Sunday, April 11, 2021

የምርጫ መቃረብን ተከትሎ በአሜሪካ የጦር መሳርያና የጥይት ገበያ ተጧጡፏል

Must Read

በአክሱም ከተማ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

  ተቀማጭነቱን በለንደን ከተማ ያደረገውና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ክትትል የሚያደርገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰአታት በፊት ባወጣው ባለ 25...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊል ድርሻ ለቱርክ መንግስት ሊሸጥ ነው

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እስከ...

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሸጠችው ቦንድ ዋጋው እያሽቆለቆለ ነው

ከውጭ ባለሃብቶች 1 ቢልዮን ዶላር ለመበደር በ2007 እ.ኢ.አ ኢትዮጵያ የሸጠችው ቦንድ በአየርላንድ የቦንድ ገበያ ላይ ባለሃብቶቹ እርስ በርስ የሚገበያዩበት...

በመጭው ጥቅምት መጨረሻ ላይ የሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መቃረብን ተከትሎ በአሜሪካ የተለያዩ አውቶማቲክ ጠመንጃዎች፣ ሽጉጦችና ጥይቶች ተፈላጊነት እጅጉን ጨምሯል። በደቡባዊው የአሜሪካ ክፍል በምትገኘው የአሪዞና ክልል አነስተኛ የጦር መሳርያዎችን የሚሸጥ አንድ ኩባንያ በሶስት ወራት ውስጥ ብቻ የሽያጩ መጠን በ125 ፐርሰንት ወይም ከእጥፍ በላይ መጨመሩን አስታውቋል። በተለይም ለአደን፣ ለስፖርትና እራስን ለመከላከል ለሚያገለግሉ መሳርያዎች ያለው ፍላጎት በመጨመሩ ገዢዎች በትእዛዝ እስከ ማሰራት መጀመራቸውንና ኩባንያው እስካሁን 45 ሚልዮን ዶላር ቅድመ ክፍያ ቢቀበልም በወቅቱ መሳርያዎቹን ማስረከብ አልተቻለም ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው ለፋይናንሻል ታይምስ ገልፀዋል።

ከዚህ በፊት ምርጫ ሲቃረብ ቀድሞውኑም መሳርያ የነበራቸው ሰዎች ጥይት ማከማቸት የተለመደ የነበረ ቢሆንም ዘንድሮ ግን የሽጉጥና ጠመንጃ መሸጫዎችን ያጨናነቁት ከዚህ በፊት መሳርያ ያልነበራቸው አዲስ ገዥዎች ናቸው። ይህም ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ በመጣው የወንጀል መስፋፋት፤ እንዲሁም በምርጫው ምክንያት ሊከሰት የሚችል አመፅና ግጭት በበርካቶች ዘንድ ስጋት መፍጠሩን ያሳያል።

ባሳለፍነው ግንቦት ጆርጅ ፍሎይድ የተባለ አንድ ጥቁር አሜሪካዊን በአደባባይ በፖሊሶች መገደል ተከትሎ የተቀሰቀሰ አመፅ ወደ 1 ቢልዮን ዶላር የሚገመት ውድመትን ሲያስከትል ህይወታቸውን ያጡም አሉ። ሁለት ፖሊስ ጣብያዎችንና አንድ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ ቤትን ጨምሮ ባንኮች፣ ሱፐር ማርኬቶች፣ መኖርያ ህንጻዎችና ሌሎች የንግድ ቦታዎች የተቃጠሉ ወይም የተዘረፉ ሲሆን በወቅቱ ጦር መሳርያን የታጠቁ ነጭ አመሪካውያን ሱቆቻቸውንና መኖርያ ቤታቸውን ጠመንጃ አንግተው በር ላይ በመቆም ሲጠብቁ ተስተውለዋል። በጆርጅ ፍሎይድ መገደል ከተቆጡ ወጣቶች ጋር በቁጥር ሊመጣጠኑ ያልቻሉት ፖሊሶች ጣብያቸውም ሆነ ከተማው ሲቃጠል ጥለው መሸሻቸው በሕብረተሰቡ ዘንድ ሽብር እንዲፈጠርና ፖሊሶቹም ከአደጋ አያድኑንም የሚል እምነት እንዲፈጠር አድርጓል። ሚኒሶታ በመባል በምትታወቀው በሰሜኑ የአሜሪካ ክፍል በምትገኝ ክልል ውስጥ የተቀሰቀሰው ይህ አመፅ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተዛምቶ ከኒውዮርክ እስከ ካሊፎርንያ እንዲሁም እስከ ዋሺንግተን ዲሲ ድረስ ከፍተኛ ውጥረትን አስከትሎ ነበር።

በሌላ በኩል በተቃውሞ ሰልፍ ወቅት በአንድ አንድ አክራሪ ነጮች ጥቃት ይደርስብናል በሚል ስጋት ጥቁር ሰላማዊ ሰልፍ ታዳሚዎች እራሳቸውን ማስታጠቅ መጀመራቸው ደግሞ የግጭት መከሰት እድሉን እያሰፋው ይገኛል። ታድያ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አንዴ ምርጫ ይራዘምልኝ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከተሸነፍኩና ምርጫው የተጭበረበረ መስሎ ከታየኝ ከስልጣኔ አልወርድም ማለታቸው ከምርጫው በኋላ በ50 ሚልዮን የትራምፕ ደጋፊዎችና በተቀረው የሕብረተሰቡ ክፍል መካከል ግጭት እንዳይከሰት ስጋት አለ።

ሌላው አሜሪካውያንን ሽጉጥና ጠመንጃ ለመግዛት እንዲሽቀዳደሙ እየገፋፋቸው ያለው ምክንያት የዴሞክራት ፓርቲው እጩ ጆ ባይደን የሪፐብሊካኑን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሸንፈው ስልጣን ይይዛሉ የሚል ግምት እየተጠናከረ በመምጣቱ ነው። ዴሞክራቶች ከሚታወቁባቸው ነገሮች አንዱ በጦር መሳርያ ግብይት ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር መደረግ አለበት የሚለው አቋማቸው ሲሆን የዶናልድ ትራምፕ ሪፐብሊካን ፓርቲ ደግሞ በአንፃሩ ሕገመንግስቱ ለዜጎች የሰጠውን መሳርያን የመታጠቅ መብት ያለምንም ክለሳ ማከበር አለበት ይላል። ለዚህም ነው የዴሞክራቱ ጆ ባይደን ማሸነፍ የጦር መሳርያ ገበያን ሊገድበው ይችላል በሚል ፍርሃት ሸማቾች ወደ እሽቅድድም የገቡት።

ይህንን ተከትሎም የጦር መሳርያና የጥይት አምራቾች የማምረት አቅማቸውን ለማሳደግ ፋብሪካዎቻቸውን ማስፋፋት ጀምረዋል።

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

በአክሱም ከተማ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

  ተቀማጭነቱን በለንደን ከተማ ያደረገውና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ክትትል የሚያደርገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰአታት በፊት ባወጣው ባለ 25...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊል ድርሻ ለቱርክ መንግስት ሊሸጥ ነው

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እስከ ግማሽ የሚጠጋ የባለቤትነት ድርሻ ለቱርክ...

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሸጠችው ቦንድ ዋጋው እያሽቆለቆለ ነው

ከውጭ ባለሃብቶች 1 ቢልዮን ዶላር ለመበደር በ2007 እ.ኢ.አ ኢትዮጵያ የሸጠችው ቦንድ በአየርላንድ የቦንድ ገበያ ላይ ባለሃብቶቹ እርስ በርስ የሚገበያዩበት ዋጋ ማሽቆልቆሉን ቀጥሏል። ከሶስት ሳምንታት...

ኤርትራ፤ ከተራራው ጀርባ ጠልቃ የቀረችው ሰሜናዊት ኮኮብ

  ኤርትራ ከባህር በሯ በዘለለ፤ ምድሯ ጥቅም የለውም የሚለው አስተሳሰብ ከኢትዮጲያ ጋር ፍቺ ሳትፈጽም በፊት ገዢ ሃሳብ ሆኖ ነው የኖረው፡፡ በደርግ ጊዜ የኢትዮጲያ ፕሬዝዳንት የነበሩት...

ኢኮኖሚያዊ ህልሙ በፖለቲካ ይጨናገፍ ይሆን?

  በ2013 እ.ኤ.አ. የአዲስ አበባ መስፋፋት የኦሮሚያ ገበሪዎችን አፈናቅሏል በሚል የተጀመረው የጸጥታ አለመረጋጋት ሰባት አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ይህ አመጽ አሁን ያሉትን ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ስልጣን አምጥቶ...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -