተቀረው የቻይና ክፍልም ሆነ የውጭ ሃገራት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይኖረው ማድረጉ፣ ብሎም በተለያዩ አጋጣሚዎች ከክፍለሃገሩ አምልጠው የወጡትን ዜጎች በጥብቅ ክትትል አሳዶ በመያዝና የጤና ክትትል ማድረጉ የቫይረሱ መስፋፋት እንዲስተጓጎል እንዲሁም የዓለም አገራት ዝግጅት እንዲያደርጉ ጊዜን ሰጥቷቸዋል። ወረርሺኙንም ተከትሎ ቻይና በዉሃን ውስጥ ለቫይረሱ ተጠቂዎች የሚያገለግል የተሟላ ሆስፒታል በ7 ቀናት ውስጥ ብቻ በመገንባት ሪኮርድን ሰብራለች። የዓለም የጤና ድርጅት ፕሬዚዳንት የሆኑት ኢትዮጵያዊው ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖምም የቻይናን ፈጣን እርምጃ ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆን ሲሉ አሞግሰውታል።

በዶክተር ቴድሮስ የሚመራው የዓለም የጤና ድርጅት “ዋናው ስጋቴ የቻይና ወረርሽኙን የመዋጋት ብቃት ሳይሆን በሌሎች ደካማ የጤና ጥበቃና የመንግስት መዋቅር ባላቸው አገራት ከተስፋፋ ሊያመጣው የሚችለው ጉዳት ነው” ሲል አሳስቧል። እስካሁን በያዘው አቋም መሰረት የዓለም የጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስን “ከፍተኛ ደረጃ አደጋ” ብሎ አውጆታል። ይህንንም ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች በዓለም የጤና ድርጅትና በፕሬዝዳንቱ ዶክተር ቴድሮስ ላይ እየተሰነዘሩ ነው። በተለይም ከአንዳንድ የምዕራባውያን አገራት ፖለቲከኞች በኩል እየተሰማ ያለው ቅሬታ ዶክተር ቴድሮስ ለምን የህንን ወረርሽኝ በጤና ድርጅቱ አሰራር መሰረት የመጨረሻ ደረጃ የሆነውንና “ፓንደሚክ” የተባለውን አዋጅ አያውጁለትም የሚል ሲሆን ዶክተር ቴድሮስና የጤና ድርጅቱ ሌሎች ባለሙያዎች ግን ይህ አዋጅ ታወጀ ማለት አለምን ወደ ከፋ ድንጋጤ ከማስገባትም አልፎ የሕብረተሰቡን እንዲሁም የመንግስታትን እንቅስቃሴ በመግታት የቫይረሱን መስፋፋት ለማስቆም የሚሰራውን ስራ ሊያስተጓጉል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

Image may contain: 3 people

ይህ በቻይና እንደ የለሊት ወፍ ባሉ የተለያዩ እንስሳት ስጋ በሚሸጥበት ሱፐርማርኬት እንደተወለደ የሚነገርለት የኮሮና ቫይረስ በቅርቡ በመካከለኛዋ ምስራቅ አገር ኢራን የገባ ሲሆን የኢራንን ህዝብ ለማረጋጋት በቴሌቭዥን ቀርበው መግለጫ ሲሰጡ የነበሩትን ምክትል የጤና ሚንስቴር ከሳምንት በሁዋላ እራሳቸውን ይዟቸዋል። በተጨማሪም ሌሎች 7 የኢራን ባለስልጣናት በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን የአገሪቱን ምክትል ፕሬዝዳንትም ይጨምራል። ኢራን እስካሁን ባጠቃላይ 66 የሚሆኑ ዜጎቿን በጉንፋኑ እንዳጣች ይፋ ብታደርግም አንዳንድ የውጭ ተንታኞች ግን የኢራን መንግስት ቁጥሩን አሳንሶ ነው የገለፀው ብለው ይገምታሉ።

ኢትዮጵያን ጨምሮ አብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት ኮሮና ወደ አገራቸው እንደገባ እስካሁን ይፋ ያደረጉት ነገር የለም። ነገር ግን ቫይረሱ ቀስ በቀስ ወደ ኢትዮጵያ ደጃፍ እየተቃረበ ያለ ይመስላል። በቀይ ባሕር ዳርቻ ያሉት ግብፅና ሳዑዲ አረብያ በሽታው እንደገባባቸው የገለፁ ሲሆን ናይጄርያ አልጄርያ ቱኒዝያና ሞሮኮ ጥቂት ሰዎች ቫይረሱን ተሸክመው ወደ አገራቸው እንደገቡ ገልፀዋል። ላለፉት ጥቂት ሳምንታት የኢትዮጵያ መንግስት ወረርሺኙ ወደ አገር ውስጥ ቢገባ በሚል ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ሲገልፅ ቆይቷል። በተለይም በቦሌ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፍያ ከተለያዩ አገራት በተለይም ከቻይና የሚመጡ መንገደኞችን የቫይረሱ ምልክት ካሳዩ በሚል አነስተኛ ምርመራ እያደረገ በማሳለፍ ላይ ይገኛል። ከነዚህ ውስጥ ጥቂት የሚሆኑ ትኩሳትና ሌሎች አጠራጣሪ ምልክቶችን ያሳዩ በራሪዎች ለልዩ ክትትል ከሕብረተሰቡ ወደተገለለ የጤና ማዕከል የተወሰዱ ሲሆን ከተጨማሪ የላብራቶሪ ምርመራ በኋላ ቫይረሱ እንደሌለባቸው በመረጋገጡ በነፃ ተለቀዋል።

እስካሁን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና በሳምንት 35 ጊዜ የሚያደርገውን ቀጥታ በረራ ቀጥሏል። በአለም ላይ አውሮፓውያንን ጨምሮ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ አገራት ከቻይና የሚመጣ ማንኛውንም በረራ ሙሉ በሙሉ ባቋረጡበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ1500 በላይ ተሳፋሪዎችን በየቀኑ ከቻይና ወደ አዲስ አበባ አሳፍሮ ማምጣቱ አንዳንድ የአፍሪካ ባለስልጣናትን አሳስቧል። የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ባሳለፍነው ወር ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ ለጊዜው እንዲያቋርጥ ጥያቄ አቅርበዋል። በሌላ በኩል በናይጄርያ አንድ የምክር ቤት አባል መንግስታቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድን የአዲስ አበባ ወደ ናይጄርያ በረራዎች እንዲያስቆም በመሞገት ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስክያጅ አቶ ተወልደ ገብረ መድህን በበኩላቸው አየር መንገዱ በረራውን ማቋረጡ ቫይረሱን የግድ ያስቆመዋል ማለት እንዳልሆነ ገልፀው የአየር መንገዱ ቋሚ ደንበኞች በሆኑ በርካታ ቻይናውያን ላይ በችግራቸው ጊዜ አየር መንገዱ ፊቱን ማዞር እንደማይገባው ስለሆነም ወደ ቻይና የሚደረገው በረራ እንደማይቋረጥ አስታውቀዋል። አቶ ተወልደ ምናልባት ውሳኔያቸውን የገለፁበት መንገድ አጥጋቢ ያልሆነና ሕዝቡን አሳማኝ በሆነ መልኩ ላይሆን ይችላል የአየር መንገዱ ውሳኔ ግን ትክክለኛና ምክንያታዊ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቻይና በተጨማሪ ወደ ደቡብ ኮርያ፣ ጃፓን፣ ሲንጋፖር፣ ማሌዥያ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ፊሊፒንስ፣ ሆንግ ኮንግ፣ ቬትናምና ሌሎች የእስያ አገራት በቀጥታ ይበራል። ታድያ አብዛኛዎቹ ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ የሚበሩ መንገደኞች በስራ ነክ ጉዳዮች የሚጓዙ በመሆናቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን ቀጥታ በረራ ስላቆመ ሃሳባቸውን ቀይረው የሚቀሩ አይደሉም። ከላይ የተጠቀሱትን ሌሎች የጎረቤት አገራት እንደ መሸጋገርያ በመጠቀም በቀላሉ ወደ ኢትዮጵያ ከመግባት የሚያግዳቸው ነገር ይኖራል ማለት አይቻልም። ይባስ ብሎም በተለያዩ አየር መንገዶች ወይም መሸጋገሪያ አገሮች አቆራርጠው ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ተጓዦችን በቦሌ አየር ማረፍያ እያሳደዱ መመርመርና መቆጣጠር ለኢትዮጵያ መንግስት ሌላ ያልታሰበ ራስ ምታት በመሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በራሱ አቋም ፀንቶ መቆሙ ሊደገፍ የሚገባው ይሆናል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን እስከ አምስት ጊዜ ወደ ቻይና በመብረር ለአገር የሚያስገኘው ከአንድ ሚልዮን ዶላር በላይ የለት ገቢ ለአገሪቷ ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተወፅኦ ከግምት ሊያድር ይገባል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ መንግስት ወደ አገር ውስጥ መግባቱ ለማይቀረው ይህ የጉንፋን ቫይረስ ከወዲሁ ጥንቃቄ የተሞላበት ዝግጅት ሊያደርግ ይገባዋል። ጉንፋኑ በአሁኑ ሰዓት በአውሮፓ አገራትም ጭምር በፍጥነት እየተስፋፋ በመሆኑ በቦሌ አየር ማረፍያ የሚደረገው ምርመራ ከቻይና በሚመጡ መንገደኞች ላይ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም የዓለም ክፍል በሚመጡት እንግዶችም ሆነ ዜጎች ላይ መደረግ አለበት።

በተጨማሪም እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥርና መጨናነቅ ባለባቸው ከተሞች ላይ ትኩረት በማድረግ ሆስፒታሎችና ጤና ጣብያዎች በቂ የሆነ ቁሳቁስ እንዲሟላላቸው እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ለህሙማን እንክብካቤ በሚያደርጉበት ወቅት እራሳቸውን ለቫይረሱ አደጋ እንዳያጋልጡ የሚረዱ ጭምብሎችና ጓንቶች የመሳሰሉትን ማሟላት ይኖርበታል። ከዚያም አልፎ የጤና ባለሙያዎች አንድ ሰው ቫይረሱ በቀላሉ እንዳይዘው እጁን ደጋግሞ መታጠብ እንዳለበት ከዛም ባለፈ አንዴ በቫይረሱ ተጠቂ ከሆነ በኋላ በርከት ያለ ፈሳሽ እንዲወስድ እየመከሩ በመሆኑ በከተሞች ያለው የቧንቧ ውሃ አቅርቦት በተቻለ መልኩ በጥቃቅን ምክንያቶች እንዳይቋረጥ ቢደረግ ህዝቡ እራሱን እንዲጠብቅ ይረዳዋል።

ሌላውና ዋነኛው ቅድመ ዝግጅት መሆን ያለበት ህዝቡ ስለ ቫይረሱ በቂ መረጃ እንዲኖረውና የተሳሳተ አመለካከት በመያዝ ወደ አላስፈላጊ ውዥንብር እንዳይገባ ቀድሞውኑ ማስተማሩ ግድ ይላል። ለምሳሌ በአዲስ አበባ ከተማ የቫይረሱ መግባት ቢታወጅ ሕዝቡ በትንሽ በትልቁ ባስነጠሰው ቁጥር በድንጋጤ ወደ ጤና ማዕከላት ሊሮጥ ስለሚችልና በሆስፒታሎች ትርምስ ስለሚፈጥር በትክክል የህክምና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች በወረፋ ምክንያት እርዳታ ሳያገኙ እንዳይቀሩ ያሰናክላል። እንደዚህ አይነት የህዝብ መደናገጥን ሊያባብሱ የሚችሉ ሃሰተኛ ወሬን በፌስቡክና ሌሎች ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የሚያሰራጩ አክቲቪስቶች ይህ ተግባራቸው በአገሪቷና በሕብረተሰቡ ላይ ትልቅ ጉዳትን ሊያደርስ እንደሚችል በማስገንዘብ በማወቅም ሆነ በአለማወቅ ከሚፈፅሟቸው አባባሽ ተግባራት እንዲቆጠቡ መምከር ያስፈልጋል።

ምናልባት በከተሞች የሕዝቡ መደናገጥ ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ከፍቶ ቢወጣና በቁሳቁስና ወይም እህል እጥረት ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶችን ለመግታት የመከላከያ ሃይሉ የማረጋጋት ሚና ለመወጣት እንዲችል እቅድ በመንደፍ በተለይም ደግሞ ቫይረሱ በመከላከያ አባላት ካምፖች ውስጥ ገብቶ እነሱን እራሳቸውንም እንዳያሸብር ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

የኮሮና ቫይረስ እስካሁን በዓለም ላይ ያለውን የሰዎች የለተ እለት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የገታ ባይሆንም በቻይና አብዛኛዎቹን ፋብሪካዎች ያዘጋ ሲሆን በአንዳንድ የአውሮፓ አገራት የህዝብ መጓጓዣ የሆኑ እንደ ባቡርና አውቶብስ የመሳሰሉት ባዷቸውን እንዲንቀሳቀሱ አስገድዷል። በሰሜን አሜሪካም ዋሺንግተን በተባለችው የአሜሪካ ግዛት ውስጥ ያሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የተዘጉ ሲሆን በጃፓን ደግሞ በአገሪቱ ያሉ ትምሀርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ ተደርጓል። ይህ ወረርሺኝ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ትፅዕኖ በማሳደር ላይ ይገኛል። በአሜሪካ አውሮፓና ኤስያ ያሉ የአክስዮን መገበያያዎች የካምፓኒዎች አክስዮን ዋጋ በአንድ ሳምንት ውስጥ እስከ 8 ፐርሰንት እንዲወርድ አድርጎታል። በኢትዮጵያም ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገውን የንግድ እንቅስቃሴ በአብዛኛው የሚገታ በመሆኑ በጥቁር ገበያ ላይ ያለው የብር የመግዣ አቅም ተጠናክሮ የዶላር ዋጋ እስከ መርከስ ወይም ቢያንስ ከዚህ በፊት የዶላር ዋጋ ሲጨምርበት የነበረውን ፍጥነት እንደሚቀንሰው ይገመታል። ቫይረሱ ኢትዮጵያ ከገባ ሊከተል የሚችለው የሸማቾች ወደ ገበያ ፍልሰት የእህል ዋጋን ሊያስወድደውና በሁለት አሃዝ ደረጃ ያለውን የዋጋ ግሽበት ይባሱኑን ሊያንረው ይችላል።

ኢትዮጵያ ከዚህ በመስፋፋት ላይ ካለው ቫይረስ ሙሉ በሙሉ የማምለጥ እድሏ እጅጉን አነስተኛ ቢሆንም በሌሎች ሁለት ምክንያቶች ግን እንደ ቻይና ጃፓን እንዲሁም አውሮፓ ካሉ አገራት በተሻለ መልኩ በሽታውን ልትቋቋም እንድትችል የሚረዱ ሁለት ምክንያቶች አሉ። በመጀመርያ ቫይረሱ ካጠቃቸው አጠቃላይ ታማሚዎች ውስጥ እስከ ሞት የሚደርሱት ከ5 ፐርሰንት የማይበልጡ ሲሆኑ ከሞቾቹ አብዛኛዎቹ በእድሜ የገፉ አዛውንቶች ወይም ሌላ ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ናቸው። ወደ 110 ሚልዮን የሚጠጋ የህዝብ ቁጥር እንዳላት የሚነገርላት ኢትዮጵያ ከ70 ፐርሰንት በላይ የሚሆነው ህዝቧ ከ30 ዓመት እድሜ በታች ያለ ነው። ስለዚህም በቫይረሱ ተጠቂ ቢሆን እንኳን እስከ ሞት የመድረስ እድሉ አነስተኛ ነው። በአንፃሩ እንደ ጃፓን እና ጣልያን ያሉት ኮሮና በፍጥነት እየተስፋፋባቸው ያሉ አገራት የህዝባቸው አማካይ ዕድሜ ከኢትዮጵያ በጣም ከፍ ያለ በመሆኑ በበሽታው የሚሞትባቸው ሰው በርከት ያለ ነው። ሌላው የኮሮናን ቫይረስ መስፋፋት ከሚያባብሱ ሁኔታዎች አንዱ የከተሞች መጨናነቅ ነው። ነገር ግን በኢትዮጵያ ያለው ከ80 ፐርሰንት በላይ የሚሆነው ህዝብ በግብርና ላይ የተሰማራና ከከተሞች ውጪ ያለ በመሆኑ ረዘም ላለ ጊዜ እራሱን እየመገበ ከከተማው ህዝብ ተገልሎ የመቆየት ብቃት ያለው ነው።

ከዚህም በመነሳት የኮሮና ቫይረስ ከሚያመጣው የጤና መታወክ እጅጉን በባሰ በሕብረተሰቡ መደናገጥ ሊፈጠር የሚችለው አለመረጋጋት ለኢትዮጵያ ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ኢትዮኖሚክስ ያሳስባል!

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -