Saturday, January 22, 2022

የኮሮና ቫይረስን መስፋፋት ለመግታት ዋነኞቹ መሳርያዎች የመንግስት ግልፅነትና የተቋማት ቅንጅት ናቸው

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የኢትዮጵያ መንግስት ማድረግ የሌለባቸውን ነገር ማወቅ ከፈለጉ በቀላሉ የመካከለኛው ምስራቅ አገር የሆነችውን ኢራንን መመልከት በቂ ነው፡፡ የኢራን መንግስት ኮሮናን ለማቆም የተጠቀመበት ዘዴ ለሌላው ዓለም መጥፎ አርዐያ ቢሆንም ለብዙ መንግስታት ግን ትምህርት ሊሆን ይችላል፡፡ እስካሁን ከ11ሺ በላይ ዜጎች ተበክለውብኛል የምትለው ኢራን በአለም ካሉ አገራት ከቻይናና ጣልያን ቀጥሎ ከፍተኛ ጥቃት የደረሰባት ሶስተኛዋ አገር ናት፡፡ ይባስ ብሎም አንዳንድ የውጭ ባለሙያዎች በኢራን የቫይረሱ ተጠቂዎች ብዛት ይፋ ከተደረገው በከፍተኛ መጠን ሊበልጥ እንደሚችል ይገምታሉ፡፡ ታድያ ቫይረሱ ወደ ኢራን በገባበት የመጀመሪያው ሰሞን ላይ የአገሪቱ መንግስት ለህዝቡ በቂ የሆነ መረጃ በመስጠት ፋንታ የጤና ሚኒስቴር ድኤታ የሆኑትን ሰው በቴሌቭዥን በማቅረብ መንግስታቸው በቂ ዝግጅት እንዳደረገና ቫይረሱም በቁጥጥር ስር እንደሆነ ለህዝቡ እንዲገልፁ ማድረግን ነበር የመረጠው፡፡ ሆኖም ሚኒስትር ድኤታው በቀጥታ ስርጭት ሲተላለፍ የነበረውን መግለጫቸውን ሳይጨርሱ በህዝብ ፊት ጠንካራ ሳል ሲያስሉ ታይተዋል፡፡ ይህን መግለጫ ሰጥተው ብዙም ሳይቆዩ እሳቸው እራሳቸው የቫይረሱ ተጠቂ እንደሆኑ በምርመራ አረጋግጠዋል፡፡

ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ሰልፎችንና አመፆችን ሲያስተናግድ የቆየው የኢራን መንግስት በህዝቡ ዘንድ ተዐማኒነትን ማጣቱ የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት እንዳያስችለው ከፍተኛ እንቅፋትን ደቅኖበታል፡፡ ለምሳሌ መቀመጫቸውን በቴህራን ያደረጉት ባለስልጣናት ህዝቡ ከቤት እንዳይወጣና በብዛት ከመሰብሰብ እንዲቆጠብ እንዲሁም በመስጊዶችና ሌሎች የተቀደሱ ስፍራዎች በሮችን እንዳይስም ቢያስጠነቅቁም ህዝቡ ለባለስልጣናቱ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለቱ ቫይረሱ በከፍተኛ ፍጥነት እንዲሰራጭ አድርጎታል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ የመንግስት አካላት ለህዝቡ የሚያቀርቡት መረጃ እርስ በርሱ የሚጋጭና ያልተናበበ መሆኑ በህዝቡ ላይ የበለጠ መደናገርንም ፈጥሯል፡፡ በተለይም በቂ የሆነ መረጃ በወቅቱና በአግባቡ ለሕብረተሰቡ አለመቅረቡ ህዝቡ የተለያዩ የራሱን ግምቶች እንዲሰነዝርና ሃሰተኛ ዜና እንዲስፋፋ አበረታቷል፡፡ አሁንም ቢሆን ታድያ የኢራን ባለስልጣናት ሃላፊነትን ከመውሰድ ይልቅ ችግሩን እንደ አሜሪካ ባሉ ውጫዊ አካላት ላይ እያላከኩ ይገኛሉ፡፡

Image may contain: 6 people, crowd and outdoor

ይህ ኢራን ውስጥ እየታየ ያለው ክስተት ለኢትዮጵያውያን አዲስ ነገር አይደለም፡፡ መንግስት አልፎ አልፎ በስልጣን ዝቅ ያሉ አካላትን በመገናኛ ብዙሃን በማቅረብ ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ተዘጋጅታለች ከማለት ውጪ ለህዝቡ በቂ መረጃን ሲያቀርብ አይታይም፡፡ በርግጥ በርካታ የጤና ባለሙያዎችና ተቋማት ኢትዮጵያ ቫይረሱን እንድትቋቋም የተቻላቸውን ለማድረግ ላይና ታች እያሉ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም በሌሎች አገራት እንደሚታየው ከሆነ ቫይረሱን እነዚህ የህክምና ተቋማትና ባለሙያዎች ብቻቸውን የሚዋጉት አይሆንም፡፡ ፖለቲከኞች በተለይም ደግሞ የመንግስት ባለስልጣናት ለህዝቡ በቀጥታ መረጃ ማቅረብና የስነ ልቦና ዝግጅት እንዲያደርግ የማገዝ ከፍተኛ ሃላፊነት አለባቸው፡፡ ይህም መጀመር ያለበት ከላይ ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሲሆን ለህዝቡ ቀጥተኛና ሃቀኛ እንዲሁም ወቅታዊ መረጃን በመስጠት ይጀምራል፡፡ የመረጃ ማሰራጫ የሆኑ የሬድዪና የቴሌቪዥን ጣብያዎች ላይ ትኩረት መደረግ ያለበት ሲሆን በተለይም ደግሞ የሞባይል ኢንተርኔት አጠቃቀም በአገሪቷ በመስፋፋቱ መንግስት እንደ ፌስቡክ ያሉ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃንን ቢጠቀም መልዕክቱን በተሻለ መልኩ ማድረስ ይችላል፡፡ በአሜሪካና አውሮፓ አገራት እየተደረገ እንዳለውም የሞባይል ኢንተርኔት ዳታ ከፍተኛ ቅናሽ ቢደረግበት ወይም በነፃ ቢደረግ ከፍተኛ ጥቅም ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል የወረቀት ጋዜጣ ህትመቶች ቫይረሱን በንክኪ ሊያሰራጩ ስለሚችሉ ለጊዜው ቢታገዱ ይመረጣል፡፡

እንደ አዲስ አበባ ባሉ የህዝብ መጨናነቅ ያለባቸው አካባቢዎች ማንኛውም አላስፈላጊ የሆነ የህዝብ መሰብሰብ እንዲቆም አዋጅ ማውጣት ግድ ይላል፡፡ እንደ ስታድየም፣ ቲያትሮች፣ ጭፈራ ቤቶችና የተለያዩ የማህበራዊ መሰባሰቢያዎች እንዲዘጉ ማወጅ ቀጥሎም መሰረታዊ አገልግሎት ለህዝብ የማይሰጡና የቅንጦት አገልግሎት ተብለው የሚመደቡ ንግድ ላይ የተሰማሩ ተቋማት በሙሉ ስራ እንዲያቆሙ ከተቻለም በአዲስ አበባ ያሉ ትምህርት ቤቶች ባጠቃላይ እንዲዘጉ ማወጅ ተገቢ ነው ብሎ ኢትዮኖሚክስ ያምናል፡፡ እንደዚህ አይነት አዋጅ ሲወጣ በከተማው ላይ የሚደረጉ ግዴታ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ የሚረዳ ሲሆን የታክሲዎችና የባቡሮችን መጨናነቅ ስለሚቀንስ ሌሎች ለህዝብ አስፈላጊና መሰረታዊ አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎች በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ወደ ስራ ሲጓዙ የሚገቡትን ስጋት ሊያቃልልና ፈርተው በየቤታቸው እንዳይቀሩ ሊረዳ ይችላል፡፡

ሌላው ትኩረት መደረግ ያለበት በሆስፒታሎች ሲሆን እነዚህ ሆስፒታሎች የህክምና ቦታዎች እንጂ የቫይረሱ ዋነኛ መሰራጫ ማዕከል መሆን የለባቸውም፡፡ ለዚህም ተገቢ የሚሆነው እርምጃ ለጤና ባለሙያዎች በቂ የሆነ ትጥቅ በማቅረብ እራሳቸው የቫይረሱ ተጠቂዎች እንዳይሆኑ መከላከል እንዲሁም በሆስፒታሎቹ የውሃና ሳሙና አቅርቦትን በማመቻቸት ታካሚዎችም ሆኑ ሌሎች እጃቸውን በየጊዜው እንዲታጠቡ ማመቻቸት ይሆናል፡፡ በኢትዮጵያ እንኳን የቫይረስ ወረርሽኝ ተከስቶ ይቅርና በህክምና ተቋማት ያለው መጨናነቅ ከድሮውም ከአቅም በላይ በመሆኑ እድሜያቸው ከ40 በታች የሆኑ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምልክት ከታየባቸው እራሳቸውን ለሁለት ሳምንታት በማግለል በቂ ፈሳሽ በመጠጣትና እረፍት በመውሰድ ወደ ህክምና ሳይሄዱ ማገገም እንደሚችሉ ማስተማር ይገባል፡፡ በቻይና በተመዘገበው አሃዝ መሰረት ከአጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ውስጥ የህምና እርዳታ ያስፈለጋቸው 15 ፐርሰንት የሚሆኑት ብቻ ሲሆኑ ሌሎች 5 ፐርሰንት የሚሆኑት ደግሞ የድንገተኛ ህክምና እርዳታ ያስፈለጋቸው ነበሩ፡፡ ይህም ማለት ከአጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ውስጥ 80 ፐርሰንት የሚሆኑት ምንም አይነት ህክምና ሳያስፈልጋቸው ድነዋል፡፡ ነገር ግን የቻይና ህዝብ የአማካይ ዕድሜ ከኢትዮጵያ ከፍ ያለ በመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚጠቁ ህሙማን ውስጥ የህክምና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከ20 ፐርሰንትም የሚያንስ ይሆናል፡፡ እንደዚህ አይነት መረጃዎች በትክክል ለህዝቡ ከተሰራጩ የህክምና ማዕከላትን መጨናነቅ ሊቀንስ ይችላል፡፡ ከህመሙ ተጠቂዎች ውስጥ ለሞት የሚዳረጉት ሰዎች ቁጥርም በዝቅተኛ ደረጃ እንዲቆይ ይረዳል፡፡

Image may contain: text


የዚህን ቫይረስ ስርጭት ለመግታት ከመንግስት ቀጥሎ ከፍተኛውን ሃላፊነት መሸከም ያለባቸው የሓይማኖት ተቋማት ናቸው፡፡ በኢራንና በደቡብ ኮርያ ለቫይረሱ መስፋፋት ከፍተኛውን አስተዋፅኦ ያደረጉት አንድ ቤተክርስትያንና አንድ መስጊድ እንደሆኑ ታውቋል፡፡ የሓይማኖት መሪዎች ሃላፊነታቸውንና በህዝቡ ዘንድ ያላቸውን ተሰሚነት በመረዳት በሳይንስ ላይ የተመሰረተ፣ በመረጃ የተደገፈና ምክንያታዊ የሆነ ምክር በመስጠት ለሕብረተሰቡ ደህንነት ከፍተኛ አስተዋፅኦን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የአምልኮ ስፍራዎች በተለምዶ ከፍተኛ የህዝብ መጨናነቅ የሚፈጠርባቸው በመሆኑ ከተቻለ ሰዉ በነዚህ ስፍራዎች ከመሰብሰብ እንዲቆጠብ ቢያበረታቱም ይመረጣል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከህዝቡ መደናገጥ ጋር ተያይዞ እየታየ ያለው የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጥና እህል ነክ ምርቶች ዋጋ መጨመር እንዳይባባስ ይህም ወዳልተፈለገ የፀጥታ ችግር እንዳያመራ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ቫይረሱ ተሰራጭቶባቸው ሊሆን ይችላሉ ተብለው በሚጠረጠሩ ከተሞች መንግስት በፍጥነት በቂ ምርመራዎችን በማድረግ የተጠቁትን ከተሞች ሙሉ ለሙሉ በመዝጋትና ከሌሎች አካባቢዎች ጋር ግንኙነት እንዳይፈጥሩ መንቀሳቀስ ይኖርበታል፡፡ ይህ ከሆነ ሌላው የአገሪቱ ክፍል ለነዚህ ተጠቂ አካባቢዎች በቂ እህልን ማቅረብ እንዲችልና የምግብ እጥረት እንዳይከሰት ይከላከላል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የቀን ሰራተኞች እንዲሁም ጎዳና ተዳዳሪዎችና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አካላት በከተማው ያለው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ወደ መቆም በሚቃረብበት ጊዜ የለት መተዳደርያቸውንና ገቢያቸውን ስለሚያጡ ችግር ላይ እንዳይወድቁና ይባስ ብሎም ወደ ሌሎች ወንጀሎች ተገደው እንዳይገቡ የመመገብያ ማዕከላት በመንግስት፣ የሓይማኖት ተቋማትና ሕብረተሰቡ ትብብር ሊዘጋጁ ይገባል፡፡
የኮሮና ቫይረስ እስካሁን መድሃኒት ያልተገኘለት ሲሆን ክትባቱን ለገበያ ለማቅረብ እስከ አንድ አመት ሊፈጅ እንደሚችል ይገመታል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ዋነኛ አላማ መሆን ያለበት ክትባቱ ወደ ኢትዮጵያ እስኪደርስ የቫይረሱን የመስፋፋት ፍጥነት መቀነስና በአገሪቱ ኢኮኖሚና ፀጥታ ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ችግር መቀነስ ነው ሲል ኢትዮኖሚክስ ያሳስባል፡፡

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -