Tuesday, July 27, 2021

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ቃል ገብቶት የነበረውን ከ2 ቢልዮን ዶላር በላይ አገደ – ዋዜማ ሬድዮ

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

ከታማኝ ምንጭ መረጃ ደረሰኝ ያለው ዋዜማ ሬድዮ ዛሬ ጠዋት በድህረ ገፁ ባወጣው ፅሁፍ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የተጀመረውን ለውጥ ለማገዝ ቃል ገብቶት የነበረውን ከ2 ቢልዮን ዶላር በላይ የሚገመት የብድርና ድጎማ ድጋፍ ማገዱን ዘግቧል። በኢኮኖሚ ፖሊሲ አለመግባባት ምክንያት ከቀድሞው የኢህአዴግ መንግስት ጋር የሻከረ ግንኙነት የነበረው የዓለም ባንክ ባለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት አግኝቶ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ቀናት ወዲህ ግን ከመንግስት ጋር አለመግባባት ውስጥ የገባ ይመስላል።

በአሜሪካዊው ዴቪድ ማላፓስ የሚመራው የዓለም ባንክ ባሳለፍነው የካቲት ወር በህዳሴ ግድብ ዙርያ ኢትዮጵያን ከግብፅና ሱዳን ጋር እንዲያደራድሩ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከተመረጡት ሁለት አካላት አንዱ የነበረ ሲሆን በወቅቱ አደራዳሪዎቹ ለግብፅ ወገንተኝነትን አሳይተዋል በሚል ኢትዮጵያ የዋሽንግተን ዲሲውን ድርድር አቋርጣ ወታለች። ይህንን ተከትሎም ከአሜሪካ መንግስት በኩል ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ስምምነት ላይ ከመደረሷ በፊት የህዳሴ ግድብ ሙሌት እንዳይካሄድ የሚል ማስጠንቀቅያ በተደጋጋሚ ተሰምቶ ነበር። ዋዜማ ሬድዮ ከውስጥ አዋቂ አገኘሁት ባለው መረጃ መሠረት እገዳው ሰብአዊ እርዳታዎችንና ለኮቪድ19 የሚውሉ ድጋፎችን የማይመለከት ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ የጀመሩትን ከልማታዊ መንግስት ወደ የነፃ ገበያ መር ኢኮኖሚ የሚደረግ ለውጥ ለማገዝ በሚል ኢትዮጵያ በብድርና በበጀት ድጎማ መልክ ሊሰጣት የነበረው ከሁለት ቢልየን ዶላር በላይ ግን ተቋርጧል።

ኢትዮጵያ ጥቅማቸው በውል የማይታወቁና አንዳንዴም ጉዳታቸው የሚያመዝን የኢኮኖሚ ለውጦችን በችኮላ እንድታደርግ የዓለም ባንክ ጫና እያደረገ ነው በሚል ኢትዮጵያውያን የኢኮኖሚ ባለሙያዎችና ፖለቲከኞች ተቃውሞ እያሰሙ የቆዩ ቢሆንም የባንኩን ምክሮች መንግስት ከሞላ ጎደል ተቀብሎ ሲተገብረው መታየቱ ባንኩ ድጋፍ እስከ ማገድ የሚያደርስ ምክንያት እንዳልነበረውና ጉዳዩም ከህዳሴ ግድብ ጋር የተያያዘ መሆኑን የሚያመላክት ነው። የአለም ባንክ ባለድርሻ ከሆኑት አባል አገራት ውስጥ ትልቁን ቦታ የምትይዘው አሜሪካ ስትሆን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ከተመሠረተ ጀምሮ በታሪኩ የባንኩ ፕሬዝዳንቶች አሜሪካውያን ብቻ ሆነው ኖረዋል። ይህም ተቋሙ በአሜሪካ መንግስት ተፅዕኖ ሳይጥለው እንዳልቀረ በተለያዩ ጊዜያት ባለ ድርሻ አካላት ሲያስጠነቅቁ ኖረዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በአንድ ወቅት “ከዓለም ባንክ መበደር ከእናት እንደ መበደር ነው” የሚል ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎም በማወቅም ሆነ ባለ ማወቅ ለባንኩ ኢትዮጵያ ውስጥ ስር የሰደደ ተፅዕኖ የመፍጠር እድልን አመቻችተውለታል የሚል ስጋትን በብዙዎች ዘንድ ሊፈጥር ችሏል። ከሳምንት በፊት አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከምታደርገው ዓመታዊ እርዳታ እስከ 130 ሚልዮን ዶላር በሚሆነው ላይ እገዳ ማድረጓ የሚታወስ ሲሆን በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ ፍጹም አረጋም ስለ ጉዳዩ የአሜሪካንን መንግስት ማብራርያ እንደጠየቁና እገዳውም ጊዜያዊ መሆኑን እንደተረዱ በትላንትናው እለት ይፋ አድርገዋል።

የአንድ አገር መንግስት በኢኮኖሚው ላይ ያለው ሚና የተወሰነ መሆን አለበት የሚል መርህ የሚያራምደው የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ መንግስት የሚገነባቸውን ዩንቨርስቲዎች ቁጥር እንዲቀንስ ብሎም ተማሪዎችን ማስከፈል እንዲጀምር፣ መንግስት ግድቦችን ከመገንባት እንዲቆጠብ፣ እንዲሁም ለገበሬዎች በድጎማ የሚያከፋፈለው ማዳበርያና የእህል ዘር ተቋርጦ ለግል ነጋዴዎች ቦታ እንዲለቅ በሚል ከቀድሞው የኢትዮጵያ መንግስት ጋር በተደጋጋሚ እሰጣገባ ውስጥ በመግባቱ ባንኩ ከኢትዮጵያ ጋር የነበረው ግንኙነት እንዲዳከምና አንዳንድ ቢሮዎቹም እንዲዘጉ ዳርጎት ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዓመት ከ800 ሚልዮን ዶላር በላይ እርዳታ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው አሜሪካ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ውሳኔ ከፊል እገዳ ትጣል እንጂ ፕሬዝዳንቱ ቀሪውን እርዳታ ለማቋረጥ ቢፈልጉ እንኳን በአገሪቱ ምክር ቤት ማፀደቅ ስለሚኖርባቸው ከምክር ቤቱ ጋር ወደ ውዝግብ ላለመግባት ሲሉ የዓለም ባንክን እንደ ማስፈራርያ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ኢትዮኖሚክስ ከሁለት ቀን በፊት አሳስባ ነበር። ፕሬዝዳንቱ አሁንም ኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና ለማጠናከር ካሰቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሜሪካ የሚያደርገውን በረራ እስከ ማቋረጥ የሚደርስ ውሳኔ ሊያሳልፉ ይችላሉ።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በእስራኤልና ፍልስጤም መካከል ስምምነትን ለማምጣት ከአራት ዓመት በፊት በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም ያመጡት የመፍትሄ ሃሳብ ለእስራኤል ያደላ ነው በሚል ተቃውሞን ገጥሞታል። አንድ አንድ ተንታኞች እንደሚገልፁትም ፕሬዝዳንቱ መጭው በነሐሴ ወር የሚደረግ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት እንደ ግብፅ ያሉ አገራትን በማሳመን የመፍትሄ ሃሳባቸው ተቀባይነት እንዲያገኝ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ በአካባቢው ተሰሚነት ያላትን ግብፅ ለማግባባት ሲሉ ራስ ምታት የሆነባትን የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ሊፈቱላት እንዳሰቡ ይገመታል።

- Advertisement -

15 COMMENTS

 1. Unquestionably believe that which you stated.

  Your favorite justification appeared to be on the web the easiest thing to be aware
  of. I say to you, I certainly get irked while people think about worries
  that they just don’t know about. You managed to hit the nail upon the top
  and defined out the whole thing without having side effect
  , people can take a signal. Will likely
  be back to get more. Thanks

 2. Whoa! This blog looks exactly like my old one! It’s on a entirely different subject but it has pretty much the same
  layout and design. Wonderful choice of colors!

 3. Attractive section of content. I just stumbled upon your weblog and in accession capital to assert that I acquire in fact
  enjoyed account your blog posts. Any way
  I’ll be subscribing to your augment and even I achievement you access consistently rapidly.

 4. Hi, Neat post. There’s a problem together with your website in web explorer, might check this?
  IE still is the market chief and a good component to people will
  pass over your excellent writing due to this problem.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -