Saturday, January 22, 2022

የአሜሪካው ሪፐብሊካን ፓርቲ በኢትዮጵያ ላይ ያለው አመለካከትና የቻይና ሚና

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

ከሁለት ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በፓርላማ ቀርበው ቃለ መሃላ ከመፈፀማቸው ጥቂት ሳምንታት ቀደም ብሎ በአሜሪካ አንድ ውይይት ተካሂዶ ነበር። የምክር ቤት አባል በሆኑት ክሪስ ስሚዝ መሪነት ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ የተካሄደው ውይይት “አፍሪካ በቻይና” የሚል ርዕስ ነበረው። ይህ ውይይት ለአፍሪካ ከመቆርቆር እንደተደረገና በተለይም አንዳንድ የአህጉሪቱ አገራት የገቡበት የእዳ ክምር እንዳሳሰባቸው አሜሪካውያኑ በወቅቱ ገልፀው ነበር። ይሁን እንጂ ቻይና በአፍሪካ አገራት ዘንድ እያገኘች ያለችው ተቀባይነት አሜሪካንን እያሳጣት ነው የሚል ቁጭትና ስጋታቸውን የውይይቱ ተሳታፊዎች ሊደብቁ አልቻሉም ነበር ። የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የሆኑት የውይይቱ ሰብሳቢ ክሪስ ስሚዝ ኢትዮጵያን በስም ጠቅሰው በወቅቱ በስልጣን ላይ የነበረው የኢህአዴግ መንግስት እያካሄደው የነበረው አፈናና የሰብአዊ መብት ጥሰት ከቻይና እንደተማረው ተናግረው ኢትዮጵያ ለአካባቢው የሃይል አሰላለፍ ወሳኝ እንደሆነችም አስምረው ነበር።

ታድያ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በፍጥነት ነበር እኚሁ የምክር ቤት አባል ክሪስ ስሚዝ የልኡካን ቡድን እየመሩ አዲስ አበባ የተገኙት። በጉብኝታቸው ወቅትም ኢትዮጵያ የሚገባት የዓለምን ደረጃ የጠበቀ መሪ እንደሆነና በዶ/ር አብይ አማካኝነትም ይህንን አይነት መሪ እንዳገኘች ጠቅሰው አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር የጀመሩት በፖለቲካውና በኢኮኖሚው ላይ የሚደረግ ለውጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው መክረው ነበር ወደ ዋሽንግተን የተመለሱት። አጠር ያለ ቁመትና በከፊል የሸበተ ፀጉር ያላቸው የ67 ዓመቱ ክሪስ ስሚዝ ላለፉት 40 ዓመታት የኒውጀርሲ ክልልን በመወከል በአሜሪካ ምክር ቤት አባልነት ያገለገሉ ሲሆን በቀድሞው የኢህአዴግ መንግስት አመራር ወቅት በሰብአዊ መብት ጥሰቶችና የሕዝብ ድምፅ አፈና ላይ ከፍተኛ ተቃውሞን ሲያሰሙ ኖረዋል። ክሪስ ስሚዝ ኢህአዴግ ላይ ያሳዩት በነበረው ጠንካራ ተቃውሞም በዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ በሚኖሩ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት ዘንድ እውቅናን ሲያስገኘላቸው በተለይም ከግንቦት 7 አባላት ጋር ወዳጅነትን ፈጥረው ነበር። ታድያ ዘንድሮ ክሪስ ስሚዝ ያለወትሯቸው በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አስተያየትን ከመስጠት መቆጠብ ከጀመሩ ሰንበት ብለዋል።

ባሳለፍነው አርብ 20 የሚሆኑ የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ማይክ ፖምፔዮ አንድ ደብዳቤ ፅፈዋል። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ያለው አለመረጋጋት፣ የፀጥታ አካላት እየወሰዱት ያለው የሃይል እርምጃ፣ ሃይማኖትንና ብሔርን ያተኮሩ ግጭቶች፣ እንዲሁም አገሪቱ እየሄደችበት ያለችው ኢ ዲሞክራሲያዊ አካሄድ እያሳሰባቸው እንደሆነ ደብዳቤውን የፃፉት የምክር ቤት አባላት ገልፀው ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጀምራው ከነበረው የዴሞክራሲ ምህዳርን የማስፋት ሂደት እያፈገፈገች እንደሆነና የመናገር መብት መጣስ፣ የጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች መታሰር ብሎም የኢንተርኔት መዘጋት ለዚህ ማሳያ መሆኑንም አብራርተዋል። በመቀጠልም መረጋጋት የሌለባት፣ በብሔር ግጭቶች የተጠመደችና ከፖለቲካ የነፃ የፍርድ ስርአት የሌለባት ኢትዮጵያ ለአሜሪካ ዘላቂ አጋር መሆን እንደማትችል ስለዚህም በዶናልድ ትራምፕ ተሹመው የውጭ ጉዳይ ቢሮን የሚመሩት ማይክ ፖምፔዮ ከኢትዮጵያ መንግስት፣ ከተቃዋሚዎችና ከአክቲቪስቶች ጋር ተወያይተው በ60 ቀናት ውስጥ ለአሜሪካ ምክር ቤት ምላሽ እንዲሰጡ ደብዳቤው ይጠይቃል።

የደብዳቤው ይዘት የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ውጥረት እየተከታተለው እንደሆነ ቢያሳይም ዋናው ቁም ነገር ያለው ግን የፀሃፊዎቹ ማንነት ላይ ነው። በደብዳቤው ላይ ፊርማቸውን ካሰፈሩት 20 የምክር ቤት አባላት ውስጥ 19ኙ የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ሲሆኑ ስቲቭ ስቲቨርስ የተባሉት የኦሃዮ ክልል ተወካይ ብቸኛው የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል ናቸው። ይህ የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም። በብልፅና ፓርቲ የሚመራውን የኢትዮጵያ መንግስት በሚነቅፍ ደብዳቤ ላይ 1 የሪፐብሊካን አባል ብቻ መሳተፉ ሁለቱ የአሜሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን የአመለካከት ልዩነት የሚያሳይ ነው።

ዛሬ ዋይት ሃውስንና የላይኛውን (ከታችኛው የላቀ ስልጣን ያለውን) ምክር ቤት የተቆጣጠረው የሪፐብሊካን ፓርቲ በነፃ ገበያ የሚያምንና አሜሪካ ትቅደም በሚል መርህ የሚንቀሳቀስ ሲሆን ማንኛውም ከውጭ አገራት ጋር የሚደረግ ግንኙነት በአሜሪካ ጥቅም ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት የሚል አቋም ያለው ነው። አብዛኛውን የገንዘብ፣ የቁሳቁስና የፖለቲካ ድጋፍ የሚያደርጉት የሪፐብሊካኖቹ ማሕበራዊ መሠረት የሆኑት ቱጃር ባለሃብቶች፣ ከከተማ ውጭ የሚኖሩ አሜሪካውያንና እንዲሁም አክራሪ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ፓርቲው የሚያደርገውን ነፃ ገበያን የማስፋፋትና በዓለም መድረክ ላይ የአሜሪካን ጥቅም የማስከበር እንቅስቃሴዎች አጥብቀው የሚደግፉ ናቸው። በአጥባቂ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይነቱ የሚታወቀው የሪፐብሊካን ፓርቲ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ቻርልስ ዳርዊን የተባለው እንግሊዛዊ ፈላስፋ ዓለም የፉክክር መድረክ እንደሆነችና ትልልቅ አሳዎች ትንንሽ አሳዎችን እየዋጡ የሚኖሩበት ሂደት ተፈጥሮአዊ ግዴታ እንደሆነ ባስተማረው መሠረት በነፃ ገበያ ላይ የተመሰረተች ጉልበተኞች አቅመ ደካሞችን እየገፉ ያለ ገደብ የሚገዝፉባትን ዓለም ማየት ይሻሉ።

ሪፐብሊካኖች የአሜሪካንን ጥቅም ያስከብራሉ ካሏቸው ሁሉ ጋርም ይሰራሉ። በአንድ በኩል በካስትሮ ቤተሰቦች ስትመራ የኖረችውን ኩባን ዲሞክራሲያዊት አይደለችም በሚል ለ60 ዓመታት የዘለቀ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ቢጥሉባትም በሌላ በኩል ደግሞ ከአምባገነኖቹ የሳውዲ አረብያ ንጉሳውያን ቤተሰብ ጋር የጠበቀ ወዳጅነትን አፍርተዋል። በአሁኑ ወቅትም በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መሪነት በዓለም መድረክ ላይ ተቀናቃኛችን በሚሏት አዲሲቷ የዓለማችን ሃያል ቻይና ላይ ቀዝቃዛ ጦርነትን አውጀዋል።

ሪፐብሊካኖች ኢትዮጵያ በኢህአዴግ ዘመን ታራምደው የነበረው የልማታዊ መንግስት መር ኢኮኖሚ አሜሪካዊ ባለሃብቶችን የሚያገልና በአንፃሩ ቻይና በአፍሪካ ለተጎናፀፈችው ተፅዕኖ ፈጣሩነት ፈር የቀደደ ነው ብለው ስላመኑ ኢህአዴግ የነበረበትን የዲሞክራሲ ጉድለት እንዲሁም ያከናውናቸው በነበሩት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ ከፍተኛ ትኩረት አድርገው ነበር። የቻይና በአፍሪካ መስፋፋት እንቅልፍ የነሳቸው እንደ ክሪስ ስሚዝ ያሉ ፖለቲከኞችም በተደጋጋሚ በኢህአዴግ መንግስት ላይ ማእቀብ ለመጣል ሞክረዋል። ይሁን እንጂ እንደ የግብፁ አል ሲሲ የመሳሰሉ የተመረጠ መንግስትን ገልብጠው ስልጣን የያዙና በአገራቸው ሕዝብ ላይ ከፍተኛ አፈናን የሚያካሂዱ አምባገነኖች ጥቅማችንን ያስጠብቁልናል ብለው ስላመኑ ብቻ ጠንካራ ድጋፍን ሲያደርጉላቸው ይታያሉ።

ታድያ ዛሬ ዋሺንግተን ዲሲ ያሉት የምክር ቤት አባላት በፃፉት ደብዳቤ ላይ አንድ የሪፐብሊካን አባል ብቻ ቢኖር ብዙም የሚደንቅ አይደለም። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ አምባገነንነት ተጠናውቶት የነበረውንና ከምዕራባውያን ጋር በኢኮኖሚ ፖሊሲ ጉዳይ ፊትና ጀርባ ሆኖ የቆየው ኢህአዴግን አፍርሰው አዲሱን የብልፅግና ፓርቲን መመስረታቸው በሪፐብሊካኖች ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍን አስገኝቶላቸዋል። ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር የፈጠሩት ቁርኝትም ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አዲስ እየተቀረፁ ባሉ ፖሊሲዎች ላይ በእጅ አዙር እንዲሳተፉ እድልን ፈጥሮላቸዋል። በገንዘብ ሚንስትር ዴኤታው የሚመራው “አገር በቀል የኢኮኖሚ ለውጥ” እንደ ስሙ ሳይሆን አብዛኛውን ለውጦች እያካሄደ ያለው የምዕራባውያን ጉዳይ አስፈፃሚ የሚል ቅፅል ስም በተሰጣቸው ተቋማት ማለትም ዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ሞግዚትነት መሆኑን አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ስሞታ ሲያቀርቡ ተሰምተዋል።

በነዚህ የዋሺንግተን ዲሲ ተቋማት ግፊት ብሔራዊ ባንክ እያከናወነ ያለው ብርን የማዳከም ሂደት፣ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅትን እንድትቀላቀልና እንዲሁም ለዘመናት በመንግስት እጅ የቆዩ ድርጅቶችን ለመሸጥ እየተኬደበት ያለው ፍጥነት የአሜሪካና አውሮፓ ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ሲጎመጁበት የኖሩትን ጥቅም በመጨረሻም እንዲያገኙ የሚያመቻች ነው። አይ ኤም ኤፍ ግንቦት ወር ላይ ባወጣው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የሚተነትን ፅሁፍ ላይም መጪው ምርጫ የተጀመረውን የኢኮኖሚ ለውጥ ሊያደናቅፍ እንደሚችል አሳስቧል። ይህ የአይ ኤም ኤፍ ስጋት የአገሪቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከኢዜማ እስከ ህወሃትና ኦፌኮ ድረስ እያሰሙት ያለውን ተቃውሞ ከግምት በማስገባት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በምርጫ ከተሸነፉ የኢኮኖሚ ለውጡ ሊያጋጥመው የሚችለውን እንቅፋት በመስጋት ይመስላል።

ዛሬ በሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ የምትመራው አሜሪካ ከአዲሷ ባላንጣዋ ቻይና ጋር ከፍተኛ አተካራ ውስጥ ገብታለች። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በልማታዊ መንግስት የምትመራውን ቻይናን ለማዳከም ወደ አሜሪካ በሚገቡ የቻይና እቃዎች ላይ ቀረጥ ጥለዋል፣ እንደ ቲክ ቶክ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን አግደዋል፣ በተጨማሪም ህዋዌ የተባለውን የቴሌኮም ኩባንያ ከአሜሪካም አልፎ ከአውሮፓ እንዲባረር ጫና በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ከሁለት ዓመት በፊት በኢህአዴግ መንግስት ላይ ማእቀብ ለመጣል ህግ ፅፈው የአሜሪካ ምክር ቤት እንዲያፀድቀው ጎንበስ ቀና ሲሉ የነበሩት ክሪስ ስሚዝም በቻይና ላይ ከፍተኛ ተቃውሞን በማሰማት የሚታወቁ ናቸው። ከ4 ዓመት በፊት በተሰራ አንድ ጥናታዊ ፊልም ላይ ቻይና እንዴት የአሜሪካን ፋብሪካዎች ወደ አገሯ እንደወሰደችባቸው ብሶት ሲያሰሙ ይታያሉ። ለዚህም ነው የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ደጋፊ የሆኑና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነን የሚሉ እንደ ክሪስ ስሚዝ ያሉ ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባላት ሰሞኑን ዲሞክራቶች በፃፉት የኢትዮጵያን መንግስት የሚኮንን ደብዳቤ ላይ ፊርማቸውን ከማዋል የተቆጠቡት።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የውጭ ጉድይ ተጠሪው ማይክ ፖምፔዮ ለስራ ጉብኝት ዛሬ ወደ ሱዳን የተጓዙ ሲሆን የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ዛሬ ሱዳን ደርሶ መመለስም ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተገናኘ ነው የሚል ግምት አለ። ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ቁጥጥር ውጪ እየወጣ የሚመስለውን የኢትዮጵያን ውስጣዊ አለመረጋጋት ተከትሎ ማይክ ፖምፔዮም ሆነ የዶናልድ ትራምፕ መንግስት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከስልጣን እንዲወርዱ ፍላጎት ይኖራቸዋል ተብሎ ባይታመንም የአሜሪካንን ገፅታ ለመጠበቅ ሲባል ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አለመረጋጋት በቶሎ እንዲፈታ ግፊት ማድረጋቸው የማይቀር ነው። ይሁን እንጂ የቻይን በተወሰነ መልኩም ቢሆን ከኢትዮጵያ መገለል እፎይታን የሰጣቸው ሪፐብሊካን ጠቅላይ ሚንስትር አብይን መደገፍ እንደ የተሻለ አማራጭ ማየታቸውን የሚቀጥሉ ይሆናል።

- Advertisement -

5 COMMENTS

 1. ፅሁፉ ጥልቀት ይጎለዋል !
  ስለ ፊርማው ሲተነትን የምርጫ ግዜ መሆኑን ችላ ይላል።
  ስልሳ አመት ሙሉ ኩባን ያገዳት የሪፐብሊካን ፓርቲ ነው ብሎ ይደመድማል። false
  ታሪክን ካየን ለኢትዮጵያና መላው አፍሪካ የተሻለው ዴሞክራት ወይስ ሪፐብሊካን ?
  ቻይና እና ኢትዮጵያ አሁን ያላቸው ግንኙነት ምን ይመስላል?


  ..

 2. This is no economics this is poilitica…..hhhhhh this is no for china or USA this is about dr abiy….i think ethio with US has better advantage!

 3. This is no economics this is politica…..hhhhhh this is no for china or USA this is about dr abiy….i think ethio with US has better advantage!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -