Saturday, January 22, 2022

የኢትዮጲያውያን የተባበረ ኢኮኖሚያዊ ክንድ በጨረፍታ

እያደገ የመጣው የቀጥተኛ በጎ አድራጎት ባህል እና ቸልተኛ ተመጽዋች

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

 

በረከት ኤልያስ በነሃሴ 12 2012 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በወረዳ 06 ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ ሆያ ሆዬ ለመጨፈር እየተዘጋጁ ነበር። ከአንድ ቀን በኋላ በሚደረገው የደብረታቦር በዐል ላይ ሆያ ሆዬ ለመጨፈር እየተዘጋጁ የነበሩትን ወጣቶች እድሜ ለተመለከተ ለዘመናት ከተለመደው ወጣ ሊልበት ይችላል፡፡

በእድሜ ትንሹ እኔ ነኝ ማለት ይቻላል፡፡ እኔ 25 አመቴ ነው፡፡

ይላል በረከት በዐሉ ካለፈ ከአንድ ወር በላይ ቢሆነውም፤ ለዚህ ጽሁፍ ኢትዮኖሚክስ ባናገረው ወቅት ለማስታወስ እየሞከረ፡፡

ይህ በዋናነት በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በሚከበረው በዐል ላይ የሚደረገውን ጭፈራ ከሁሉም ሃይማኖት የተውጣጡና እድሚያቸው ከ18 አመት ያልዘለለ ልጆች የሚሳተፉበት ሆኖ ለረጅም አመታት ቆይቷል፡፡ ከጥቂት አመታት ወዲህ ግን ጭፈራው በዋናነት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የሚሳተፉበት እየሆነ ከመምጣቱም ባለፈ ለዘመናት እንደነበረው ልምድ በጭፈራው ላይ የሚሳተፉት ልጆች በየቤቱ ጨፍረው የሚሰበስቡትን ገንዘብ በየአካባቢዎቻቸው በሚገኙ ሱቆች ላይ ተደርድረው ከረሜላና ማስቲካ እየገዙ አያጠፉትም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዓሉ ላይ የሚጨፍሩት እድሚያቸው ከፍ ያለ ወጣቶች መሆናቸው ብቻ ሳይሆን የሚሰበሰበው ከፍተኛ ገንዘብ የሚውልበትም አላማ የተለየ እየሆነ መጥቷል፡፡

ኢትዮኖሚክስ በረከትን በጭፈራው ከተሳተፉ በኋላ ምን ያክል ገንዘብ እንደሰበሰቡ ጠይቆት ነበር፡፡

ያን ቀን በኮሮና ምክኒያት ብዙ ሰዐት አልጨፈርንም፡፡ በዛ ላይ ብዙ ቤቶች አልዞርንም፡፡ ስለዚህ 6000 ብር ብቻ ነው የሰበሰብነው፡፡

ይላል በረከት ለኢትዮኖሚክስ፡፡

እንደበረከት ትውስታ ከሆነ ይህ እንደ ልምድ የተጀመረው በከተማይቱ በሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በሚኖሩ ወጣቶች ነው፡፡ በተለይ ጎፋ ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚተጠራው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ወጣቶች እንደቀልድ በመጣ ሃሳብ ሆያ ሆዬ ሊጨፍሩ ወጥተው ከ100 ሺህ በላይ ብር ሰብስበው ገቡ፡፡ (ኢትዮኖሚክስ በግሉ የገንዘቡን መጠን ማረጋገጥ አልቻለም፡፡) ይህንንም ገንዘብ በወቅቱ በአገሪቱ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክኒያት ለተፈናቀሉ ዜጎች መለገሳቸው በከተማው ተሰማ፡፡ ይህም ቀስ እያለ በየአካባቢው በሚገኙ ወጣቶች ዘንድ እንደባህል ሆኖ ቀጠለ፡፡

እንደነ በረከት የጥቂት አመታት ልምድ ከሆነ በወረዳው በሚገኙ የተለያዩ መንደሮች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የወጣቶች ቡድኖች ጨፍረው ያገኙትን ገንዘብ አንድ ላይ ይሰበስባሉ፡፡ በዚህ ገንዘብም በተወካዮቻቸው አማካኝነት፤ በየመንገዱ ለወደቁ ወገኖች ምግብ ያበላሉ፤ አልባሳትን ገዝተው ያለብሳሉ፡፡

ይህን ግን አሁን ማረግ አልተቻለም፡፡ በኮሮና ምክኒያት በየመንገዱ የወደቁ ወገኖችን መንግስት እራሱ ሰብስቦ በየማዕከሉ አስገብቶ እየረዳቸው ነበር፡፡ ስለዚህ ገንዘቡን በተመሳሳይ መንገድ ሰብስበን መንግስት ለኮሮና መከላከል ላስጀመረው የበጎ አድራጎት ፕሮግራም እንዲሆን ተደርጓል፡፡ 

ይላል በረከት፡፡

እያደገ ከመጣው የበጎ አድራጎት ባህል ተጠቃሚዎቹ የጎዳና ተዳዳሪ ኢትዮጲያውያን ብቻ አይደሉም፡፡ መዝሙር ነብዩን እናስተዋውቃችሁ፡፡ በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሴተኛ አዳሪ እናቱ የተወለደው መዝሙር፤ የ4ኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ መዝሙር ከእናቱ ጋር አይደለም የሚኖረው፡፡ እናቱ ተከራይታበት ከምትኖረው ግቢ ውስጥ ትታው ከኮበለለች በኋላ በአካባው ከሚገኙ ጥንዶች መካከል አንድኛው አባወራ አቶ ነብዩ ልጁን በአደራ ተቀብለው ለማሳደግ ቃል ይገባሉ፡፡

የአቶ ነብዩ በጥበቃ የሚተዳደሩ ባለቤታቸው ደግሞ የአዲስ አበባ መስተዳድር በየመንደሩ አደራጅቶ በጽዳት ስራ ካሰማራቸው ሴቶች አንዷ ናቸው፡፡ ተጨማሪ ልጅ በሃላፊነት ወስዶ ማሳደግ ከባድ እንደሆነ ለኢትዮኖሚክስ ይናገራሉ፡-

እንደው የቤት ኪራይ ስለሌለብኝ ነው እንጂ እሱስ የኔም አንድ ልጅ አለ ገና ተማሪ ቤት ያለ፡፡ እሱን ብቻውን ማሳደግ በራሱ ከብዶን ነው የኖርነው፡፡ በአሁን ጊዜ በኔና በባለቤቴ አቅም ሁለት ልጅ ማስተማር እጅጉን ከባድ ነው፡፡

ለአቶ ነብዩ ታዲያ ብስራት የሆነው ዜና የአዲስ አበባ መስተዳድር በቅርቡ ባንኮችን ሰብስቦ ያስጀመረው የበጎ ፍቃድ ዘመቻ ነው፡፡ አስተዳደሩ ከኮረና በኋላ ትምህርት ቤቶች ሲከፈቱ ለተማሪዎች ዩኒፎርሞች ከነተቀያሪያቸው፤ ምሳ ሳህኖች፤ ጫማዎች፤ የትምህርት ሙሉ ቁሳቁሶችን በበጎ አድራጎት ዘመቻው ማዘጋጀት ችሏል፡፡ ይህ ለበጎ አድራጊው የተደረገው በጎ አድራጎት ለአቶ ነብዩ እረፍትን ሰጥቷል፡፡

ኢትዮጲያዊ በመንገድ ላይ ቆመው እንዲሁም በሩን አንኳኩተው ለሚለምኑት ከመመጽወት ተሻግሮ በተደራጀ መልኩ እጅን መዘርጋትም እየለመደ ይመስላል፡፡ በግለሰቦች አስተባባሪነት ከሚጀመሩ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎች በቴክኖሎጂ ተደግፈው እስከሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች እንደባህል ቀስ በቀስ ኢትዮጲያውያን እየተሳተፉበት ነው፡፡

አቶ ያሬድ ሹመቴ ብዙዎቻችን በቅድሚያ የምናውቀው መታወቂያው ላይ የብሄር መግለጫ እንዳይጻፍ መንግስትን በመሞገቱ ወይንም በአድዋ ጉዞ አዘጋጅነቱ ሊሆን ይችላል፡፡ በባለፉት ሁለትና ሶስት አመታት ግን ያሬድ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በጸጥታ ችግር ምክኒያት ለሚፈናቀሉ ወገኖች በማህበራዊ ድህረ ገጽ በሚያሰባስባቸው የበጎ አድራጎት ስራዎች ይታወቃል፡፡ ያሬድ ጥሬ ገንዘብ በቀጥታ መሰብሰብ የራሱ እክሎች እንደነበሩበት እና በቀጥታ በባንክ አካውንት ገንዘብ መሰብሰብ እና ድጋፍን በአይነት መሰብሰብ ከተጀመረ ወዲህ ግን ውጤታማ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ይህ ጽሁፍ በተጠናቀረበት በጥቅምት 2012 ዓ/ም ያሬድ በወለጋ በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉት ኢትዮጲያውያን ጋር በተያያዘ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 200 ሺህ ብር ዋጋ ያላቸውን ቁሳቁሶች መረከቡን አስታውቋል፡፡

በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና የተደራጀ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ ቀስ በቀስ እየተለመደ ስለመምጣቱም የሚያሳዩ ምልክቶችን ማግኘት ይቻላል፡፡ አጋር ፈንድ በይሄነው አዲስ፤ ወንደወሰን እንዳለ እና ህሊና ሙላቱ በ2019 እ.ኤ.አ. የተቋቋመ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ድህረ ገጽ ነው፡፡ ድህረገጹን ለጎበኘ ኢትዮጲያውያን በፍቃዳቸው የሚሳተፉባቸው እና በግለሰቦች የተከፈቱ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ማዕቀፎችን ይመለከታል፡፡ ድህረገጹም ሆነ በዚህ መንገድ የሚደረገው የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ጅማሮ ላይ እንደመሆኑ ብዙዎቹ ማዕቀፎች ብዙ ገንዘብ ባይሰበሰብባቸውም፤ ኮሮና ሊያመጣ የሚችለውን ጫና ለመቋቋም የተከፈተው ዘመቻ ግን እስከ 5700 ብር እንደተሰበሰበበት ማየት ይቻላል፡፡

ወንደሰንን ለዚህ ጽሁፍ ኢትዮኖሚክስ አናግሮት ነበር፡፡

እኔና ጓደኞቼ የተለያዩ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን ፍለጋ እንወያይ ነበር፡፡ ትኩረታችንን ከሳቡት ነገሮች አንዱ ድጋፎችን በተደራጀ እና ግልጽነቱን በጠበቀ መልኩ ማስተባበር የሚችል ዌብሳይት መፍጠር ነበር፡፡ ብዙ ድጋፎች በየመንደሩ እንደሚሰበሰቡ እናውቃለን፡፡ ግን ግልጽነት የጎደላቸው እና የብዙ ሰዎችን አቅም ማደራጀት የሚችሉ አይደሉም፡፡ ይህንን ይፈታል ያልነውን የቴክኖሎጂ መፍትሄ ነው ይዘን የመጣነው፡፡

ይላል ወንደሰን፡፡ 

ሌላኛው ተመሳሳይ ድህረ ገጽ በ2018 እ.ኤ.አ. የተመሰረተውና ኢትዮጲያ ውስጥ በሚገኝ ቢቲኔት ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ እና አሜሪካን አገር በሚገኘው ደጋፊ ኢንክ በጣምራ የሚተዳደረው ደጋፊ የተሰኘው ድህረ ገጽ ነው፡፡ ይህም ድህረ ገጽ ኢትዮጲያውያን ከአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ሆነው ድጋፍ የሚያደርጉባቸው የተለያዩ ማዕቀፎች አሉት፡፡ በድህረ ገጹ የወፍ በረር ቅኝት አብዛኛዎቹ ማዕቀፎች ብዙ ገንዘብ መሰብሰብ እንዳልጀመሩ ቢያሳይም ለድሬ ዳዋ ነዋሪዎች የተከፈተው ዘመቻ ግን ከ79 ሺህ ብር በላይ እንደተሰበሰበበት ማየት ይቻላል፡፡

በኢትዮጲያውያን ተነሳሽነት ተጀምረው በኢትዮጲያውያን የኢኮኖሚ አቅም እየተንቀሳቀሱ ያሉትን ለማንሳት ያክል አንጂ አገሪቱ ለበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎች አዲስ አይደለችም፡፡ የኢትዮጲያ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ምዝገባ እና ቁጥጥር ኤጀንሲ የመዘገባቸው ከ3000 በላይ የበጎ አድራጎት ማህበራት እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እነዚህ ማህበራት የነበሩባቸው የአሰራር ማነቆዎች ቀለል እንዲሉ በመደረጋቸው ከዚህም የሚጨምሩበት እድል ይኖራል ቢባል ከእውነታው የራቀ አይሆንም፡፡

የበጎ አድራጎት ያዛልቃል?

የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደየ ቀያቸው ከመመለስ፤ የተራቡና የተጠሙትን ከማብላት እና የታረዙትን ከማልበስ የዘለለ ለዘላቂ ልማት ሊሆኑ ይችላሉ ወይ የሚለው ጉዳይ በጥቂቱም ቢሆን መቃኘት ተገቢ ነው፡፡

ሂዘር ግራዲ ገለልተኛ የበጎ አድራጎቶች እንቅስቃሴዎች አማካሪ ናቸው፡፡ በ2014 እ.ኤ.አ. በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ድጋፍ ባደረጉት ጥናት የቀጥተኛ የበጎ አድራጎት ድጋፎች ለአጣዳፊ ፍላጎቶች ከመዋላቸው በዘለለ በዘላቂነት የአገራትን ቀዳዳዎች ሊሞሉ ይችላሉ ይላሉ፡፡ ለዚህ እንደማሳያም ሰበሰብኩት ባሉት መረጃ መሰረት በ2011 እ.ኤ.አ. የበጎ አድራጎት ዘመቻዎች ከ59ቢሊዮን ዶላር በላይ ማሰባሰብ መቻሉን ያነሳሉ፡፡

ምንም እንኳን በጣሙን የተለመደውና መረጃም በብዛት የሚገኝለት ከሰሜኑ የአለም ክፍል ወደደቡቡ ክፍል ስለሚፈሰው የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ ቢሆንም፤ በጎ አድራጎት ግን በአብዛኛው የአለም ማህበረሰቦች ዘንድ በባህል እና በሃይማኖትም ጭምር የተደገፈ አስተሳሰብ መሆኑን ጸሃፊዋ ያነሳሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ከአንደኛው የደቡብ ክፍል ወደሌላው የደቡብ ክፍል የሚፈሰው የተደራጀ የበጎ አድራጎት ፍሰት እየጨመረ መምጣቱንም ጥናቱ ያነሳል፡፡ እንዳውም በ2030 እ.ኤ.አ. አብዛኛዎቹ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎች አፍሪካን በመሰሉ የአለም ክፍሎች የሚሽከረከር ሊሆን ይችላል ይላሉ ጸሃፊዋ- ምክኒያቱ ደግሞ ከ10 አመታት በኋላ የመካከለኛው ገቢን የሚቀላቀሉ አብዛናዎቹ ዜጎች የሚገኙት በነዚህ የአለም ክፍሎች በመሆናቸው ነው፡፡

የቻይና፤ የህንድ እና የብራዚል አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት መጠን በ2011 እ.ኤ.አ. ከአሜሪካን፤ ካናዳ፤ ፈረንሳይ፤ እንግሊዝ እና ጀርመን አጠቃላይ ምርት ጋር የሚገዳደርበት ደረጃ ደርሷል፡፡ በዚህም እንደ አለም ባንክ ከሆነ በ2011 እ.ኤ.አ. በከፍተኛ ፍጥነት እያደጉ ካሉት አነዚህ አገራት ወደ ድሃ አገራት የሚፈሰው ቀጥተኛ የበጎ አድራጎት ድጋፍ ከ12 እስከ 15 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ይላል፡፡

አፍሪካም ምጽዋትን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን መጽዋች በሆኑ ከሁለት ደርዘን በላይ በሚሆኑ ቢሊዬነሮቿ አማካኝነት የቀጥተኛ የበጎ አድራጎት ድጋፍን እየተማረች ነው ይላል ጥናቱ፡፡ ደቡብ አፍሪካ ብቻ በ2011 እ.ኤ.አ. 96 ሚሊዮን ዶላር የቀጥተኛ የበጎ አድራጎት ድጋፍ ለድሃ አፍሪካውያን አጋሮቿ ማድረጓን ጥናቱ ጨምሮ ያነሳል፡፡ የአፍሪካውያንን የቀጥተኛ በጎ አድራጎት ድጋፍ እና እያመጣ ያለውን ለውጥ በቅጡ መረጃ ማሰባሰብ ላይ ችግር ቢኖርም የአፍሪካ ባለጸጎች ድህነትን በዘላቂነት በመፍታት፤ በፍትህ እና ዲሞክራሲ እንዲሁም በትምህርት ዘርፎች አጋር አፍሪካውያንን የመደገፍ ልምዱ እያደገ ስለመሆኑ ግን ማስረጃ አለ ትላለች ሂዘር፡፡

የተደራጁ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎች ዘላቂ ጥቅማቸው በሚሰበስቡት ገንዘብ መጠን ምክኒያት ብቻም አይደለም፡፡ እንደ ሂዘር ከሆነ እነዚህ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎች ለተለያዩ አገራት ችግሮች የእውቀት እና ክህሎት ማደራጃ እና ልምድ መለዋወጫ፤ የተለየ የችግር መፍቻ መንገዶችን መሞከሪያ እና መተግበሪያም ሆነው ያገለግላሉ፡፡ ችግር አፈታታቸውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣታቱን ያነሳሉ፡፡ ለዘመናት እንደነበረው ለአንድ አካባቢ ችግር ከሌላ አካባቢ የመጣን መፍትሄ በተለያዩ ማህበረሰቦች ላይ መጫን ሳይሆን ችግር ያለባቸው አካባቢዎችን ውስጣዊ አቅምም በማጥናት፤ በመለየት እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ከሌሎች አከባቢዎች ከመጡ ልምዶች ጋር በማዳቀል ልማትን እያፋጠኑ ነው ይላሉ አማካሪዋ፡፡

የቀጥተኛ የበጎ አድራጎት ድጋፍ ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ ስለሚያመጣው እንድምታ ኢትዮጲያ በሚሊኒየም የልማት ግቦች ላይ ላስመዘበችው ውጤት እንደ አንድ ምክኒያት ሲነሳ መቆየቱም ይታወሳል፡፡ አገሪቱ በእናቶች ሞት ቅነሳ፤ ፍጹም ድህነትን ቅነሳ እንዲሁም በህጻናት ሞት ቅነሳ ረገድ ያስመዘገበችውን ውጤት ከዚህ የቀጥተኛ የበጎ አድራጎት ድጋፍ ጋር የሚያያዝ እንድምታ እንዳለው በብዙ ተነግሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ በግል ሲያስቧቸው የከረሙ የሚመስሉት ሶስት ፕሮጀክቶችን አስጀምረው ያስጨረሱበት መንገድ የቀጥተኛ የበጎ አድራጎት ድጋፍን ለዘለቄታዊ ልማት የመጠቀም ፍንጭን ያመላከተም ነበር፡፡ በብሔራዊ ቤተመንግስት ውስጥ የተገነባው አንድነት ፓርክ፤ የሸገር ፓርክ እንዲሁም እንጦጦ ፓርክ ከኢትዮጲያውያን በቀጥታ በተሰበሰበ የበጎ አድራጎት ድጋፍ አማካኝነት ተገንብተው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡ ጠቅላዩ ገበታ ለሸገር ብለው ባስጀመሩት ፕግራማቸው ከ3ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰባቸው፤ ለዚህም አንድ እራትን በቤተመንግስት ከእርሳቸውና ከባለቤታቸው ጋር ለመመገብ አምስት ሚሊዮን ብር በግለሰብ ያስከፈሉበት አካሄድ የድጋፍ አሰባሰብ ፈጠራ የተቀላቀለበት እንዲሆን ፍንጭ ሰጥቶ ያለፈ ነበር፡፡

በ2011 በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ቤተመንግስት ውስጥ የተዘጋጀ እራት 5 ሚልየን ብር የመግብያ ዋጋ ነበረው

ኢትዮጲያውያን የተባበረ ኢኮኖሚያዊ ክንዳቸውን ለተመረጡ የልማት አላማዎች የማዋሉ እንቅስቃሴ ቀጥሎ በቅርቡ ገበታ ለሃገርም ይፋ ተደርጓል፡፡ ይህ በተመሳሳይ 3ቢሊዮን ብር ይሰበሰብበታል ተብሎ የተገመተው እና ለአንድ እራት 10 ሚሊዮን ብር ይከፈልበታል የተባለውን እራት ጠቅላዩ አስጀምረዋል፡፡ አላማውን የጎርጎራ፤ወንጪ እና ኮይሻ የባህር ዳርቻዎችን ማልማትን ያደረገው የቀጥተኛ ድጋፍ ማሰባሰቢያው ሲጠናቀቅ በቀጥተኛ እና በተዘዋዋሪ በአስርሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች በዘላቂነት የገቢ ምንጭ የመሆን ውጤት እንደሚኖረው ተገምቷል፡፡

የኢትዮጲያውያን የተባበረ ኢኮኖሚያዊ ክንድ ምን ያህላል ቢሉ- በአፍሪካ በግዝፈቱ የመጀመሪያውን በአለም ደግሞ አራተኛውን የኤሌትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ያክላል ብሎ መመለስ ይቻላል፡፡ እንደነበረከት በየመንገዱ ለሚተኙ ወገኖች ወይንም እንደነ ያሬድ በጸጥታ እና በተፈጥሮ ችግር ምክኒያት ንፋስ ለገባው ወገን በፍጥነት ለመድረስ መመጽወትን ኢትዮጲያዊ ወትሮም ያውቃል፡፡ በተደራጀ መልኩ ቀጥተኛ የበጎ አድራጎ ድጋፍን በማሰባሰብ ለዘላቂ ልማት እና ድህነት ቅነሳ ማዋልን ቀስ በቀስ እየተማረም ይመስላል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመሩ የመጡት የፖለቲካ ውጥረቶች በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ላይ ስለፈጠሩት አሉታዊ ተጽዕኖ ለጥናት በሚበቃ መልኩ የተሰበሰበ መረጃ ኢትዮኒሚክስ ባያገኝም፤ የፕሮጀክት አስተባባሪዎች የመወያያ ርዕሶች ከሆኑ ግን ዋል አደር ብለዋል፡፡

እንቅፋቱ ሌላም መልኮች አሉት ይላል ወንደሰን ለኢትዮኖሚክስ፡-

እኛ ስንጀምር ካጋጠመን እንቅፋት አንዱ የምዝገባ ጉዳይ ነው፡፡ የተደራጀ የቀጥተኛ ድጋፍ ማሰባሰብ ሃሳብ ለአገሪቱ አዲስ በመሆኑ የትኛው የመንግስት አካል ነው የሚመለከተው ስለሚለው በግልጽ የተቀመጠ ህግ አልነበረም፡፡ ከብዙ ውይይት እና ገለጻ በኋላ ከበጎ አድራጎት እና ማህበራት ቁጥጥር ኤጀንሲ ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረም ችለናል፡፡

ይላል ወንደሰን ለኢትዮኖሚክስ፡፡

ወላጅ እናቱ ጥላው የሄደችውን መዝሙርን የለት ጉርሱን መስጠት ቁምነገር ቢሆን ኖሮ ኢትዮጲያ በድህነት አረንቋ ውስጥ ባልከረመች ነበር፡፡ መዝሙር ያጣውን ወላጅነት ተክቶ፤ አስተምሮ ለቁም ነገር ማብቃት የቀጥተኛ የበጎ አድራጎት ድጋፎች ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባዋል፡፡ የቀጥተኛ የበጎ አድራጎት ድጋፎች በዘላቂነት ለቁም ነገር እንዲበቁ ስልጣን ላይ ያለው አካል ጸጥታን በማስከበር እና የህግ ማነቆዎችን በመፍታት እረገድ የማይተካ ሚና እንዳለው መገንዘብ ያሻል፡፡ ኢትዮጲያውያን በተደራጀ መልኩ የበጎ አድራጎት ላይ ያላቸውን የተሳትፎ ባህል እያሳደጉ ሲመጡ ባህሉን በአግባቡ አለመጠቀም እንደመዝሙር ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጲያውያን ላይ እንቅፋት መሆን ነው፡፡ ኢንቨስትመነት እና በጎ አድራጎት የአጥር ላይ ወፍ ነው፤ ኮሽ ሲል ይበራል እንዲሉ፤ በሰጪው ትዝብት ውስጥ እንዳይጥል መጠንቀቅ ለይደር የሚባል አይደለም፡፡

- Advertisement -

10 COMMENTS

  1. I all the tjme used to read article in nerws papers but now as I am a user of net therefore from now I am using net for articles, thanks to web. Kendre Elwood Moth

  2. Aw, this was an exceptionally good post. Spending some time and actual effort to create a very good article?but what can I say?I procrastinate a lot and never seem to get anything done. Hermina Ario Jecho

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -