Monday, April 12, 2021

የአርቲስት ሃጫሉን ግድያ ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማና በኦሮምያ ክልል ከፍተኛ አመፅ ተቀስቅሷል

Must Read

በአክሱም ከተማ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

  ተቀማጭነቱን በለንደን ከተማ ያደረገውና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ክትትል የሚያደርገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰአታት በፊት ባወጣው ባለ 25...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊል ድርሻ ለቱርክ መንግስት ሊሸጥ ነው

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እስከ...

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሸጠችው ቦንድ ዋጋው እያሽቆለቆለ ነው

ከውጭ ባለሃብቶች 1 ቢልዮን ዶላር ለመበደር በ2007 እ.ኢ.አ ኢትዮጵያ የሸጠችው ቦንድ በአየርላንድ የቦንድ ገበያ ላይ ባለሃብቶቹ እርስ በርስ የሚገበያዩበት...

ትላንትና ማታ ከምሽቱ 3፡30 በአዲስ አበባ ከተማ ገላን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመቶ የሞተውን አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ለመቅበር ዛሬ በከተማዋ በተሰበሰቡ ወጣቶችና በፀጥታ አስከባሪ ሃይሎች መካከል ግጭት ተከስቷል፡፡ የፌደራል ፖሊስ የተሰበሰቡትን ወጣቶች ለመበተን ሲል የተኮሰው አስለቃሽ ጭስ ይባሱን ቁጣ የቀሰቀሰ ሲሆን በማህበራዊ ድህረ ገፆች ላይ የሚዘዋወሩ በአግባቡ ያልተረጋገጡ ፎቶዎች እንደሚያሳዩት ጠዋት አነጋግ ላይ እራሱን ቄሮ በማለት የሚጠራው የኦሮሞ መብት ተሟጋች ቡድን ፒያሳ ወደሚገኘው የዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ሃውልት ዱላ ይዞ በማምራት ላይ ነበር፡፡

በተጨማሪም በኦሮምያ ክልል በአምቦ፣ ጅማ፣ አሰላ፣ ሻሸመኔ፣ አዳማ፣ ባሌ ሮቤ ወ.ዘ.ተ በመሳሰሉት ከተሞች አመፁ እየተቀጣጠለ የሄደ ሲሆን ድንጋይ በመደርደርና የተለያዩ ቁሳቁሶችን አስፋልት ላይ በማስተኛት መንገድ ሲዘጋ ታይቷል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎችም የጭነት ተሽከርካሪዎችና ቤቶች እንዲሁም በሻሸመኔ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት ተቃጥለዋል፡፡ ከሳምንት በፊት በኦ ኤም ኤን ቴሌቭዥን የኦሮምኛ ፕሮግራም ቀርቦ አወዛጋቢ ቃለ መጠይቅ አድርጎ የነበረው አርቲስት ሃጫሉ ከተለያዩ አካላት በፌስቡክ ዛቻ ሲደረግበት የነበረ ቢሆንም ገዳዮቹ እስካሁን በቁጥጥር ስር እንዳልዋሉና ፖሊስም በክትትል ላይ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

የተለያዩ ፖለቲከኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ አርቲስቶችና ሌሎችም በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ግድያውን እያወገዙ ይገኛሉ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው “የዚህን ክፉ ድርጊት ሙሉ የፖሊስ ምርመራ ሪፖርት እየተጠባበቅን እንገኛለን” ያሉ ሲሆን “ሀዘናችንን ራሳችንን በመጠበቅ እና ተጨማሪ ወንጀልን በመከላከል እንግለፅ ።” የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ የኦፌኮ አመራር አባል የሆኑት አቶ ጃዋር መሃመድም በበኩላቸው “የተኮሱት በኦሮሞ ልብ ላይ ነው….ሁላችንንም ልትገድሉን ትችላላችሁ ነገር ግን ልታቆሙን አትችሉም” ሲሉ ሃዘናቸውን ገልፀዋል፡፡ የሁለት ልጆች አባት የነበረው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው በ36 ዓመት እድሜው ሲሆን ለኦሮሞ መብት መከበርን በሚያስተጋቡት ዘፈኖቹ ይታወቅ ነበር፡፡

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

በአክሱም ከተማ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሙሉ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ

  ተቀማጭነቱን በለንደን ከተማ ያደረገውና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ክትትል የሚያደርገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰአታት በፊት ባወጣው ባለ 25...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊል ድርሻ ለቱርክ መንግስት ሊሸጥ ነው

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን እስከ ግማሽ የሚጠጋ የባለቤትነት ድርሻ ለቱርክ...

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሸጠችው ቦንድ ዋጋው እያሽቆለቆለ ነው

ከውጭ ባለሃብቶች 1 ቢልዮን ዶላር ለመበደር በ2007 እ.ኢ.አ ኢትዮጵያ የሸጠችው ቦንድ በአየርላንድ የቦንድ ገበያ ላይ ባለሃብቶቹ እርስ በርስ የሚገበያዩበት ዋጋ ማሽቆልቆሉን ቀጥሏል። ከሶስት ሳምንታት...

ኤርትራ፤ ከተራራው ጀርባ ጠልቃ የቀረችው ሰሜናዊት ኮኮብ

  ኤርትራ ከባህር በሯ በዘለለ፤ ምድሯ ጥቅም የለውም የሚለው አስተሳሰብ ከኢትዮጲያ ጋር ፍቺ ሳትፈጽም በፊት ገዢ ሃሳብ ሆኖ ነው የኖረው፡፡ በደርግ ጊዜ የኢትዮጲያ ፕሬዝዳንት የነበሩት...

ኢኮኖሚያዊ ህልሙ በፖለቲካ ይጨናገፍ ይሆን?

  በ2013 እ.ኤ.አ. የአዲስ አበባ መስፋፋት የኦሮሚያ ገበሪዎችን አፈናቅሏል በሚል የተጀመረው የጸጥታ አለመረጋጋት ሰባት አመታትን አስቆጥሯል፡፡ ይህ አመጽ አሁን ያሉትን ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ስልጣን አምጥቶ...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -