ካፒታል ኢትዮጵያ በመባል የሚጠራውና ባለቤትነቱ የመንግስት በሆነው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ዛሬ ይፋ እንደተደረገው ግለሰቦችና ኩባንያዎች በእጃቸው የሚይዙት ጥሬ ገንዘብ መጠን ከ1.5 ሚልዮን ብር በላይ እንዳይበልጥና የተቀረው በባንክ እንዲቀመጥ የሚያዝ አዋጅ ይፋ ሆኗል።
ከሦስት ወራት በፊት ከባንክ በአንድ ጊዜ በሚደረግ ወጪ ገንዘብ ላይ ገደብ የተጣለ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በዚህ ገደብ መሰረትም ግለሰቦች በቀን ከ200 ሺህ ብር በላይ እንዲሁም በወር ከ1 ሚልዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ማውጣት አይችሉም። ለኩባንያዎች ደግሞ በቀን ከ300 ሺህ ብር በላይ በወር ደግሞ ከ2.5 ሚልዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ከባንክ እንዳያወጡ ገደብ ተጥሎባቸዋል።