Saturday, January 22, 2022

የውጭ የቴሌኮም ኩባንያዎች በጉጉት እየተጠባበቁ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስት ጨክኖ ሊወስን አልቻለም

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከጀመሯቸው የኢኮኖሚ ለውጦች አንዱ የአገሪቱን የቴሌኮም ዘርፍ ለውጭ አገር ኩባንያዎችና ባለሃብቶች ክፍት ማድረግ ነው። ኢትዮጵያ በቀድሞው የኢህአዴግ መንግስት ዘመን ትከተለው በነበረው የልማታዊ መንግስት የኢኮኖሚ መርህ እንደ ቴሌኮም ያሉ ቁልፍ ዘርፎች በመንግስት እጅ እንዲቆዩ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ወደ የምዕራባውያን የነፃ ገበያ ርዕዮት ዓለም የሚያደሉት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በበኩላቸው እነዚህን ቁልፍ ዘርፎች ከመንግስት እጅ በማላቀቅ ለውጭ የግል ባለሃብቶች መሸጥ አለባቸው የሚል እምነት አላቸው። በዚህም መሰረት የአገሪቱ ብቸኛ የቴሌ ኩባንያ ሆኖ የቆየውን የኢትዮ ቴሌ እስከ 40 ፐርሰንት የሚሆን ድርሻ ለውጭ ባለሃብቶች በአክስዮን መልክ እንዲሸጥና በሌላ በኩል ደግሞ ሁለት አዳዲስ የንግድ ፈቃዶች ከውጭ መተው አገልግሎት ለሚሰጡ የቴሌኮም ኩባንያዎች በጨረታ እንዲሸጡ መወሰኑ ይታወሳል።

ይህ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ ውሳኔ በርካታ የአውሮፓና የአረብ አገራትን እንዲሁም አሜሪካን ትልቅ ጉጉት ውስጥ በመክተቱ እነዚህ አገራት ኢትዮጵያን በተለያየ መልኩ ለማማለል ሲሞክሩ ታይተዋል። የተባበሩት አረብ ኤመሬትና ሳውዲ አረብያ ለኩባንያዎቻቸው የንግድ ፈቃድን ለማስገኘት ከመጋረጃ በስተጀርባ ጥረት ሲያደርጉ እንደቆዩ አንዳንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የኢትዮኖሚክስ ምንጮች ገልፀዋል። በተጨማሪም የፈረንሳይ፣ የእንግሊዝ፣ የቻይና፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የኬንያና የማዳጋስካር ኩባንያዎች የቴሌኮም ንግድ ፈቃዱ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ማመልከታቸውን የኢትዮጵያ ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ይፋ አድርጓል።

በሌካ በኩል ለጨረታ ከሚቀርቡት ሁለት አዳዲስ ንግድ ፈቃዶች በተጨማሪ በኢትዮጵያ መንግስት እጅ ያለውን የቴሌን ባለቤትነት እስከ 40 ፐርሰንት የሚሆን ድርሻ ለግል ባለሃብቶች ለመሸጥ መወሰኑን ተከትሎ ከበረከቱ ለመቋደስ ከአሜሪካና ከአውሮፓ የመጡ ደላሎች፣ አማካሪዎችና የባለሃብት ተወካዮች በአዲስ አበባ ሆቴሎች ከመሸጉ ቆየት ብለዋል። የቴሌን ንብረትና ገቢ ወጪ ስሌት ለመስራት ከተቀጠረው የኒውዮርኩ ኬ.ፒ.ኤም.ጂ ጀምሮ በከፊል የሚደረገውን የሽያጭ ሂደት ለማማከር እስከተቀጠረው የለንደኑ አማካሪ ድርጅት ዴሎይት ድረስ ከቴሌ የከፊል ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ ላይ ለነዚህ ደላሎችና አማካሪዎች በመቶ ሚልዮኖች የሚቆጠር ዶላር ኢትዮጵያ የምትከፍል ይሆናል።

እጅግ ትርፋማ ከሆኑ የንግድ ዘርፎች የሚመደበው የቴሌኮም ዘርፍ በአብዛኛው የዓለም ክፍል በኩባንያዎች መካከል ፉክክሩ እየተጧጧፈ በመምጣቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ትርፋማነቱን እንዲቀንስ አድርጎታል። በተለይም አፍሪካን ጨምሮ አብዛኛው የዓለም ሕዝብ የስልክና የኢንተርኔት ተጠቃሚ መሆኑ አዳዲስና ስልክ የሌላቸው ተጠቃሚዎችን የማግኘት እድል ከእለት እለት እየጠበበ መጥቷል። ሆኖም ወደ 110 ሚልዮን የሚገመት የሕዝብ ቁጥር ያላት ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ሕዝቧ ውስጥ የስልክ ተጠቃሚ የሆነው ከ50 ፐርሰንት በታች ሲሆን ኢንተርኔት ተጠቃሚው ደግሞ ገና 21 ፐርሰንት ላይ ነው። ይህም ወደ አገር ለሚመጣ ማንኛውም የውጭ ቴሌኮም ኩባንያ ሰፊ የማደግ እድልን የሚሰጥ ነው። ይባስ ብሎም በአገሪቱ አንድና ብቸኛ በመንግስት እጅ ያለ ኋላ ቀር የቴሌኮም ኩባንያ መኖሩ ለመጭዎቹ ሁለት የውጭ ኩባንያዎች ሰፊ የመስፋፋትና የማደግ እድልን የሚፈጥር ነው ። ለዚህም ነው በተለያዩ አገራት ያሉ የቴሌኮም ኩባንያዎች የጠቅላይ ሚንስትር አብይን ውሳኔ እንደሰሙ ምራቃቸውን መዋጥ የጀመሩት።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት ሁለቱን የንግድ ፍቃዶች በጨረታ እሸጣለው እንዲሁም ቴሌን በከፊል እሸጣለው ብሎ እንቅስቃሴ ከጀመረ ሁለት ዓመት ቢሞላውም እስካሁን ጨክኖ ሊያደርገው አልቻለም። ኬ.ፒ.ኤም.ጂ እና ድሎይት የቴሌን የሂሳብ ስሌትና ለመስራትና የሽያጭ ሂደቱን ለማማከር ከመንግስት ጋር የተስማሙ ሲሆን የንግድ ፍቃድ ተጫራች ኩባንያዎችም የተጠየቁትን አሟልተው የጨረታውን ቀን በጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ ። ታድያ እስካሁን መንግስት ሊወስን ያልቻለው በምን ምክንያት ነው?

በመጀመርያ ስለ ቴሌ በከፊል የመሸጥ ጉዳይ እንመልከት። የቀድሞው የኢህአዴግ መንግስት ይከተለው የነበረው የልማታዊ መንግስት የኢኮኖሚ መርህ ኢትዮጵያ ያለባትን የመሠረተ ልማት ጉድለቶች እስክታሟላ ድረስ ኢኮኖሚዋ በመንግስት መመራት አለበት የሚል ነበር። የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ያስረዱት እንደነበረው የግሉ ዘርፍ ዋነኛ አላማ ትርፍን ማግኘት በመሆኑ አብዛኛው ትኩረቱ የሚሆነው በከተሞችና ትርፍ በቀላሉ በሚገኝባቸው እንደ የቤቶችና የሕንፃ ግንባታ፣ ከውጭ እቃ የማስገባት ንግድ፣ እንዲሁም ሌሎች እንደ መዝናኛ አገልግሎት ባሉ ዘርፎች ላይ ነው። ይህም ለኢትዮጵያ እጅግ የሚያስፈልጓት የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በተለይም ገጠር ተኮር የሆኑ እንደ መንገዶች፣ ግድቦች፣ ትምህርት ቤቶች ፣ ሆስፒታሎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ እንዲሁም የግብርናው ዘርፍ ትኩረት እንዲያጡ ያደርጋቸዋል። የግሉ ዘርፍ ምናልባት ለነዚህ መሠረተ ልማቶች ትኩረት መስጠት ቢጀምር እንኳን ዓላማው ትርፍ ማግኘት እስከሆነ ድረስ ለገበሬዎች ነፃ ትምህርት ቤት አይሰራም፣ መንገድም ሆነ ግድብ ሲገነባ የሚጠይቀው ክፍያ የኢትዮጵያን ኪስ የሚያራቁት ነው ሲሉ አቶ መለስ በተለያዩ መድረኮች ላይ ይከራከሩ ነበር።

እንደ አቶ መለስ እይታ ኢትዮጵያ በቂ መሠረተ ልማት እስኪኖራትና የአገሪቱን ሕዝብ ከ70 ፐርሰንት በላይ የሚሆነው ገበሬ መሠረታዊ ፍላጎቶቹ እስኪሟሉለት ድረስ መንግስት ሃላፊነት ወስዶ ኢኮኖሚውን በልማት ተኮር መርህ መምራት አለበት። ልማታዊ መንግስት የሚለው መጠርያም ከዚህ ጋር ተያይዞ የመጣ ሲሆን የእስያ ነብሮች የሚባሉት ሲንጋፖር፣ ታይዋን፣ ደቡብ ኮርያና ሆንግኮንግ እንዲሁም በተወሰነ መልኩ ቻይናና ጃፓን በአጭር ጊዜ ፈጣን እድገት ያሳዩት ይህንን መርህ በመከተል ነበር። ታድያ እነዚህን መሠረተ ልማቶች ለመገንባት መንግስት በቂ የሆነ አቅም የለውም። ኢትዮጵያ እንደ አረብ አገራት የነዳጅ ሃብት ወይም እንደ ኮንጎና ደቡብ አፍሪካ በማዕድን የተትረፈረፈች አገር አይደለችም። ስለዚህም የኢሃአዴግ መንግስት ለመሠረተ ልማት ለሚያውለው ገንዘብ ዋና ምንጭ ሆነው እንዲያገለግሉ ከተጠቀመባቸው ዘዴዎች አንዱ ቴሌን በመንግስት እጅ እንዲቆይና ተፎካካሪ የውጭም ሆነ የአገር ውስጥ ኩባንያዎች እንዳይኖሩ በመዝጋት በየዓመቱ የቴሌን በቢልዮኖች ብር የሚቆጠር ትርፍ ወደ መንግስት ካዝና ማስገባት ነበር።

(ግራ) የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ (ቀኝ) የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ጎርደን ብራውን – 2004 አዲስ አበባ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም – ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ከመሞታቸው 3 ወር በፊት ስለ ልማታዊ መንግስት ሲያብራሩ

ይህ በምዕራባውያን ዘንድ ተቀባይነት ያልነበረው አሰራር ነው። የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ የዩንቨርስቲ ትምህርት ነፃ መሆን የለበትም በሚል አቋሙ የሚታወቅ ነው። በአንድ ወቅት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሃለማርያም ደሳለኝ ከሮይተርስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ለምን የውጭ ባንኮችና የቴሌ ኩባንያዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ አትፈቅዱም ለሚለው ጥያቄ በሰጡት መልስ “የውጭ አገራት ባለሃብቶች ለምን ቴሌን ወደ ግል አታዘዋውሩትም እያሉ የሚጨቀጭቁን የአገራችንን ቴሌ እንደምትታለም ላም ስለሚያዩት ነው፤ እኛ ግን ቴሌን የማንሸጠው በአገሪቱ እየገነባን ያለነውን የባቡር መስመር ወጪ የምንሸፍነው ከቴሌና ከባንኮቻችን በምናገኘው ትርፍ ስለሆነ ነው” ሲሉ አብራርተው ነበር። ይሁን እንጂ ኢህአዴግ ቴሌን በመንግስት እጅ አቆይቶ ያስተዳደርበት የነበረው መንገድ ከፖለቲካ ነፃ ያልነበረ በመሆኑ ተቋሙን ለብዙ ሙስናና የሃብት ብክነት ብሎም የቴክኖሎጂ ኋላ ቀርነት ዳርጎታል የሚል ትችት ሲዘነዘርበት ቆይቷል።

ታድያ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከልማታዊ መንግስት መር ወደ ነፃ ገበያ መር ለማሸጋገር ፍላጎት ያላቸው የአሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ቴሌን በከፊል ለመሸጥ የፈለጉበት ምክንያት በአንዳንዶች ዘንድ ተቀባይነትን አላገኘም። በተለይም የሽያጩ ሂደት ያለበቂ ምክክርና ሚስጥራዊ በሚመስል ሁኔታ መካሄዱ መንግስት በሕዝብ ተመርጦ ስልጣን እስኪይዝ ድረስ ሽያጩን ያቆይ አልያም በሂደቱ ላይ ባለ ድርሻ አካላትን ያሳትፍ የሚል ጥያቄ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲነሳ አድርጎታል። በተለይም በቴሌ ሽያጭ ላይ ከፍተኛውን ተቃውሞ እያሳዩ ያሉት ኢዜማና ህወሃት ሲሆኑ ኢዜማ ሰኔ 18 ቀን ባወጣው መግለጫ “ገዢው ፓርቲ ያለበቂ ውይይት እና ግልፅነት በጎደለው መልኩ የኢትዮ ቴሌኮምን ከፊል ድርሻ ለመሸጥ እየሄደበት ያለው ጥድፍያ በአስቸኳይ ይቁም” ሲል ጠይቋል። የኢዜማው መሪ ኢኮኖሚስቱ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከወራት በፊት በሰጡት የእንግሊዘኛ ቃለ መጠይቅ ላይም “መንግስት ዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ያሉትን ሁሉ እየተቀበለ መተግበሩ አደጋ አለው” ሲሉ ትችት አቅርበዋል።

ቴሌ ተሽጦ የሚገኘው ገቢ አገሪቱም ሆነ እራሱ ቴሌ ያለበትን እዳ ለመክፈል ይረዳል ብለው የሚያምኑት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ መንግስታቸው ሽያጩን እንዲያፋጥን ከምዕራባውያን በተለይም ከዓለም ባንክና ከዓለም የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ግፊት እየተደረገበት ሲሆን በአንፃሩ ከአገር ውስጥ እየተሰማ ያለው ከፍተኛ ተቃውሞ የሽያጩ ሂደት እንዲጓተት አድርጎታል። አይ ኤም ኤፍ ከወራት በፊት ባወጣው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትንታኔ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ ውሳኔ ላይ ተቃውሞ በመብዛቱ በወቅቱ መራዘሙ ይፋ ሆኖ ያልነበረው “ምርጫ ከተካሄደ የቴሌንና የሌሎች ተቋማትን ሽያጭ ሊያስተጓጉል ይችላል” ብሏል።

ሌላው አወዛጋቢ እየሆነ የመጣው ሁለት አዳዲስ የቴሌኮም ንግድ ፈቃዶችን ለውጭ ኩባንያዎች በጨረታ የመሸጥ ውሳኔ ነው። ቴሌ ለዓመታት ሲገነባቸው የቆየው የፋይበር ኦፕቲክ መስመሮችና የማሰራጫ ምሰሶዎች ለተቋሙ ልዩ ጥቅምን የሚሰጡ ሲሆን እነዚህን መስመሮችና ምሰሶዎች ከውጭ ለሚመጡት ተፎካካሪ ኩባንያዎች በማከራየት ትልቅ ገቢ የማግኘት እድል የፈጠርለታል። ተፎካካሪዎች ይዘውት የሚመጡት አዳዲስና የረቀቀ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎችን በመሳብ ቴሌን ደንበኞቹን እንዲያጣ ሊያደርገው ይችላል የሚል ፍርሃት ቢኖርም የተዘረጉ መስመሮቹንና ምሰሶዎቹን ከውጭ ለሚመጡት ኩባንያዎች ከማከራየት በሚያገኘው ገቢ የደንበኛ ፍልሰቱን ሊያካክስ ይችላል። ሆኖም ኩባንያዎቹ መስመር ዘርግተው ከሚያከራዩ የውጭ ድርጅቶች ጋር እንድንሰራ ይፈቀድልን የሚል ጥያቄ አቅርበው የኢትዮጵያን መንግስት ማሳመናቸው ቴሌን ያስቆጣ ሲሆን በወይዘሮ ፍሬሂወት ታምሩ የሚመራውን የቴሌ አስተዳደር ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር አተካራ ውስጥ ከቶታል።

ይህንን ተከትሎም መንግስት ለውጭ ኩባንያዎች የራሳቸው መስመር መዘርጋትና ምሰሶ ማቆም እንደሚችሉ ነገር ግን የቴሌ አገልግሎት ሳይሰጡ መስመር ብቻ እየዘረጉ የሚያከራዩ ድርጅቶች አገር ውስጥ እንዲገቡ እንደማይፈቅድ ከሁለት ሳምንት በፊት ይፋ አድርጓል። ይህ ውሳኔ ኩባንያዎቹ ወይ ከኢትዮ ቴሌ መስመር እንዲከራዩ አልያም የራሳቸውን መስመር እንዲዘረጉ ስለሚያስገድድ ከሁለቱ የንግድ ፍቃዶች ጨረታ የሚገኘውን ገቢ ሊያሳንሰው ይችላል። ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ሰሞኑን ኢትዮጵያ ንግድ ፍቃዶቹን የመሸጥ ሃሳቧን ሙሉ በሙሉ ሰርዛዋለች የሚል ሙሉ በሙሉ ያልተረጋገጠ ዜና መሰማት የተጀመረው። ዕሮብ እለት ክዋርትዝ አፍሪካ የተባለው ጋዜጣ ላይ በወጣው ፅሁፍ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸችው ምንጮቼ ደረሰኝ ባለው መረጃ የኢትዮጵያ ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ሃሳቡን እንደቀየረና ለውጭ ኩባንያዎች የንግድ ፍቃድ እንደማይሰጥ ገልጿል።

በእርግጥ ቴሌ ያለምንም ተፎካካሪ አገሪቱን መቆጣጠሩ ተቋሙ የመሻሻል ፍላጎት እንዳይኖረው አድርጎ የቆየ ሲሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ዋጋ እጅግ ውድ ከሆኑባቸው አገራት እንድትመደብ አድርጓት ነበር። ቴሌ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ያደረገው የዋጋና የጥራት መሻሻል እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት መስፋፋት የታየው የውጭ ተፎካካሪዎች ወደ አገር ውስጥ ሊመጡ ነው የሚለውን ዜና ተከትሎ መሆኑ የፉክክር መንፈስ ምን ያህል ወደ አገልግሎት ጥራት እንደሚመራና ለተጠቃሚዎች እንዴት እንደሚጠቅም ማሳያ ነው። የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በማገናዘብ የቴሌ የከፊል ድርሻ መሸጥ ቢቀርና አሁን ባለው የመንግስት ሙሉ ይዞታ ቢቆይ ነገር ግን እነዚህ የውጭ ተፎካካሪዎች የራሳቸው የፋይበር ኦፕቲክ መስመር እንዳይዘረጉ እገዳ በማድረግ ቴሌን ከኪሳራ መጠበቅ የኢትዮጵያ መንግስት ለመሠረተ ልማት የሚሆነውን ገንዘብ ከቴሌ ማግኘቱን እንዲቀጥል የሚረዳ ይሆናል። ሆኖም በኢህአዴግ ዘመን በቴሌ የታየው ችግር እንዳይደገም ተቋሙ ልክ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፖለቲካ ነፃ በሆነ መልኩና የሙያ ብቃት ባላቸው አካላት እንዲመራ ማድረጉ ተገቢ ነው።

በሌላ በኩል ለተፎካካሪዎች የሚሰጠው የንግድ ፍቃድ ባይቀርና ግልፅነት በተሞላበት እንዲሁም አሳታፊ በሆነ መልኩ ቢደረግ በዘርፉ የፉክክር መንፈስ እንዲኖርና የአገልግሎት ጥራት ሁሌም እየተሻሻለ እንዲሄድ የሚያመቻች ነው። ኢትዮኖሚክስ

- Advertisement -

1 COMMENT

 1. #ዋጋ_የሚያወጣልህን_ንብረት_የቸገረህ_ጊዜ_አትሽጠው ‼️

  የኢትዮ ቴሌኮም 40% ድርሻ ለሁለት ተጨማሪ የቴሌኮም ኩባንያዎችም ፈቃድ ለመስጠት እንደታሰበ ሰማሁ።

  መንግስት ንግዱን ለግሉ ዘርፍ እየተወ ወደ ግብር መሰብሰብና ??????????? ሚናው ባግባቡ ወደመወጣት ማዘንበሉን የምደግፈው ሐሳብ ነው።

  #-ነገር_ግን_አገሪቱ_በኮሮና_ስጋት_ተውጣ፣ #በህገ_መንግስታዊና_የምርጫ_ቀውስ_አፋፍ_ላይ_ሆና፣
  #-በህዳሴው_ግድብ_ምክንያት_የደህንነት_ስጋት_አለብኝ_እየተባለ
  #በአመት_20_ቢሊዮን_ብር_የሚያተርፍን_ድርጅት_ለመሸጥ_መንግስት_ለምን_ይጣደፋል?

  ከዚያ በፊት እንደህዝብ የሰጠነው አደራ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ አድርጎ ቅቡልነት ያለው መንግስት እንዲመሰረት እንጂ ንብረታችንን እንዲሸጥ ነበር እንዴ? መንግስት ያሉትን አማራጮችና ኃብቶች ተጠቅሞ ሙሉ ትኩረቱን ለምን ወደ ኮሮና አያደርግም?

  በዘላቂና በመጪው ትውልድ ህይወት ጭምር ተፅዕኗቸው ብርቱ የሆኑ ጉዳዮችን በይደር በመያዝ አብዛኛው ህዝብ የኔ የሚለው ህዝባዊ መንግስት ሲኖረን የመንግስት ድርጅቶችን ያውም እጅግ አትራፊ የሆኑትን እንደ ኢትዮ ቴሌኮም አይነቶቹን በከፊልም ሆነ በሙሉ ወደ ግል ይዞታ ማዞር ካለብን ለምን ያኔ አናደርገውም?

  #አሁን_ሙሉ_ትኩረት_ኮሮና_ላይ_ይሁን፤ ከዛ የተረፈውን ደግሞ ምርጫውን ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ ማድረግ ላይ ቢሆን እንደ አገር ብዙ እናተርፋለን።

  #ዋጋ_የሚያወጣልህን_ንብረት_የቸገረህ_ጊዜ_አትሽጠው ‼️

  #Stay_Home ? Stay_safe
  #COVID19Ethiopia
  #Ethiopia

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -