አሜሪካ ትልቋ ባለ ድርሻ የሆነችበት የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ለመስጠት አቅዶ የነበረውን 500 ሚልዮን ዶላር አግዷል የሚል የውስጥ አዋቂ መረጃ ደርሶኛል የሚል ዜና ያወጣው ኢትዮጵያን ኢንሳይደር የተባለው የእንግሊዘኛ ድህረ ገፅ የዶላር ዋጋ አሁን በባንክ እየተሸጠ ካለበት 34 ብር ጨምሮ በጥቁር ገበያ ከሚሸጥበት ዋጋ እኩል እንዲሆን እፈልጋለው ቢልም የኢትዮጵያ መንግስት በተፈለገው ፍጥነት እየተገበረው ባለመሆኑ የገንዘብ ድጋፉን አግጃለው ማለቱን ከደቂቃዎች በፊት የወጣው ዘገባ ይገልፃል፡፡ ባንኩ በተጨማሪም ከሃይል ማመንጨት ዘርፉ ጋር ተያይዞ እየተካሄደ ያለው ለውጥ በተፈለገው መልኩ ኢትዮጵያ እየተገበረችው አይደለም የሚል ምክንያት ማቅረቡም ተሰምቷል፡፡
ሆኖም ከተመሰረተ ጀምሮ በአሜሪካውያን ዋና ዳይሬክተሮች ብቻ ሲመራ የይኖረውና አሜሪካ ትልቋ ባለ ድርሻ የሆነችበት ባንክ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ከግብፅ ጋር ሳትስማማ እንዳትሞላ የሚል ትዕዛዝ ከሳምንታት በፊት ማስተላለፉ ገንዘቡን የማገድ ውሳኔው ኢትዮጵያ ግድቡን እሞላለው ከማለቷ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይገመታል፡፡ ዋና ፅህፈት ቤቱን በዋሺንግተን ዲሲ ከዋይት ሃውስ በ600 መቶ ሜትር ርቀት ላይ ያደረገው የዓለም ባንክ ባለፈው ጥር ወር ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር በግድቡ ዙርያ ለመደራደር በሄደችበት ወቅት እንደ አደራዳሪ ሆነው ከቀረቡት ሁለት አካላት አንዱ ሲሆን ሌላኛው አካል ደግሞ በአሜሪካው የግምዣ ቤት ዋና ፀሃፊ ስቲቭን ምዩንሽን የተወከለ ነበር፡፡ ታድያ ጉዳዩን የሚያወሳስበው አሜሪካ በባንኩ ያላትን ድርሻ ወክለው ድምፅ የሚሰጡት በሌላ በኩል እንደ ሁለተኛ አደራዳሪ የቀረቡት እራሳቸው የግምዣ ቤቱ ፀሃፊ ስቲቭን ምዩንሽን መሆናቸው ኢትዮጵያን ባልታሰበ ወጥመድ ውስጥ አስገብቷት ነበር፡፡
የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በብድርና በስጦታ መልክ ለመስጠት ቃል ሲገባ የቆየው የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ እንደ ቴሌና አየር መንገድን ያሉ ተቋማትን ለውጭ ባለሃብቶች እንድትሸጥ ከፍተኛ ግፊት ከማድረግም አልፎ እንደ ቅድመ ሁኔታ ሲያቀርበው ቆይቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በልማታዊ መንግስት ከሚመራ ኢኮኖሚ ወደ ነፃ ገበያ መር የሚደረገውን ለውጥ ከዓለም የገንዘብ ተቋም ጋር በመሆን በዋነኛነት እየመራ ይገኛል፡፡
You have mentioned very interesting points! ps decent website . “By their own follies they perished, the fools.” by Homer.