Saturday, January 22, 2022

ልዩ ትንታኔ – ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የኤርትራ የወደፊት እጣ ፈንታ ክፍል ሁለት

Must Read

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ።...

ባሳለፍነው ሳምንት በተለቀቀው የክፍል አንድ ትንታኔ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሲያሳስባቸው የኖረው የኤርትራ ዘላቂ ሉአላዊነትና የጎረቤት ኢትዮጵያ በአካባቢው በኢኮኖሚ እንዲሁም በዲፕሎማሲ መግዘፍ ለወደፊት አገራቸው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር በመስጋት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያቆራኟትን ባሕላዊ፣ ሃይማኖታዊና ኢኮኖምያዊ ድልድዮች ለማፍረስ ምን ስራዎችን ሲሰሩ እንደቆዩ ኢትዮኖሚክስ ዘርዝሯል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከዚህም አልፎ ኤርትራ በአካባቢው ጠንካራ ተፅዕኖ ፈጣሪ አገር እንድትሆን ተስፋ ሳይቆርጡ በትጋት ሰርተዋል፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንደተገነጠለች ሰሞን አቶ ኢሳያስን ጨምሮ የህዝባዊ ግንባር አመራሮች ያስቀመጡት እቅድ የሲንጋፖርና የስዊድንን ኮቴ ተከትሎ በጠንካራ የኢንዱስትሪና ፋይናንስ ዘርፍ ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ አዲስ በተወለደችው አገር መትከል ነበር፡፡ በተለይም በወቅቱ በአስመራ በርካታ ፋብሪካዎችና በቂ የተማረ የሰው ሃይል የነበረ ሲሆን የተሟላ አገልግሎት መስጠት ከሚችሉ ሁለት ወደቦች እንዲሁም ካለው ጠንካራ የህግደፍ አመራር ጋር ተደምሮ እውነትም ኤርትራ የኢንዱስትሪ እድገት በአጭር ጊዜ ውስጥ ማምጣት ትችላለች የሚል ግምት በአለም አቀፉ ሕብረተሰብ ዘንድ አደረ፡፡

ነገር ግን ሰጥቶ አይሰጥምና አንድ ችግር ነበር፡፡ የአቶ ኢሳያስንና የባልደረቦቻቸውን በኢንዱስትሪ የመመንደግ ህልም ለማሳካት በቂ ጥሬ እቃ ማቅረብ የሚችል የተፈጥሮ ሃብት በኤርትራ አልነበረም፡፡ ይህንን ጠንቅቀው ያውቁ የነበሩት የኤርትራ መሪዎች ገና ጨርሳ ያልተረጋጋችው ጎረቤት አገር ኢትዮጵያ እንደ የጓሮ አትክልት ሊጠቀሙባት እንደሚችሉ ተማምነው ነበር፡፡ እንደ አቶ ኢሳያስ እምነት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የፖለቲካ አለመረጋጋት ያለባት አገር በመሆኗ በወቅቱ አዲስ አበባን የተቆጣጠረው የህወሃት መንግስት በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተቀባይነት የሌለውና በምንም መልኩ ተረጋግቶ ወደ ኢንዱስትሪና ልማት የመሄድ ዕድል ስለማይኖረው ለወደፊትም ኢትዮጵያ ብዙ የእርስ በርስ ግጭቶች የሚጠብቋት ስለሆነ የአገሪቱን የተፈጥሮ ሃብትም ሆነ የእርሻ ምርቶች ወደ ኤርትራ ለማጋዝ ብዙም አይከብድም የሚል ነበር፡፡

በተለይም አላማችንን ለማሳካት ይረዳናል ካሏቸው መንገዶች ዋነኛው በአዲስ አበባ በከፍተኛ መደራጀት በንግድ ዘርፍ ተሰማርተው ከነበሩ ኤርትራውያን ባለሃብቶች ጋር በአጋርነት በመስራትና እንደ ቡና ያሉ ምርቶችን ከኦሮምያ ክልል በብር ወደ ኤርትራ በማስገባት ቀጥሎም እነዚህን ምርቶች ወደ ውጭ በዶላር በመላክ ኤርትራ በቂ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝ፣ አልፎም እነዚሁ ኤርትራውያን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ባሉ የማዕድን ማውጣት፣ የእርሻና የፋይናንስ ዘርፎች ውስጥ እንዲሳተፉ በማበረታታት በእጅ አዙር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በኤርትራ ቁጥጥር ስር ማዋል ነበር፡፡

ሆኖም ይህንን የህግደፍ መሪዎች አላማ የሚያጨናግፍ ሁኔታ ከኢትዮጵያ በኩል ቀስ በቀስ ብቅ ማለት ጀመረ፡፡ ህወሃት ከሌሎች የታጠቁ ቡድኖች በተለይም ከኦነግ ጋር ወደ ስምምነት ደርሶ አዲስ ህገመንግስት ስለረቀቀና የፌደራል ስርዐት ማቋቋሙ በተወሰነ በኩል ከኦነግ ጋር የነበረውን ውጥረት በማርገቡ አዲስ የተመሰረተው የኢህአዴግ ግንባር በከፍተኛ የህወሃት ጫና ስር ሆኖ ኢትዮጵያን ከዳር እስከ ዳር መቆጣጠር ጀምሮ ነበር፡፡ ከዚህ በመቀጠልም እራሱ የማርክሲስት ታሪክ ያለው ህወሃትና የያኔው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ወደ ልማታዊ መንግስት የሚያደላ ፖሊሲ መቅረፅ ጀምረው በመንግስት የሚመራ ኢንዱስትሪና ግብርና ላይ ያተኮረ የኢኮኖሚ መርህ ቀስ በቀስ በኢትዮጵያ እየታየ መጣ፡፡

በተለይም በትግራይ ክልል በኤፈርት መሪነት እንደ የጨርቃጨርቅ፣ ሲሚንቶና ሌሎች ፋብሪካዎች እንዲሁም ባንኮች መቋቋም ሲጀምሩ ኤርትራውያንን እጅጉን ስጋት ላይ ከተታቸው፡፡ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የኢንዱስትሪና የፋይናንስ ዘርፍ ማቋቋም ከጀመረች ያሰቡትን ያህል ጥሬ እቃ ወደ ኤርትራ ማጋዝና ኤርትራ ውስጥ የተፈበረኩ ምርቶችን ደግሞ ኢትዮጵያ አምጥተው መሸጥ እንደማይችሉ ብሎም እራሱን እያጠናከረ የመጣው የኢህአዴግ መንግስት ኤርትራውያን ለነሱ በሚያመች መልኩ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጣልቃ እንዳይገቡ ዕድል እንደማይሰጣቸው እየተረዱ መጡ፡፡

ታድያ በዚህ ሁኔታ ተስፋ ያልቆረጡት የኤርትራ ባለስልጣናት ሌሎች ከኢትዮጵያ ጥቅም የሚያገኙባቸውን መንገዶች መፈለጉን ቀጠሉ፡፡ ለምሳሌ በወቅቱ ሁለቱም አገራት የሚጠቀሙት በኢትዮጵያ ብር ቢሆንም ኤርትራውያን ግን የራሳቸው ወደ ዶላር መዘርዘርያ ዋጋ በማውጣት ማለትም በአስመራ ባንኮች አንድ ዶላር አዲስ አበባ ከሚገዛው የብር መጠን በበለጠ እንዲዘረዘር በማድረግ አብዛኛው ከዳያስፖራም ሆነ ከነጋዴዎች የሚመጣ ዶላር ወደ ኤርትራ እንዲሄድ ሆኗል፡፡ ብዙም ሳይቆዩ ናቅፋ ተብሎ የተሰየመውን የራሳቸውን የመገበያያ ገንዘብ በማወጅ በይፋ ከኢትዮጵያ ብር ጋር ከተለያዩ በኋላ በኤርትራ መንግስትና ሃብታም ነጋዴዎች እጅ የቀረውን የኢትዮጵያ ብር በመተማመን ለኢትዮጵያ መንግስት ሁለቱ አገራት በብር መገበያየት መቀጠል አለባቸው የሚል ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በኤርትራና በኢትዮጵያ የሚደረግ ንግድ ምንም አይነት የቦርደር ቁጥጥር እንዳይኖረው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አሳሰቡ፡፡ በዚህ ሰዓት ከ60 ፐርሰንት በላይ የሚሆነው የኤርትራ ምርት ወደ ኢትዮጵያ ይላክ ነበር፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች ውድቅ ያደረገው የኢትዮጵያ መንግስትም እንደማንኛውም የጎረቤት አገር ከኤርትራም በዶላር እንደሚገበያይ ገለፀ፡፡

ይባስ ብሎም የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራ የሚገቡ የፋብሪካ ውጤቶች በጉሙሩክ ቢሮክራሲ እንዲያልፉ ማድረጉ ትግራይ ከኤርትራ በሚገቡ ምርቶች እንዳትጥለቀለቅና የራሷ ኢንዱስትሪ እንዳይዳከም ከሚል ስጋት ነው የሚሉ ግምቶች አሉ፡፡ ሆኖም ኤርትራ የተከማቸው የኢትዮጵያ ብር በህገወጥ መንገድ በትግራይ ድንበርና በሱዳን በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ቀጠለ፡፡ ከኤርትራ እየገባ ያለው ከፍተኛ መጠን ያለው የብር መጠን የዋጋ ግሽበትን ከማባባስም አልፎ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በማምጣቱ በጊዜው የነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ አዲስ የብር ኖቶች መጠቀም መጀመሯን ሳይታሰብ በድንገት ይፋ አደረጉ፡፡ ይህ የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ውሳኔ “ለአስርት አመታት በግዛትና በጦርነት ወደ ኋላ ስላስቀረችን ልትክሰን ይገባል” የሚል ጠንካራ አቋም በኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን የህግደፍ አባላት እጅጉን አበሳጨ፡፡ በተለይም በህዋሃት አመራሮች ላይ “ከሃዲዎች” በሚል ውንጀላ በኤርትራውያን ዘንድ ከፍተኛ ጥላቻን አሳደረ፡፡ ወድያውኑም ኢሃአዴግ አሁንም ቢሆን በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ስለሌለው ጦርነት ከተጀመረ የኢትዮጵያ መንግስት ይፈረካከሳል በሚል እምነት በፕሬዝዳንት ኢሳያስ ትእዛዝ የኤርትራ ሜካናይዝድ ብርጌድ ጦር ባድመን ተቆጣጠረ፡፡

Image may contain: one or more people, people standing, crowd and outdoor


ድንበሩ በውጭ ሃይል መወረሩ ውስጣዊ ክፍፍል ውስጥ የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግስትን ከማፍረስ ይልቅ ጭራሽ ከመንግስት ጎን እንዲቆም አደረገው፡፡ በተሳሳተ ስሌት ቁማር የተበሉት የኤርትራ መሪዎች እንኳን የኢትዮጵያን መንግስት ሊያፈርሱ አስመራንም ለቀው ለመሄድ ዝግጅት እስከ መጀመር የሚያደርስ ሽንፈት አጋጠማቸው፡፡ የኢትዮጵያ ጦር አስመራ ሊገባ በጥቂት ርቀት ላይ ሲደርስ እስከዛሬ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በተሰጠ ትዕዛዝ ጦሩ ሊመለስ ችሏል፡፡ ጦርነቱ ከቆመ በኋላ የህግደፍ አመራሮች የያዙት ስልት በተገኘው መንገድ ሁሉ የኢትዮጵያን መንግስት ማዳከም ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያን መንግስት ማዳከም በኤርትራ መሪዎች አይን ሁለት ጥቅም የሚኖረው ሲሆን የመጀመርያው አሁን በስራ ላይ ያለው የፌደራል ስርዐት ለወደፊትም በኤርትራ ብሔር ብሔረሰቦች ዘንድ ችግር ሊፈጥር ስለሚችል እንዲፈርስ መንገድ የሚያመቻች ሲሆን ሁለተኛው ጥቅሙ ደግሞ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ጠንክሮ የሚቆጣጠር አካል ስለማይኖር ለኤርትራ ነጋዴዎች ዕድል ስለሚከፍት ይሆናል፡፡ ከዚህም በመነሳት የህግደፍ አመራር የኢትዮጵያ መንግስት መዳከም ለኤርትራ የህልውና ጉዳይ ነው ብሎ በመደምደም በተለያዩ መንገዶች ለምሳሌ በሱማልያ በደቡብ ሱዳን እንዲሁም እንደ ኦነግና ግንቦት 7 የመሳሰሉትን ተቃዋሚዎች በመደገፍ ስራዬ ብሎ ኢትዮጵያን ሲያተራምስ ቆይቷል፡፡

ፕሬዝደንት ኢሳያስ ከኢኮኖሚው ባለፈ በፀጥታው ዘርፍም የአካባቢው ተፅዕኖ ፈጣሪ በመሆን እጅጉን የሚተማመኑበትን ጦራቸውን ወደ የመን፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ እንዲሁም ኮንጎ ልከው በአሜሪካኖች ፊት እንደ ጠንካራ የሰፈር አለቃ ለመታየትና ዲፕሎማሲያዊ ሽፋንን ከምዕራባውያን በማግኘት በጉልበት አገራቸውን ለመጥቀምም እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር፡፡ ስለዚህም በአካባቢው ተቀናቃኛቸው የነበረውን የኢህአዴግ መንግስት ይበልጡን ለመጣል እንዲጓጉ ምክንያት ሆናቸው፡፡ ነገሮችን አስፍቶ የማሰብ ችሎታና ድፍረትን የተካኑት ፕሬዝደንት ኢሳያስ በኢትዮጵያ ባይሳካላቸውም በሱዳን የሸረቡት ተመሳሳይ ሴራ በተወሰነ መልኩም ሊሳካላቸው ችሏል፡፡

በኢትዮጵያና በአካባቢው ላይ ሲያካሂዱ የቆዩት የማተራመስ ስራ የኤርትራን ኢኮኖሚ ከማድቀቁም አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ አገራቸው እንድትገለል ማድረጉ መሠረታዊ የሆኑ ፍላጎቶችን ወደ አገር ውስጥ የተፈለገውን ያህል ማስገባት እንዳይቻል አደረገ፡፡ ከነዚህ የመሠረታዊ ፍላጎቶች አንዱም የነዳጅ አቅርቦት ሲሆን ኤርትራ ነዳጅ እየገዛች ለማምጣት የሚበቃ ዶላር እጥረት አጋጥሟት ነበር፡፡ ይህንንም ችግር ለመፍታት ኤርትራ በምስራቃዊ የሱዳን ክፍል ያሉ የቤጃ አማፅያንን በማስታጠቅና በድንበሯ አስገብታ በማስልጠን ለካርቱሙ የአልበሽር መንግስት ራስ ምታትን በመስጠቷ በተለያዩ የሱዳን ክፍሎች ካሉ አማፅያን ጋር ጦርነት ውስጥ የነበረው የሱዳን መንግስት ሌላ ተጨማሪ ግጭት ውስጥ መግባት ካለመፈለግ የተነሳ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የቤጃ አማፅያንን እንዲቆጣጠሩለት ለማግባባት ከገበያ በታች በሆነ ርካሽ ዋጋ ነዳጅ ለኤርትራ እያቀረበ ለአመታት ኖሯል፡፡ ከዚህ አልፎም የኤርትራ ወታደሮች፣ የደህንነት አባላትና ከመንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች የሰሜናዊ ምስራቅ ሱዳን ክፍልን እንደፈለጉ ሲፈነጩበትና ህገወጥ የመሳርያ፣ የስደተኞችና የኮንትሮባንድ ንግድ ማዘዋወርያ ሲያደርጉት አማራጭ ያጣው የካርቱም መንግስት አይቶ እንዳላየ ሲያልፍ ቆይቷል፡፡

ፕሬዝደንት ኢሳያስ የኤርትራ ሕዝብ ለሳቸው ካለው አክብሮትና ውለታ በመነሳት ቢታገሳቸውም የኢኮኖሚ እድገትም ሆነ የዴሞክራሲ መብት ተነፍጎ ዕድሜ ልኩን ተቀብሎ እንደማይኖር ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ያሰቡትን ሳያሳኩ ከስልጣን እንዳይወርዱ በመስጋትም የሲቪል ማሕበረሰቡ በፖለቲካ እንዳይደራጅ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አግደውና የግል ሚድያ ተቋማት እንዳይኖሩ ከልክለው የቆዩ ሲሆን ኢኮኖሚውም ሙሉ በሙሉ ወይ በመንግስት እጅ ወይ ደግሞ በህግደፍ ፓርቲ በሚተዳደረው የህድሪ ኮርፖሬሽን ስር ብቻ እንዲቆይ አድርገዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ የተማረ የሰው ሃይል ከመጣ የመብት ጥያቄ ሊያመጣ ይችላል ብለው በማሰብም በኤርትራ የነበረውን ብቸኛ የአስመራ ዩንቨርስቲ አዘገዋል፡፡

Image may contain: 2 people, people sitting, table and indoor

በሌላ በኩልም የመከላከያ ሰራዊቱና የአገሪቱን ኢኮኖሚ የሚቆጣጠረውን የህግደፍ ፓርቲ ተራርቀው እንዲሰሩ አድርገዋል። ጦሩ የራሱ የሆነ የፋይናንስ አቅም እንዳይኖረው እንዲሁም ፋይናንሱን የሚቆጣጠረው የህግደፍ ፓርቲ ደግሞ የውትድርና አቅም እንዳይኖረው ሁለቱ ለየቅል ስራቸውን እንዲሰሩና በምንም አጋጣሚ እንዳይጣመሩ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በጥንቃቄ ለይተዋቸዋል፡፡ ይህ ዘዴ የጦር ጀነራሎች የፖለቲካ አቅም የሚገነቡበት ገንዘብ እንዳይኖራቸውና መንግስት ለመገልበጥ እንዳይሞክሩ ገንዘብ ያላቸው የህግደፍ ፓርቲ መሪዎች ደግሞ ፕሬዝዳንት ኢሳያስን የሚፈታተኑበት የወታደር አቅም እንዳይኖራቸው ሆን ተብሎ የተሰራበት ነው፡፡ በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የኢትዮጵያን ሜቴክ ያፈራረሱበት ፍጥነት በኤርትራና በአሜሪካ ምክር እንደሆነ አንዳንድ ድርጊቱን የሚቃወሙ አካላት ወቀሳ ሲያሰሙ ይስተዋላል፡፡

ሌላውና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተጠናከረ የመጣው የፕሬዝዳንቱ ስልጣን የማጠናከር ስልት ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ ባለው የአገራት የእርስ በርስ መናቆር ውስጥ ጣልቃ በመግባት አንዱን ከአንዱ እያፎካከሩ ጓደኝነትን በጨረታ እየሸጡ ዲፕሎማስያዊና የገንዘብ ጥቅም ማግኘት ነው፡፡ ለምሳሌ ከአስር አመታት በፊት ሳውዲ አረብያን ጨምሮ የበርካታ አረብ አገራት ጠላት ከሆነችው ኢራን ጋር ወዳጅነት መስርተው የኢራን መርከቦች በአሰብ ወደብ ላይ መታየት ጀምረው ነበር፡፡ በወቅቱም እስራኤልን ጨምሮ ምዕራባውያን ስጋታቸውን ገልፀው የነበረ ሲሆን የኢራን መሳርያ ወደ ሃማስ፣ ሄዝቦላና የየመን አማፅያን በሚያልፍበት ወቅት ኤርትራ እንደ መሸጋገርያ ምናልባትም ተባባሪ እስከመሆን ደርሳለች የሚሉ ወቀሳዎች ይሰሙ ነበር፡፡ ለዚህ ትብብሯ ኤርትራ ከኢራን የገንዘብ፣ የመሳርያና የነዳጅ እርዳታ ታገኝ ነበር ተብሎም ይገመታል፡፡

ሆኖም የተሻለ ጥቅም ያዩት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከአምስት አመታት በኋላ ቡድን በመቀየር ከነ ሳውዲና የተባበሩት አረብ ኤመሬቶች ጋር በመወገን በየመን የኢራን ወዳጆች ከሆኑትና ራሷ ኤርትራ ከዚህ በፊት ስታግዛቸው ከነበሩት የሁቲ አማፅያን ጋር በሚደረገው ውግያ እስከ ቅርብ ጊዜ ቀንደኛ ተባባሪ ነበረች፡፡ ለዚህም አስተዋፅኦዋ ሳውዲ አረብያና ኤመሪት ዳጎስ ያለ ክፍያና የነዳጅ እርዳታ አድርገውላታል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በአግባቡ የሚመራ ኢኮኖሚ ኤርትራ ውስጥ እስካሁን አላቋቋሙም፡፡ በህግደፍ ፓርቲ የተቋቋመው የህድሪ ኩባኛ አብዛኛውን ንግድ ሲያካሂድ ተቆጣጣሪ የሌለውና የሚያመጣው ናቅፋም ሆነ ዶላር በፕሬዝዳንቱ ትእዛዝ የሚንቀሳቀስ ነው፡፡ እንዲሁም አንዳንድ ጀነራሎች ሃብት እንዳያካብቱ ከንግዱ ተገለው በመቆየታቸው ጥያቄዎችን ማንሳት ስለጀመሩ በፕሬዝዳንቱ ፈቃድ ጀነራሎቹ በኤርትራ መንግስት እውቅና ከተሰጣቸው የተለያዩ በህገወጥ ንግድ ላይ ከተሰማሩ ግለሰቦች ጋር በመቀናጀት ከሱዳን እስከ ሊብያና ግብፅ ብሎም ከደቡብ ሱዳን እስከ ኡጋንዳ የሚደርስ የተደራጀ የማፍያ ቡድን አሰማርተው ይገኛሉ፡፡ ይህ ቡድን በቅርቡ መሳርያ እንዳትገዛ ማዕቀብ ወደተጣለባት ሊብያ ከአረብ ኤመሬት የመጡ የጦር መሳርያዎችን ሲያዘዋውር እንደነበር በአለም አቀፍ ሚድያ ተዘግቧል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጤንነት ጋር በተያያዘ ሳውዲ አረብያ ውስጥ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የተለያዩ ዘገባዎች እየተሰሙ ይገኛሉ፡፡ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከስልጣን ከወረዱ ድምበር ዘለል በሆነ ህገወጥ ስራ ላይ የተሰማሩት ጀነራሎች፣ የህግደፍ ፓርቲ አመራሮች፣ እንደ አፋር ባሉ ብሔር ተኮር አማፅያንና ስልጣን ይገባናል የሚሉት የሙስሊም ቡድኖች መካከል የሚደረገው የስልጣን ሽኩቻ በምስራቅ አፍሪካ ምን አይነት ተፅዕኖን ይፈጥራል? እንዲሁም ከአረቦችና ከሌሎች ሃያላን አልፎም ከኢትዮጵያ የሚደረገው ጣልቃ ገብነት እስከምን ይደርሳል የሚለውን በመጨረሻውና የክፍል ሶስት ትንታኔ ይጠብቁ፡፡

- Advertisement -

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisement -

Latest News

ሰበር ዜና – ዛሬ ረፋድ ላይ አዲግራት ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ወድቃለች

ባለፉት አራት ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ፀረ ማጥቃት የጀመረው በህወሃት የሚመራው የትግራይ ሰራዊት በርካታ ከተሞችን መቆጣጠሩን ከስፍራው የደረሰን...

“የትግራይን ሕዝብ እናጠፋዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቃል በቃል ነግረውኛል” የአውሮፓ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ

ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት የፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፔካ ሃቪስቶ በትላንትናው እለት አስደንጋጭ የሆነ ንግግር በአውሮፓ ሕብረት...

የኢትዮጵያ መንግስት ሃሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭባቸው የነበሩ ከመቶ በላይ ገፆችን ዘግቻለው ሲል ፌስቡክ አስታወቀ

የማህበራዊ ድህረገፁ ፌስቡክ በትላንትናው እለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ከመቶ በላይ የሆኑ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ንክኪ ያላቸው ገፆችን እንደዘጋ አስታወቀ። ፌስቡክ ባደረገው ውስጣዊ ምርመራ እነዚህ...

“ዳቦ ከጠፋ ለምን ኬክ አይበሉም?” አዲስ አበቤነትና የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ

እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1965 ዓ.ም በወሎ ስለተከሰተው አስከፊ ረሃብ መረጃ የደረሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምናልባት አዲስ አበባ ላይ በቂ ግንዛቤ ላይኖር ይችላል በሚል ከኒውዮርክ...

ቢሮ እንኳን ሳይኖረው የ3.6 ቢልዮን ዶላር ፕሮጀክት የወሰደው የአሜሪካ ኩባንያና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትብብር

ባሳለፍነው ታህሳስ ተቀማጭነቱን በኒውዮርክ ከተማ ባደረገ አንድ ክዋርትዝ የተሰኘ የኢንተርኔት ጋዜጣ ላይ የታተመው ፅሁፍ የኢትዮጵያን መንግስት አንገት ያስደፋና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣን ያጫረ ነበር።...
- Advertisement -

More Articles Like This

- Advertisement -