Saturday, January 22, 2022

የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የደቀነው አደጋና ይዞት የመጣው እድል

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ሰማያት ያለውን ከፍተኛ የበረራ አገልግሎት ፉክክር ተቋቁሞ ለአመታት የአህጉሩ ዋነኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ባለፉት 4 ወራት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በዓለም ላይ የተፈጠረውን የአየር ጉዞ መመናመን ተከትሎ እራሱን ለማዳን በአይነቱ ለየት ያለ እሽቅድድም ውስጥ ገብቷል፡፡ የኮሮና ቫይረስ የዓለምን ሕዝብ እንደዚህ ማሸበር ሳይጀምርና የአየር ተጓዦች የአውሮፕላን ማረፍያ ተርሚናሎችን አጥለቅልቀው በነበረበት ወቅት አየር መንገዱ በቀን እስከ 350 የመንገደኛ በረራዎችን ያደርግ የነበረ ሲሆን ዛሬ ግን እነዚህ በረራዎች ቆመው 10 ፐርሰንት የሚሆኑት ብቻ ቀርተዋል፡፡

ይህም አየር መንገዱን ለከፍተኛ የሒሳብ ቀውስ ዳርጎታል፡፡ ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንደገለፁት እስካሁን በአራት ወራት ውስጥ ብቻ የ550 ሚልዮን ዶላር ኪሳራ የተመዘገበ ሲሆን የያዝነው የፈረንጆች አመት ሲገባደድ ኪሳራው 1 ቢልዮን ዶላር እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡ ይህን ተከትሎም አየር መንገዱ በቢሾፍቱ ከተማ በ5 ቢልዮን ዶላር ወጪ እየገነባው ያለውን አዲስ አየር ማረፍያ ለጊዜው ግንባታውን እንዲያቆም አስገድዶታል።በየወቅቱ የሚደረግ የብድር ክፍያ፣ የኢንሹራንስ፣ የአውሮፕላን ሊዝና፣ በበርካታ አገራት ያሉ ሰራተኞች ክፍያ የአየር መንገዱ ዋነኛ ወጪዎች ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ቋሚ ወጩዎች ማለትም ስራ ቀዘቀዘም አልቀዘቀዘ የማይቀሩ ናቸው፡፡ አየር መንገዶች ገቢያቸው በድንገትና በከፍተኛ መጠን በሚወርድበት ወቅት አውሮፕላኖቻቸው በባንክ ሃራጅ ሊሸጡባቸው፣ ሰራተኞችን ለማባረር ሊገደዱና ያላቸው ገበያ በሌሎች ተፎካካሪዎች ሊወሰድባቸው ይችላል፡፡

ይሁን እንጂ የዚህ አይነት ኪሳራ ያጋጠመው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ብቻ አይደለም፡፡ በአሁኑ ሰዓት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየተስፋፋና ጥቂት የማይባሉ አገራትን ክፉኛ እያጠቃ ሲገኝ በሁሉም የአለማችን ክፍሎች አብዛኛው የመንገደኞች በረራ ቆሟል። በዚህ ምክንያትም የዓለማችን በጣም ትርፋማ የሚባሉትን የአሜሪካ አየር መንገዶች ጨምሮ ታላላቅ የሚባሉ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች በከፍተኛ የገንዘብ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል፡፡ የዶናልድ ትራምፕ መንግስት በአሜሪካ ላሉ እንደ ዴልታ፣ ዩናይትድና አሜሪካን አየር መንገዶች የ25 ቢልዮን ዶላር ድጋፍ በእርዳታና ዝቅተኛ ወለድ ባለው ብድር መልክ አቅርቧል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም በአውሮፓና እስያ ያሉ ግዙፍ አየር መንገዶች ወደ መንግስቶቻቸው የእርዳታ ጥሪ አድርገው ድጋፍ በማግኘት ላይ ይገኛሉ፡፡

ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተለይም የውጭ ምንዛሬን በማምጣት ከፍተኛ አስተዋፅኦን ሲያደርግ የቆየው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአገሪቱ ደካማ አቅም አንፃር እስካሁን ከመንግስት ሊደረግለት የሚችል በቂ ድጋፍ ባለመኖሩ እራሱን ችሎ ላለመውደቅ እየተጣጣረ ይገኛል፡፡ ለዚህም እንደ ዋነኛ ስልት አድርጎ የተነሳው ያሉትን በርካታ የበረራ መስመሮች በመጠቀም የጭነት ማጓጓዝ ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ ሆኗል፡፡
የጭነት ማጓጓዣ ክፍል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፍፁም አባዲ ለአንድ የሕንድ መፅሄት እንደገለፁት አየር መንገዱ እስካሁን በኮሮና ምክንያት ስራ ፈተው የተቀመጡ 22 የሚሆኑ ትላልቅና አነስተኛ የመንገደኛ አውሮፕላኖች መቀመጫ ወንበሮቻቸውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በማውጣት ወደ ጭነት ማመላለሻ ስራ እንዲገቡ ወስኖ ስራ ጀምሯል፡፡ የጭነት ጉዞ የሚደረግባቸው የበረራ መስመሮችም ወደ 70 ከፍ ያሉ ሲሆን ይህም በኮንትራት መልክ ለአጭር ጊዜ የሚደረጉ የጭነት ማመላለስ አገልግሎቶችን አይጨምርም፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት ምዕራብ አፍሪካን ከቻይና ሕንድና ሌሎች የእስያ አገራት፣ እንዲሁም የደቡባዊ አፍሪካ ሃገራትን ከአውሮፓና አሜሪካ በማገናኘት ኮሮናን ለመዋጋት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መድሃኒቶች፣ የፊት ጭምብል፣ የእጅ ጓንትና ሌሎች የህክምና መሳርያዎችን በማጓጓዝ ከፍተኛ አገልግሎት በአለም በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ለአንዳንድ ደንበኞች የውጭ መንግስታትን ጨምሮ አውሮፕላኖቹን በኮንትራት መልክ አከራይቶ ዜጎቻቸውን እንዲያጓጉዙ አግዟል፡፡

ይህ ታድያ የኢትዮጵያን ባንዲራ የተቀቡ አውሮፕላኖች ባልተለመዱ አገራት የአየር ማረፍያዎች ላይ እንዲታዩ አድርጓል፡፡ ባለፉት 2 ወራት ብቻ እንደ ኒው ኦርሊንስና ማያሚ በመሳሰሉት የአሜሪካ ከተሞች እንዲሁም በህንዷ ሃይድራባድ ከተማና በቀድሞዋ የሶቭየት ሕብረት አባል ቦስንያ የኢትዮጵያ አውሮፕላኖች ታይተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአየር መንገዱ በተለመዱ መስመሮች የጭነት ማጓጓዝ ስራው ተጧጡፏል፡፡ ለምሳሌ ከአስራ አምስት ቀናት በፊት አንድ የቦይንግ 777 ግዙፍ አውሮፕላን ከአዲስ አበባ 52 ቶን የሚመዝን የአበባና የግብርና ውጤቶችን ጭኖ ወደ ቤልጅየም ብራሰልስ ከበረረ በኋላ በቀጥታ ወደ ሆንግ ኮንግ በመጓዝ የህክምናና የኮሮና መከላከያ ቁሳቁሶችን ይዞ አዲስ አበባ ተመልሷል፡፡

አየር መንገዱ በአጭር ጊዜ ስልቱን ቀይሮ የተከሰተውን ችግር ለመጋፈጥ መወሰኑ በተወሰነ መልኩም የተጋረጠበትን አደጋ እንዲቋቋም እየረዳው ነው፡፡ የኮሮና ወረርሽኝ የፈጠረው መደናገጥ በርካታ አገራት በፍጥነት የፊት ጭምብልና ጓንት የመሳሰሉትን እንዲሁም የህክምና መሳርያዎችና መድሃኒቶችን ከቻይናና ከሕንድ ለመግዛት እየተጣደፉ በመሆናቸው በዓለም ላይ የጭነት ማመላለሻ አውሮፕላን እጥረት የተከሰተ ሲሆን ለጭነት ማመላለሻ የሚከፈለው ገንዘብ በዶላር ባለፉት 3 ወራት ብቻ በ6 እጥፍ ሊጨምር ችሏል፡፡ በተለይም አብዛኛዎቹ የአፍሪካም ሆነ የሌሎች አየር መንገዶች የዘረጓቸው የበረራ መስመሮች ቁጥራቸው አነስተኛ በመሆኑና የአፍሪካዎቹ ደግሞ ከልምድ ማነስ ጋርም በተያያዘ ኮሮና የፈጠረውን አዲስ እድል ሊጠቀሙበት ባለመቻላቸው ለኢትዮጵያ አየር መንገድና ሌሎች እንደ ኬንያ ላሉ ጥቂት ባለ ከባድ ሚዛኖች ትልቅ መንገድን ከፍቷል፡፡

ለአብነት ያክልም የቻይናው ባለሃብትና የአሊ ባባ መስራች አቶ ጃክ ማ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ቆስቋሽነት ለአፍሪካ አገራት የለገሷቸው በሚልዮኖች የሚቆጠሩ የኮሮና መከላከያ ቁሳቁስና የህክምና መሳርያዎች ወደ አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፍያ ከቻይና በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጭነው ከመጡ በኋላ ከ50 በላይ ለሚሆኑ የአፍሪካ አገራት እንዲያሰራጭ ኮንትራት የተሰጠው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ነበር፡፡

ዋና ስራ አስክያጁ አቶ ተወልደ እንዳሉት “በወቅቱ ትኩረታችን በጭነት ማመላለስ ላይ ነው፡፡ በአለም ላይ ከሰሜን ወደ ደቡብ እንዲሁም ከምስራቅ ወደ ምዕራብ የህክምና ቁሳቁሶች በአፋጣኝ እየተፈለጉ በመሆኑ የጭነት ማመላለስ ንግዳችን በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ በዛ ላይ የተወሰኑ የመንገደኛ አውሮፕላኖቻችንን ወደ ጭነት ማጓጓዣነት እየቀየርናቸው ነው” ብለዋል።

Image may contain: sky and outdoor

ይህ በእንዲህ እንዳለ አየር መንገዱ ጭነት በማጓጓዝ ከሚያገኘው ገቢም በተጨማሪ ሌላ እድል ተፈጥሮለታል፡፡ ከኢትዮጵያና ሌሎች ጥቂቶች በስተቀር ቀድሞውንም በኪሳራ የሚታወቁት የተለያዩ የአፍሪካ አየር መንገዶች የኮሮና ቫይረስ በቀላሉ ወደ ማይወጡበት አዘቅት ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ ለረጅም አመታት እየከሰረ አወዛጋቢ ሆኖ የቆየው የደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ የሚከፍለው ገንዘብ በማጣቱ ከሰራተኞቹ ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ የገባ ሲሆን ከገዛ ተቀጣሩዎቹ ጋርም ፍርድ ቤት ተካሷል፡፡ ባለቤትነቱ የደቡብ አፍሪካ መንግስት የሆነው አየር መንገድ ያለፉት 12 ዓመታት ሂሳብ ሲሰላ ከ 1.7 ቢልዮን ዶላር በላይ ኪሳራ ያስመዘገበ ሲሆን ኮሮና ያመጣበት አዲስ ችግር ደግሞ ካለበት ከፍተኛ የብድር መጠን ጋር ተደምሮ ዳግም እንዳያንሰራራ ሊቀበርው እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡ ይህንን አጋጣሚ ተከትሎም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደቡብ አፍሪካው ተቀናቃኙ ጋር ድርድር መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ድርድሩ በዚሁ ከቀጠለ አክስዮን ከመግዛት እስከ የአስተዳደር ኮንትራት የመውሰድ ወይም ደግሞ በአጋርነት የመስራት እድል ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሊፈጥርለት ይችላል፡፡

በተጨማሪም ከሞሪሸስ መንግስት ጋር ተመሳሳይ ድርድር መጀመሩን አቶ ተወልደ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛምብያ አየር መንገድ ላይ የ45 ፐርሰንት የባለቤትነት ድርሻ ያለው ሲሆን “ኤ ኤስ ኬ ዋይ” ተብሎ በሚጠራው ሙሉ በሙሉ በግል ይዞታ ላይ ባለው የትጎ አየር መንገድ ደግሞ የ40 ፐርሰንት የባለቤትነት ድርሻ እንዲሁም በማላዊ አየር መንገድ የ49 ድርሻ አለው፡፡ ከደቡብ አፍሪካና ከሞሪሸስ ጋር እየተደረገ ባለው ድርድር ወደ ስምምነት ከተደረሰም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የአየር በረራ ንግድ ላይ ያለው ባለ ድርሻነት እንዲጨምርና ተፅዕኖ ፈጣሪነቱ ይበልጡን እንዲጎላ ይረዳዋል፡፡

ሆኖም አየር መንገዱን እዚህ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያደረገው የመንገደኞች በረራ አገልግሎት 90 ፐርሰንት ተስተጓጉሎ እንዳለ ከቀጠለ በሚቀጥሉት 2 ወራት የኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ ማስፈለጉ አይቀሬ ነው፡፡ ከፍተኛ የዶላር እጥረት ያለበት የኢትዮጵያ መንግስትም ለአየር መንገዱ የማገዝ አቅሙ ይህ ነው ባይባልም ለአገር ውስጥ ሰራተኞችና ሌሎች የአገር ውስጥ ወጪዎች የሚያግዝ ድጋፍ በብር ሊያደርግ ይችላል፡፡ ያም ሆነ ይህ አየር መንገዱ ከጭነት ማመላለሻ ንግዱ እያገኘ ያለው ተጨማሪ ገቢ አየር መንገዱ ከመንገደኞች በረራ መስተጓጎል ያጣውን ገቢ ሙሉ በሙሉ ባያካክስለትም ለወደፊት በጭነቱ በኩል ግዙፍ የመስፋፋት ዕድል እንዳለ የኮሮና ወረርሽኝ ያልታሰበ ፍንጭ ሰጥቷል፡፡

- Advertisement -

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -