Saturday, January 22, 2022

የትምህርት ስርዐቱ ወደነበረበት ባይመለስ ይሻል ይሆን

ተማሪዎች ወደ ት/ቤት እየተመለሱ ነው

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

የኮሮና ቫይረስ በቀል በሚመስል መልኩ ዓለምን አናግቷል፡፡ በዓለም ላይ ከ40 ሚሊዮን በላይ በኢትዮጲያ ደግሞ ከ90 ሺህ ሰዎች በላይ ተጠቅተዋል፡፡ እንደ ጤና ጥበቃ እለታዊ መረጃ ከሆነ በኢትዮጲያ የሟቾች ቁጥር ከ1300 በላይ ደርሷል፡፡ ብዙዎች ቫይረሱ ኢትዮጲያ ላይ የተፈራውን ያክል አልጨከነባትም በሚለው ይስማማሉ፡፡
የኢትዮጲያ መንግስት ገና በጠዋቱ ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ ትምህርት ቤቶችን መዝጋት ነበር፡፡ ተማሪዎች በቤታቸው ከከረሙ ሰነባብተዋል፡፡ ሰሞኑን በኢትዮጲያውያን ካላንደር እስከ መስከረም 30 2013 ዓ/ም ድረስ ትምህርት ቤቶች ደረጃ በደረጃ እንዲከፈቱ የትምህርት ሚኒስቴር አዟል፡፡ ትዕዛዙ ለተማሪዎች እና ለአንዳንድ ወላጆች መልካም ዜና ይመስላል፡፡

ቢታኒያ ሰለሞን በአዲስ አበባ በአቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ በወረዳ 6 ፕሮሚስ ኪፐርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ትምህርቷን ልትጀምር በዝግጅት ላይ ናት፡፡ ሩብ አመቱን እንዳጠናቀቀች ያቋረጠችው የ7ኛ ክፍል ትምህርቷን ከቤት ውስጥ ተከታትላ፤ ለብሄራዊ ፈተና ዝግጅት ወደ ሚደረግበት ክፍል ተሸጋግራለች፡፡ ጥቅምት 13፤ 2013 ዓ/ም ኢትዮኖሚክስ ከወላጇ ጋር ሲያናግራት እፎይታው ወላጅና ልጅ ላይ ይነበብ ነበር፡፡ 

“አረ ልጄ ማበዷ ነበር፡፡ ቫይረሱን ወደ ወላጆቻቸው ማምጣታቸው ብቻ ከሆነ ክፋቱ እኛ ታመን እነሱ ከጭንቀት ቢተርፉ ይሻላል፡፡”

የቢታኒያ ወላጅ እናት ማርሸት አበበ ለኢትዮኖሚክስ የትምህርት ቤት ይከፈት ዜናው እንዳስደሰታት አብራርታለች፡፡ 

“ልጄ ለራሷ ጭምት ናት፤ እቤት ውስጥ ሆና የሆነ ነገር ብትሆንብኝስ?!”

የቢታኒያ ጭምትነት ለኢትዮኖሚክስ ጥያቄዎች መልስ በመግደርደሯ ጭምር ይገለጻል፡፡ ኮሮናን ተከትሎ የመጣው የቤት ውስጥ ክተቱ አዋጅ ጭምት ልጆች ላይ ያመጣው የስነልቦና ተጽዕኖ የባለሞያዎች መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ ከዚህ አንጻር የቢታኒያ ወላጆች ደስታ ምክኒያታዊ ነው ማለት ይቻላል፡፡

ልጆች ወደትምህርት ቤት ሲመለሱ፤ የትምህርት ስርዐቱ ግን ወደነበረበት መመለሱ ለብዙዎች የመከራከሪያ ጭብጥ ከሆነም እንደዚያው ሰነባብቷል፡፡ ለመሆኑ ምክኒያታዊ ትውልድ ባለመፍጠር የሚታማው የኢትዮጲያ የትምህርት ስርዐት ምን ይመስል ነበር፡፡ 

የትምህርት ስርዐቱ በወፍ በረር

ትምህርት በኢትዮጲያ ሲሰቃይ ነው የኖረው፡፡ እውነት ነው ብዙ ልጆች ወደትምህርት ቤቶች እየሄዱ ነው፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ከ99 በመቶ በላይ የሚሆኑ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ጀምረዋል ይላል፡፡ በተቃራኒው የቆሙ ድምጾች ይህ ቁጥር ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎችን ከግምት ውስጥ አላስገባም፤ በዚያ ላይ የወረዳ ካድሬዎች ሪፖርት ለማሳመር አስገድደው እየመዘገቡ ልጆች ትምህርት ቤት ስለመዋላቸው እንኳን የሚያውቁት ነገር የለም የሚሉ ክሶች ይቀርብበታል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የተለቀቀ አንድ ዶክመንት፤ ከ9 እስከ 12ኛ ድረስ ያሉትን ሳያካትት፤ በሌሎች ክፍሎች ላይ ያለው የተመዝጋቢ ተማሪዎች ቁጥር እያሽቆለቆለ ነው ይላል፡፡ በ2016/17 እ.ኤ.አ. 8ኛ ክፍልን ያጠናቀቁ የሴት ተማሪዎች ቁጥር 55 በመቶ ብቻ ሲሆን የወንዶቹ ደግሞ 55 በመቶ ብቻ ነበር፡፡ ትምህርታቸውን የሚተዉ ሴት ተማሪዎች ወደ 12 በመቶ ሲጠጋ ለወንዶቹ 11 በመቶን ይሻገራል፡፡ ዘጠነኛ እና 10ኛ ክፍል መመዝገብ ከሚገባቸው ተማሪዎች በተመሳሳይ አመት ትምህርታቸውን የጀመሩት ሴቶች 45 በመቶ ብቻ ሲሆኑ ይህ ቁጥር ለወንዶቹ ከ48 በመቶ በላይ ነው፡፡ 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ለሴቶች 25 ለወንዶቹ ደግሞ 24 በመቶ ድረስ ያሽቆለቁላል፡፡

ከኢህአዴግ በፊትና በኋላ ለሚለው ንጽጽር ያክል ዝርዝሩ ውስጥም ሳይገባ የግል ትምህርት ቤቶች መስፋፋት ወደ ትምህርት ቤቶች የሚሄዱ ተማሪዎች ቁጥር መጨመሩን እንደማሳያ ተጠቅሞ መስማማት ይቻላል፡፡ ዘመኑን ለሚመጥን የትምህርት ስርዐት መሃይምነትን ለማጥፋት ራዕይ ላላት አገር ምን ያክል ሰርታለች የሚለው ጭብጥ ግን ማከራከሩን ይቀጥላል፡፡

ጥራት፤ የኢትዮጲያ ትምህርት መግዛት ያቃተው የቅንጦት እቃ

ለሚያስተምሩበት የትምህርት ደረጃ አስፈላጊው የትምህርት ዝግጅት ስላላቸው መምህራን የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ እራሱ መረጃው ያለው አይመስልም፡፡ ለዚህ ፅሁፍ ዋቢ ያደረግነው ዶክመንት ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል ከሚያስተምሩ መምህራን መካከል 80 በመቶ ሴቶች እና 66 በመቶ ወንዶች ብቁዎች ሊሆኑ ይችላሉ ይላል፡፡ በ2013/14 እ.ኤ.አ. በዓለም አቀፉ የመጀመሪያ ደረጃ መማሪያ ቤቶች የጥራት ደረጃ መመዘኛ መሰረት ሶስተኛ ደረጃ እና ከዚያ በላይ የተሰጣቸው 21 በመቶ ብቻ ነበሩ ይላል፡፡

በተመሳሳይ አመት 46 በመቶው ትምህርት ቤቶች የትምህርት ማሰራጫ ቴክኖሎጂ አቅርቦት የነበራቸው ሲሆን 60 በመቶ የሚሆኑት የቴከኒክና ሞያ ተማሪዎች ደግሞ ብቁ አልነበሩም ይላል፡፡ በሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ በተደረገ የዳሳሳ ጥናት በአማርኛ፤ በኦሮሚኛ፤ ሶማሊኛ፤ ሲዳምኛ፤ ትግርኛ እና ወላይትኛ መሰረታዊ የሆነ የማንበብና የመጻፍ ክህሎት የነበራቸው 29 በመቶ ብቻ ነበሩ፡፡ 10ኛ ክፍል የብሄራዊ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል በ2013/14 እ.ኤ.አ. 64 በመቶ ሴቶች እና 76 በመቶ ወንዶች ሁለት ነጥብ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ሲሆን፤ በ12ኛ ክፍል መመዘኛ ደግሞ 350 እና ከዚያ በላይ ያመጡት 41 በመቶ ሴቶች እና 51 በመቶ ወንዶች ብቻ እንደነበሩ ዶክመንቱ ያብራራል፡፡

እ.ኤ.አ 2013/14 የትምህርት ማሰራጫ ቴክኖሎጂ የነበራቸው ትምህርት ቤቶች 46 በመቶ ብቻ ነበሩ

ለመሆኑ ለኢትዮጲያ ትምህርት ጥራት ለምን የቅንጦት ሆነ?

ኢትዮኖሚክስ ፋልከን አካዳሚ፤ ፍሬሂዎት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ኢትዮተርኪሽ የማህበረሰብ ትምህርት ቤት በተባሉ ተቋማት ውስጥ ከሚያስተምሩ መምህራን ጋር ባደረገው ውይይት የሚከተሉትን ችግሮች ነቅሶ አውጥቷል፡፡ 

የካሪኩለም ትግበራ ቁጥጥር ማነስ

ኢትየኮኖሚክስ ከቢታኒያ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ የፊዚክስ ትምህርት እንደሚከብዳት ተረድቷል፡፡ 

“ትምህርቱን የጀመርነው ስድስተኛ ክፍል እያለን ነበር ትላለች፡፡”

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት አቅጣጫ ይህ የትምህርት አይነት መጀመር ያለበት ሰባተኛ ክፍል ነው ይላል፡፡ የግል ትምህርት ቤቶች በራሳቸው የመሄዳቸውን ባህሪ መምህራኑንም ይስማሙበታል፡፡

አስራት አዲሱ የቅድመ ኮሌጅ ዝግጅት ክፍል የባይሎጂ መምህር ነው፡፡ 

“እውነቱን እንነጋገር ከተባለ የግል ትምህርት ቤቶች የፈለጋቸውን ነው የሚያደርጉት” ይላል፡፡

አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ደጋፊ መጻህፍት ሲኖሯቸው አንዳንዶቹ ሙሉ በሙሉ የመንግስትን መጻህፍት የማያስተምሩም አሉ፡፡ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ግን የመንግስትን መጻህፍት ያስተምራሉ፡፡ አንዳንዶች 50 በመቶ የማለፊያ ነጥብን አይከተሉም፤ ሌሎች ይከተላሉ፡፡ አንዳንዶች የትምሀርት ዝግጅትን እና የስራ ልምድን እንደ ትልቅ መመዘኛ ሲመለከቱ ሌሎች ዩኒቨርስቲ ገብቶ ከወጣ ማስተማር ይችላል የሚል ብሂል ያላቸው ይመስላል- በመምህራኑ ከተነሱት ወጣ ገባ አሰራሮች በጥቂቱ፡፡ 

የተጓዳኝ ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎችን የማቀድና የመተግበር ፍላጎት ማነስ

ተፈሪ አለምቀረ ስሙን መጥቀስ ባልፈለገው አንድ የግል ትምህርት ቤት ውስጥ ሲያስተምር ያጋጠመውን እንዲህ ለኢትዮኖሚክስ አጫውቷል፡-

“የአማርኛ አስተማሪ ነበርኩ፡፡ ተማሪዎቼ በቋንቋ ክህሎት እንዲዳብሩ በማስብ የስነጽሁፍ ምሽት በትምህርት ቤቱ ውስጥ እንዲዘጋጅ ጥያቄ አቀረብኩ፡፡ ፕሮፖዛል አዘጋጅ ተባልኩና አዘጋጅቼ አቀረብኩ፡፡ ከዚያም በወቅቱ ምክትል ዳይሬክተር የነበረው ወጣት ይህንን ልንፈቅድልህ አንችልም፤ ምክኒያቱም ተማሪዎች ስለፍቅር ሊጽፉ ይችላሉ ብሎ ከለከለኝ፡፡” ይላል፡፡

ስፖርታዊ ውድድሮች፤ የስነጽሁፍ ምሽቶች፤ አሊያም የስዕል እና የኪነጥበብ ክፍለጊዜዎች በአብዛኛው የግል ትምሀርት ቤቶች የማይታሰቡ ሆነዋል፡፡ በፊት በፊት በዚህ የማይታሙት የመንግስት ትምህርት ቤቶችም በጊዜ ሂደት እየተዉት ይመስላል፡፡ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ባንድ ወረዳ ውስጥ የአካባቢው ትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር የሚያደርጉበት ሜዳ ተሸንሽኖ ለግለሰብ ሱቆች እንዲሸጥ መደረጉም አንዱ ማሳያ አድርገው መምህራኑ ያነሳሉ፡፡

ቶፊቅ ናስር ቅድመ ኮሌጅ ዝግጅት ክፍል የፊዚክስ ትምህርት አስተማሪ ነው፡፡ የተጓዳኝ እንቅስቃሴዎች በካሪኩለሙ ላይ የሚኖራቸውን አዎንታዊ ተጽዕኖ እንዲህ ሲል ለኢትዮኖሚክስ አስረድቷል፡-

“ኤሌትሪክ ከረንት እኮ በአካላዊ ቁስነት ደረጃ የምታየው አይደለም፡፡ አትዳስሰውም፡፡ ይህን ጽንሰ ሃሳብ በደምብ ለመረዳት ምዕናብ ጥቅም ላይ መዋል አለበት፡፡ ስነጽሁፍ የምዕናብ አድማስን ያሰፋል፡፡ የሰፋውን ምዕናባዊ አድማስ ለፊሲክስ ታውለዋለህ፡፡ ላብራቶሪውን ተወው! እሱ በየትምህርት ቤቱ በራፉ ላይ ሳር በቅሎበታል፡፡ በምዕናብ እንኳን አንዳንድ ነገር እንድታሳይ አስፈላጊ ተጓዳኝ እራዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡”

ብዙ ማስተማር ይጠበቅብናል፤ ያለው ጥቂት ጊዜ ነው፡፡

አንድ የሁለተኛ ደረጃ የኬሚስትሪ አስተማሪ ከ250 ገጽ በላይ የሚሆን መጽሃፍ በ10 ወራት ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል፡፡ ለተማሪዎቹ ደግሞ ይህንን በ10 መጽሃፍ ማባዛት ያለባቸውን ጫና ያሳያል ይላሉ መምህራኑ፡፡ ተግባራዊ ትምህርትን ለማሰብ፤ ፍጹም አይቻልም፡፡ ዋናው ገጾቹን መጨረስህን ለበላይ አለቃህ ሪፖርት ማድረግ ነው፤ እንደ መምህራኑ ማብራሪያ፡፡

ለመምህራን የሚሰጥ የስልጠና እጥረት

በቅርቡ ቀድሞ ደቡብ ክልል በነበረው አካባቢ በተደረገ የመምህራን ምዘና፤ የሚያስተምሩትን ትምህርቶች የወደቁ መምህራን በብዛት መስተዋላቸው ተዘግቧል፡፡ የቅድመ ኮሌጅ ዝግጅት ክፍል የጂኦግራፊ አስተማሪ የሆነው በፍቃ ዳምጠው ለዚህ መምህራኑ መወቀስ እንደሌለባቸው ይከራከራል፡፡ 

“መምህራን የኢንተርኔት አቅርቦት በማያገኙበት፤ በአመት አንድ ጊዜ እንኳን ስልጠና በማያገኙበት ከመምሀራን ምን እንደሚጠበቅ አይገባኝም፡፡”

በፍቃዱ ጉዳዩን ከህክምና ባለሞያዎች ጋር ያነጻጽራል፡፡ የህክምና ባለሞያዎች ጊዚያቸው ከፈቀደላቸው እና ፍላጎቱ ካላቸው በአመት ምናልባት በመቶዎች የሚቆጠሩ ስልጠናዎች በተለያዩ ተቋማት አዘጋጅነት ማግኘት ይችላሉ፤ ይላል ለኢትዮኖሚክስ፡፡ 

በ1999 አ/ም የትምህርት ሚኒስቴር ባስተዋወቀው የትምህርት ጥራት ማዕቀፍ ውስጥ ተከታታይ የመምህራን ስልጠና በየትምህርት ቤቶቹ መሰጠት እዳለበት ቢያዝም እነዚህ ግን የግል ፕሮፋይልን ከማደራጀት የዘለለ እንዳልነበር መምህራኑ ይገልጻሉ፡፡

ሙስና

ትምህርት ቤቶች በሶስት መስፈርቶች መወዳደርን እንደ ብሂል የያዙት ይመስላል፡፡ እንግሊዘኛ ቋንቋን አቀላጥፎ መናገርን፤ የብሄራዊ ፈተናን የሚያልፉ ተማሪዎች ቁጥር እና የሳይንስ ፈጠራ ትዕይንት፡፡ ውድድሩ ባልከፋ፤ ውድድሩን ግን በሙስና ማለፍ የሚቻልባቸው መንገዶች መብዛታቸው ጥራትን የማይታሰብ አድርጎታል ይላሉ መምህራኑ፡፡ በቀላል ገንዘብ የወረዳ የትምህርት ቢሮ አላፊዎችን በመግዛት የግል ትምህርት ቤቶች ሁሉንም የጥራት መመዘኛ ማለፍ እንዲችሉ ያስችላቸዋል፡፡ 

“መምህራን እራሳችን በግል ቤታችን ያሉንን መጻህፍት እንድናመጣ ታዘን አንድ ክፍል ውስጥ በማስቀመጥ የመጻህፍት ቤት እንዳለ ተቆጥሮ ፍቃድ የተሰጠው ትምህርት ቤት ሰርቺያለው፡፡ መጻኅፍቱን ማዋጣታችን ሳይሆን ያዩትን እንዳላዩ እንድያልፉ ገንዘብ የተሰጣቸው የወረዳ አስተዳዳሪዎች ፍቃዱ እንዲሰጠው እንዳደረጉ ትዝ ይለኛል፡፡” ይላል የሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ክፍል ምክትል ሃላፊው አኗር ከድር፡፡”

የኢትዮጲያ ትምህርት ሁለት አስርተ አመታት ጉዞው ይህንን ይመስላል፡፡ ኢቲዮኖሚክስ ቢታኒያን በቤቷ ሲጎበኛት ቦርሳዋን አሳጥባ ዳግም ሊጀመር 15 ቀናት ብቻ ወደቀሩት ትምህርቷ ለመመለስ ተዘጋጅታለች፡፡ ተማሪዎች ወደቀደመው ትምህርታቸው ሲመለሱ የትምህርት ስርዐቱ ወደነበረበት እንዳይመለስ ጥረት ማድረግ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች አዲሱ እና ምናልባትም ረጅሙ ግብግብ አንደሚሆን ጥርጥር የለውም፡፡

የትምሀርት ሚኒሰቴር በዚህ ጽሁፍ ላይ ለተነሱት ሃሳቦች ማብራሪያ እንዲሰጠን ጠይቀን ምላሻቸውን አላገኘንም፡፡ ምላሻቸውን ስናገኝ ጽሁፉን ከልሰን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

- Advertisement -

2 COMMENTS

  1. ምን ያህል የታመመ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ እንዳለፍን ሳነሳ መሳሳቴን ለማሳመን የሚሞግቱኝ ብዙዎች ናቸው…..ያው አልፈርድባቸውም ከ’ሲስተማቸው’ አልወጣም…..ጥቂት መልካም የተደረጉልን ነገሮች (specially the spoon feeding part) ቢኖሩም….ቁጥር ሥፍር የሌላቸው ክልከላዎች÷አስጨናቂና ከባባድ ፈተናዎች÷ክህሎት እና ፍላጎትን ያላማከለ ትምህርት አሠጣጥ እንዲሁም ውሃ የማያነሡ ህጎች የብዙዎቻችንን በራስ የመተማመን ስሜት አሸማቀውታል ባይ ነኝ፡፡ ይህ ደሞ ብዙ ህልሞችን ጭንጋፍ ሆነው እንዲቀሩ የበዛ አስተዋፆ አድርጓል፡፡ ለሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና የሚያልፍ ተማሪ ብቻ ማፍራት ፍሬ ቢስ ነው(that is business) የሚሻለው የህይወትን ፈተና በሙሉ ልብ አሸንፎ ህልሙን እውን የሚያደርግ ትውልድ መፍጠር ነው፡፡ ያለፈው አልፏል ለሚመጣው ግን ጤናማ የትምህርት ሥርዓት ቢኖረን…..በዚያ ላይ ገጠር የሚማሩ ሴት ተማሪዎች ተዘንግተዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -